የምርጫ ቦርድ አዲሱ የምርጫ ህግ፣ መመሪያዎች፣ ህጋዊ ማዕቀፍ ነክ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል
የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ እያከናወነ ያለውን ተቋማዊ ግልጽነትን እና ተአማኒነትን የሚያሳዩ እንዲሁም የተቋም ማንነት ለውጥን የሚወክሉ መገለጫዎችን በማካተት የተቋሙን አዲስ አርማ አዘጋጅቷል። ይህም አርማ የተዘጋጀው የቦርዱን ግልጽነት በሚያሳይ እና አንድ ወጥ የሆነ የተቋም ማንነት ምስል በሚፈጥር መልኩ ነው። የዛሬው ስብሰባ አንዱ ዓላማም ይህንኑ የቦርዱን አዲስ አርማ ለባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለሕዝብ ማስተዋወቅ ነው።
