የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግሥቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ስድስት (6)የጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፤ አራት (4) የአካባቢ ምርጫ፣ እና ስምንት (8) ሕዝበ ውሳኔዎችን አካሂዷል። እንዲሁም የተለያዩ የሟሟያ እና ድጋሚ ምርጫዎችን በተለያዩ ዓመታት አከናውኗል፡: በአጠቃላይ አስራ አራት (18) ምርጫዎችን አስፈጽሟል፡፡ እስካሁን በተከናወኑት ስድስት ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫዎች ለአምስት መቶ አርባ ሰባት (547) የፌዴራል መቀመጫዎች እና ለስድስት መቶ ሃምሳ አራት (654) የክልል መቀመጫዎች እጩዎች ቀርበዋል፡፡ የሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫዎች የተጠቃለለ መረጃ ከስር ይገኛል፡፡