የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቀጣዮ አገር አቀፍ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሰነዶች ህትመትና የቁሳቁሶች ግዥ ጀመረ
ታኅሣሥ 9 ቀን 2012 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ከሚያደርጋቸው ዝግጅቶች መካከል አንዱ የሆነውን የመራጮች ምዝገባን ዘመናዊ እና ተአማኒ የሚያደርግ የህትመት ሥራ እንዲጀመር በትላንትናው ዕለት በዱባይ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የዚህ የህትመት ውል ዓላማ የምርጫው ሂደት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ እና አዲሱ የምርጫ ህግ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ እንዲሆን፣ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ለመቀነስና እና ማጭበርበርን ለማስወገድ የሚረዳ እንዲሆን እንዲሁም ለምርጫ አስፈጻሚዎች ለመረዳትና ለማስፈጸም ቀላል እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡