የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በ1,812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያስፈጸመውን የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ፣ ሰኔ 20 2015 ዓ.ም የመጨረሻውንና የተረጋገጠውን የሕዝበ ውሣኔ ውጤት ይፋ አድርጓል:: ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡ የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በጋሞ፣ በጎፋ፣ በዎላይታ፣ በጌዴኦ፣ በኮንሶና፣ በደቡብ ኦሞ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በአማሮ፣በዲራሼ፣ በባስኬቶ እና በአሌ) ሕዝበ-ውሣኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በጋሞ፣ በጎፋ፣ በዎላይታ፣ በጌዴኦ፣ በኮንሶና፣ በደቡብ ኦሞ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በአማሮ፣በዲራሼ፣ በባስኬቶ እና በአሌ) ላይ ያስፈጸመውና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረበው የሕዝበ-ውሣኔው የአፈጻጸም ሪፖርት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (በጋሞ፣ በጎፋ፣ በዎላይታ፣ በጌዴኦ፣ በኮንሶና፣ በደቡብ ኦሞ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (በቡርጂ፣ በአማሮ፣በዲራሼ፣ በባስኬቶ እና በአሌ) ሕዝበ-ውሣኔ
የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሲዳማን በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀረበ ጥያቄ መሠረት ኅዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም. የተደረገ የሕዝበ ውሣኔ ነው፡፡ በሕዝበ ውሳኔው የሲዳማ ክልልነትን መደራጀት እደግፋለሁ የሚለው አማራጭ በ98.9 በመቶ ድምፅ ያገኘ ሲሆን ስለሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡
የሲዳማ በክልልነት የመደራጀት ሕዝበ ውሳኔ
ለምርጫ አስፈፃሚነት የተመለመሉ አስፈጻሚዎች ኃላፊነት ተግባር ግዴታዎች እና የተከለከሉ ተግባራት
የአማራና ቅማንት ሕዝቦች ሕዝበ ውሳኔ
የአማራና ቅማንት ሕዝቦች ሕዝበ ውሳኔ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ጎንደር ዞን በአራት ወረዳዎች የአማራና ቅማንት ሕዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች በቅማንት ራስ አስተዳደር ወይም በአማራ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግሥት አስተዳደር መተዳደር እንደሚፈልጉ ለመወሰን መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ ነው፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡ የአማራና ቅማንት ሕዝቦች ሕዝበ ውሳኔ
የወንዶ ገነት ሕዝበ ውሳኔ
የወንዶ ገነት ሕዝበ ዉሳኔ ወረዳው በኦሮሚያ ክልል ወይስ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይካተት የሚለውን ለመወሰን ጥቅምት 30 ቀን 2001 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ ነው፡፡ ስለወንዶ ገነት ሕዝበ ወሳኔ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡ የወንዶ ገነት ሕዝበ ውሳኔ
የሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች ሕዝበ ውሳኔ
የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች ሕዝበ ውሳኔ በሁለቱ ክልሎች ወሰን ላይ በሚገኙ 463 ቀበሌዎች የሚኖሩ ሕዝቦች፣ በመረጡት ክልል እንዲተዳደሩ ለመወሰን ጥቅምት 14 ቀን 1997 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ ነው፡፡ ስለ የሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች ሕዝበ ውሳኔ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡ የሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ሕዝበ ውሳኔ
የቤጊ ወረዳ ሕዝበ ውሳኔ
የቤጊ ወረዳ ሕዝበ ውሳኔ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መካከል የቤጊ ወረዳ ይገባኛል ጥያቄ ለመወሰን ሰኔ 25 ቀን 1987 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተደረገ ሕዝበ ውሳኔ ነው፡፡ ስለቤጊ ወረዳ ሕዝበ ውሳኔ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡፡ የቤጊ ወረዳ ሕዝበ ውሳኔ