የምርጫ ህጉ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ካስቀመጣቸው ኃላፊነት ያለባቸው የምርጫ የባለድርሻ አካላት ዝርዝር አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ነው፡፡ ይህ ምክር ቤት የሚመሠረተው በምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ህጉ የተቀመጡ ድንጋጌዎችንና ሌሎች የጋራ ጉዳዮችን ተግባራዊ ለማድረግና በምርጫው ሂደት በሚነሱ ልዩ ልዩ የአፈፃፀም፣ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችንና የህግ የበላይነትን በኢትዮጵያ ለማጎልበት በሚያግዙ ጉዳዮች ላይ በመመካከር ችግሮችን እያቃለሉ ለመጓዝ ይችሉ ዘንድ ነው፡፡

ይህንንም ተፈፃሚ ለማድረግ መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. 116 የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱን የአሠራር ደንብ ለመወሰን የቃል ኪዳን ሰነድ ፈርመዋል፡፡ ይህ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአሠራር ደንብ የቃል ኪዳን ሰነድ በፈረሙት እና ወደፊት በሚፈርሙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን ነው፡፡ ምክር ቤቱ በአመራርነት ዶ/ር ሙሣ አደም ሊቀመንበር፣ አቶ ግርማ በቀለ ም/ሊቀመንበር እና ዶ/ር ፋሪስ ኢሳይያስ በፀሐፊነት ምክር ቤቱ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ መርጦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ 

ከስር የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የፓለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለማስፈጸም የወጣ የሥነ ሥርዓት ደንቡን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአሠራር ደንብ ይመልከቱ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የቃል ኪዳን ሰነድ ለማስፈጸም የወጣ የሥነ ሥርዓት ደንብ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአሠራር ደንብ