በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተግባራት ዙሪያ የሚነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎችና መልሶቻቸው


መልስ - የጊዜ ሰሌዳው ከመውጣቱ አስቀድሞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተከታታይ ምክክሮች ማድረጉ ይታወሳል፣ በዚህም መሰረት የተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች ሁለት ሲሆኑ አንደኛው ፓርቲዎች እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ አለብን የሚሉት ችግሮች ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው። ያንን መሰረት አድርጎ የጊዜ ሰሌዳ ከመውጣቱ አስቀድሞ ቦርዱ ሁለት ዋና ዋና ተግባራትን አከናውኗል። አንደኛው በመንግስት በኩል የምርጫ ጸጥታ እቅድ ዝግጅት እንዲኖር እና ቦርዱ ምርጫን የተመለከቱ እቅዱ ቴክኒካዊ መረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ያካተተ እንዲሆን በሂደቱ በመሳተፍ ማረጋገጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በየክልሉ ያሉ በፓርቲዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የሶስትዮሽ መድረክ ማዘጋጀት ነው፣ በዚህም መሰረት በየክልሎቹ ፓርቲዎች የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታት የሶስትዮሽ ውይይቶች መከናወን ጀምረዋል።እነዚህ ውይይቶች እስከአሁን ሶስት ክልሎች ላይ የተደረጉ ሲሆን በዚህ ውይይትም ገዥው ፓርቲ፣ በክልሎቹ የሚንቀሳሰቀሱ ፓርቲዎች እንዲሁም ቦርዱ ተገኝተው ዝርዝር አቤቱታዎች ላይ ውይይት በማድረግ መፍትሄዎች ላይ መስማማት ላይ እንዲደርሱ ጥረት እየተደረገ ነው። እነዚህ አሰራሮች ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ይረዳሉ ብሎ ቦርዱ ያምናል።

መልስ - ምርጫ አስፈጻሚዎች ለአንድ ምርጫ ክልል (constituency) ብቻ ደምረው ሪፓርት ያደርጋሉ፣ ይህም የውጤት ስህትት እንዳይፈጠር ያደርጋል፤ ድምፅ ሰጪዎች ያለምንም መምታታት ድምፅ መስጠት ይችላሉ፤ የምርጫ ታዛቢዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም የፓርቲ ወኪሎች አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች ላይ በመገኘት ሙሉ አቅማቸውን በመጠቀም (የአቅም መበታተን ሳይኖር) የምርጫን ሂደት መከታተል ተአማኒነቱንም ማረጋገጥ ይችላሉ።

መልስ - ለአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድሮች ምክር ቤቶች የድምፅ መስጫ ቀን ከአገር አቀፍ ምርጫ ጋር በተመሳሳይ አለመሆኑን ቦርዱ አሳውቋል፡፡ ይህም የሆነው ግንቦት 28 ቀን 2013 የሚካሄደው ምርጫ የፌዴራል መቀመጫ የሚመረጥበት የምርጫ ክልል (constituency) እና የአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተሞች መስተዳደር መቀመጫዎች የሚመረጡት የምርጫ ክልል (constituency) በመለያየቱ ነው፡፡ የከተማ መስተዳድሮች/ ክልሎች የምርጫ ክልሎቻቸው የሚወስኑት በራሳቸው ሲሆን ቦርዱ የክልል/የከተማ መስተዳድሮች ምርጫን የሚያስፈጽመው ክልሎች/ከተማ መስተዳድሮች በወሰኑት የምርጫ ክልል መሰረት ነው።  ለምሳሌ በምርጫ 97 የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር መቀመጫ የሚመረጥበት የምርጫ ክልል እና ከከተማው ለተወካዮች ምክርቤት ተወካዮች የሚመረጡበት የምርጫ ክልል ተመሳሳይ የነበረ ሲሆን ቆጠራውም በተመሳሳይ የሚቆጠር በመሆኑ ምርጫ አስፈጻሚዎች ውጤት ሲያሳውቁ ለተመሳሳይ የምርጫ ክልል ሪፓርት ያደርጉ ነበር፡፡ ነገር ግን ከምርጫ 97 በኋላ 2000 . በተካሄደው የከተማው መስተዳድር መቀመጫ ምርጫ የከተማ መስተዳድሩ የምርጫ ክልሎቹን በመቀየር ክፍለከተሞችን እንደምርጫ ክልል አዋቅሮ ምርጫዎቹም በዚያ መሰረት ሲከናወኑ ቆይተዋል። ከዚያ በኋላ የነበሩት ምርጫዎችም የከተማ መስተዳድሩ ምርጫ ከፌደራል ምርጫ ጊዜ በተለየ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል። የድሬደዋ ከተማ መስተዳድርም ከፌደራል መቀመጫ (2 ብቻ) በተለየ በመስተዳድሩ ስር ያሉትን 47 ቀበሌዎች እንደመስተዳድሩ የምርጫ ክልል ስለሚጠቀምባቸው አንድ ሰው ድምጽ ሲሰጥ ለፌዴራል መቀመጫ ድምጽ የሚሰጥበት እና ለመስተዳድሩ ድምጽ የሚሰጥበት የምርጫ ክልል ይለያያል። ይህም ውጤት ቆጠራን በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል። እንደሚታወሰውም የድሬደዋ ከተማ ምርጫም ከፌደራሉ በተለየ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።

መልስ - የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ከምርጫው ጋር መደረጉ የህዝበ ውሳኔውን ኦፕሬሽን በጣም ቀላል የሚያደርገው ሲሆን ከፍተኛ ወጪንም የሚቀንስ ይሆናል፡፡ ቦርዱ ለብሔራዊ ምርጫ እየተዘጋጀ ቀድሞ ህዝበ ውሳኔ ለማደራጀት በቂ ጊዜ የማይኖረው ሲሆን ከዚያም በተጨማሪ ህዝበ ውሳኔን ለብቻው ለማደራጀት የሚወጣው ከፍተኛ ወጪ እና ዝግጅት ከብሔራዊ ምርጫ ጋር በመደረጉ በግማሽ የሚቀንስ ይሆናል። ቦርዱም አስፈጻሚዎችን በሚያሰለጥንበት ወቅት ተጨማሪ የህዝበ ውሳኔ አስተዳደር ስልጠና በመስጠት፣ ተጨማሪ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ወረቀት በማተም በተመሳሳይ መራጮች ምዝገባ ሂደትን በመከተል ህዝበ ውሳኔውን ለማስፈጸም ቀላል ይሆንለታል።

መልስ - አንድ ሰው አንድ ቦታ በመራጭነት ለመመዝገብ በምርጫ ጣቢያው ነዋሪነቱን ተረጋግጦ ሲሆን መስፈርቱን አሟልቶ ለመመዝገቡ ደግሞ የመራጭነት መታወቂያ መያዝ አለበት። በአካባቢው ነዋሪ ያልሆነ መራጭ ተመዝግቧል የሚል ጥርጣሬ ካለ የመራጮች ምዝገባ መዝገብ በየምርጫ ጣቢያው 10 ቀን ክፍት የሚሆንበት እና ቅሬታ የሚቀርብበት ስርአት አለ፣ ፓርቲዎች፣ ታዛቢዎች እና ሲቪል ማህበራት ሂደቱን መታዘብ እና ቅሬታን ማቅረብ ይችላሉ። በተጨማሪም የመራጮች ዝርዝር ወደ ዳታ ቤዝ የሚገባ በመሆኑ የተደጋጋሚ የመራጭነት ምዝገባን በቴክኖሎጂ ለመለየት የሚቻልበት አሰራርም በቦርዱ በኩል ተዘርግቷል። በመሆኑም የድምጽ መስጫ ቀኖቹ መለያየት የምርጫውን የጥራት ደረጃ የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ አይሆንም።

መልስ - ድምጽ ሰጪዎች ድምጽ የሚሰጡበት የምርጫ ክልሎች የተለያዩ በመሆናቸው በድምጽ አሰጣጥ ወቅት መምታታትን ያስከትላል፤ ምርጫ አስፈጻሚዎች ውጤት ቆጥረው ወደሚመለከተው የምርጫ ክልል የሚልኩ ሲሆን በአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ግን ለሁለት እና ለሶስት ምርጫ ክልሎች ውጤትን አከፋፍለው እንዲልኩ ይገደዳሉ ይህም በውጤቱ ድመራ ላይ መምታታት ሊያመጣ ይችላል፣ የምርጫውን አፈጻጸምም አስቸጋሪ ያደርገዋል፤ ምርጫ አስፈጻሚዎች ለተለያዩ የምርጫ ክልሎች ውጤትን በታትነው እንዲልኩ የተለየ የቆጠራ እና የውጤት ሪፓርት አደራረግ ስልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል ይህም ተጨማሪ የኦፕሬሽን ጫና ከመሆኑም በላይ ለዚህ የተለየ ህትመቶችን የማዘጋጀት ተጨማሪ ጫና ያስከትላል። 

መልስ - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች እጩ ለማስመዝገብ ያላቸውን አጭር ጊዜ በመረዳት፣ እንዲሁም በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ ሊኖር የሚችለውን ንክኪ ለመቀነስ ያቀረቡትንም አቤቱታ መሰረት በማድረግ እጩዎች ለማቅረብ የሚጠበቅባቸውን ፊርማ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ብቻ እንዲታገድ ለተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄውን አቅርቧል። አንዳንድ ጠያቂዎች ለፓርቲዎች መስራች ፊርማ የኮቪድ ወረርሽኝን ቦርዱ ለምን ከግምት ውስጥ እንዳላስገባ ሲጠይቁ የነበረ ቢሆንም የመስራች ፊርማ ማሰባሰብ ጊዜ ገደብ የተጠናቀቀው ወረርሽኙ አገራችን ከመግባቱ በፊት በመሆኑ የፓርቲዎች መስራች ፊርማ ማሰባሰብ እና ኮቪድ ወረርሽኝ ግንኙነት እንዳልነበራቸው ማስታወስ ያስፈልጋል።

መልስ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ሰራተኞቹ ከቤት ሆነው የቀረው ደግሞ በፈረቃ ስራውን በማከናውን ላይ ሲሆን መሰብሰብ የማያስፈልጋቸው ስራዎቹን ማህበራዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩ፣ሁኔታው ተቀይሮ ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ ሲመለስ በተገቢው ሁኔታ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያሥችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ ይቆያል፡፡ በዚህም መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎቸን ዲጂታል ኮምኒኬሽን መረጃ እየሰበሰበ ይገኛል፡፡ ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረው ግንኙነትም በተቻለ መጠን በዲጂታል መንገድ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡ 

መልስ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ተጠሪነቱ ለተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡ የአፈጻጸም ሪፓርቶችን የሚያቀርበውም ለምክር ቤቱ ነው በመሆኑም ውሳኔውን ለተወካዮች ምክር ቤት ከማሳወቅ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ ቦርዱ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት ችግሩን ለተወካዮች ምክር ቤት ከማቅረብ እና በጥናት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ከማድረግ ውጨ ከስልጣኑ ውጪ የሰራው ወይም ስልጣኑ ኖሮት ሳይወጣ የቀረው ሃላፊነት የለም፡፡

መልስ - ቦርዱ የኮቪድ19 በምርጫ ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡ ያደረገው ምክክር በሁለት ዙር ሲሆን በእለቱም ፓለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ የሰጧቸው አስተያየቶችም ችግሩን አለም አቀፍነት በተለይ ደሞ እንደኢትዮጵያ ላለ አገር ሊያስክተል የሚችለውን ቀውስ እና በምርጫ ስራ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ እንደሚረዱ ገልጸዋል፤ ምርጫ ቦርዱ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመመካከር እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ ምክክሩን ማድረጉን አድንቀው መንግስት ያስቀመጠው የ14 ቀን ክልከላ ታይቶ ቢወሰን የሚል አማራጭም አቅርበዋል፡፡ ውይይቱ በመግባባት የተጠናቀቀ ሲሆን የፓርቲ አመራሮች ይህንን እድል የአገራችንን ፓለቲካ ለማስተካከልም ሆነ በቂ ዝግጅት ለማድረግ መጠቀም እንደሚገባ፣ ይህ ውሳኔ በቦርዱ መወሰን እንዳለበት እና ፓርቲዎችን ማማከር ጥሩ ቢሆንም ውሳኔው ከፓርቲዎች በላይ መሆኑን እና በአገር የመጣ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ለመቋቋምም ሁሉም ፓርቲዎች ተባብረው መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡ ቦርዱ የተለያዩ ተጨማሪ ምክክሮችን ለማድረግ ያሰበ ቢሆንም
- የመጀመሪያው ውይይት የተካሄደው የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በተገኘ 3ተኛው ቀን በመሆኑ ከዚያ በኋላ ያሉ ክልከላዎች መጠናከራቸው እና የተለያዩ እርምጃዎች በክልሎችም ጭምር በመወሰዳቸው ክልከላዎችን መጣስ ስለማይቻል፣ እንዲሁም ኮቪድ19 የደቀነው አደጋ በጣም ግልጽ መሆኑን ፓርቲዎችም እንደሚረዱ በማመኑ 
- ከፓርቲዎች የተገኘው ግብአት በቂ በመሆኑ እና ቦርዱም ለውሳኔው እንደግብአት ስለተጠቀመበት ቦርዱ በመግለጫው እንዳሳወቀው ውሳኔውን በሚወስንበት ወቅት የፓርቲዎችን አስተያየት እንደግብአት ከተጠቀመባቸው መረጃዎች አንዱ ነው፡፡ 

መልስ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ዋና አላማ ምርጫውን ቀድሞ ባቀደው ቀን ማለትም ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ማከናወን እንደማይችል ማሳወቅ ሲሆን፣ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጥናት አካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጠሪነቱ ለተወካዮች ምክር ቤት ስለሆነ ውሳኔውንም ለተወካዮች ምክር ቤት አሳውቋል፡፡ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ምርጫውን ማከናወን ካለመቻሉ በስተቀር የተራዘመ ቀን ቆርጦ አላቀረበም፡፡ ቦርዱ ማድረግ የሚችለው አለመቻሉን ብቻ ገልጾ ሪፓርት ለሚያደርግለት ለተወካዮች ምክር ቤት ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ 
በመግለጫው ተገለጹት የቦርዱ ዋና ዋና ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 
• በኮቪድ19 የተነሳ ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ የማይቻለው መሆኑን በመረዳት ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ ፤
• ቦርዱ የወረርሽኙ ሥጋት ተወግዶ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደገና ግምገማ በማድረግ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን እቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቀሴውን እንደሚያስጀምር፤
• በኮቪድ 19 የማይስተጓጎሉ፣ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩ፣ሁኔታው ተቀይሮ ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ ሲመለስ በተገቢው ሁኔታ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያሥችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ መቆየት እንዳለበት፤ 
• በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት በስራ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስልጣን ጊዜው ከሚያበቃበት አንድ ወር አስቀድሞ ቦርዱ አጠቃላይ ምርጫውን ማድረግ የማይችል መሆኑን ም/ቤቱ ተገንዝቦ፣ ከዚህ አንጻር የሚሰጠው ውሳኔ ቢኖር ለመነሻነት ያገለግለው ዘንድ ይህ ውሳኔ እንዲሁም ቦርዱ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ለህዝብ ተወካዮች እንዲተላለፍለት

መልስ - የፓለቲካ ፓርቲዎች በሶስት አመት አንድ ጊዜ ከአባላት ጋር በመገናኘት ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ አሰራራቸውን የሚያረጋግጡበት መንገድ ነው፡፡ ሶስት አመት ለጠቅላላ ጉባኤ አጠረ የሚባል አይደለም፡፡ አንድ ፓርቲ ከሶስት አመት በላይ ጠቅላላ ጉባኤ ሳያደርግ ከቆየ ውስጠ ፓርቲ አሰራሩ ላይ ያሉ ችግሮችንም በፍጥነት የመፍታት እድሉ ይጠባል፡፡ የአዋጁ አላማ ፓርቲዎችን አሰራር ማጠናከር፣ ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲያቸውን ማበረታታት እና መቆጣጠር እንደመሆኑ መጠን ይህ አነስተኛ መስፈርት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

መልስ - ቀድመው የተመዘገቡ የፓለቲካ ፓርቲዎችን አስመልክቶ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ከተቀመጠው መስፈርት ጋር የሚጣጣሙበትን መንገድ አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ መመሪያ እንዲያወጣ ህጉ ያስገድዳል፡፡ በመሆኑም ተመዝግበው የሚገኙ ፓርቲዎች በሂደት መስፈርቱን የሚያሟሉበትን ዝርዝሩን ከቦርዱ ከፓርቲዎች ጋር በመመካከር በሚያወጣው መመሪያ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡