• ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ.
    ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ የቦርድ ሰብሳቢ
    ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ በተለያዩ የመንግስትና የግል ዘርፎች ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱ ሲሆን በተለያዩ የአመራር ስፍራዎችም ላይ ሠርተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ድርጅቱን ለሁለት ዓመታት በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ያገለገሉ ሲሆን በ2013 ዓ.ም. በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫም ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።
  • ውብሸት አየለ.
    ውብሸት አየለ የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ
    አቶ ውብሸት አየለ፣ በ1947 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1980 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል
  • አበራ ደገፋ (ዶ/ር).
    አበራ ደገፋ (ዶ/ር) የቦርድ አባል
    ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ በህግ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሠሩት በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሶሻል ወርክ እና ሶሻል ዴቨሎፕመንት ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
  • ብዙወርቅ ከተተ.
    ብዙወርቅ ከተተ የቦርድ አባል
    በ1952 ዓ.ም. የተወለዱት ብዙወርቅ ከተተ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በግሪክ፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኩባ ሐቫና ዩኒቨርሲቲ የውጪ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል በሥነ ቋንቋ የሁለተኛ ደረጃ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡
  • Fikre Gebrehiwot.
    ፍቅሬ ገ/ሕይወት የቦርድ አባል
    አቶ ፍቅሬ ገ/ሕይወት ከአምስቱ የቦርድ አመራር አንዱ ናቸው። አቶ ፍቅሬ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሕግና በታሪክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያገኙ ሲሆኑ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በልማት ጥናቶችና በፕሮጀክት አስተዳደር አግኝተዋል።