Skip to main content

የምርጫ ቀን በምስል

ዜጎች በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ድምጽ እየሰጡ ሲሆን ከምርጫ ጣቢያዎች የተወሰኑት ይህንን ይመስላሉ

Share this post

ስለ ድምፅ መስጫ ቀን በጥቂቱ

በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው?

  • ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ዙሪያ መለስ ርቀት ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ወይም በሌላ በማናቸውም ፀጥታን በሚያደፈርስ ሁኔታ ውስጥ መገኘት የለበትም
  • መራጭ ያልሆኑና ድምፅ የሰጡ ሰዎች በምርጫ ጣቢያው ውስጥ መገኘት የለባቸውም
  • ማንኛውም ሰው ያለፈቃድ ወደምርጫ ጣቢያው በመግባት ወይም በምርጫ ጣቢያው ግቢ ውስጥም ሆነ ውጭ የምርጫውን እንቅስቃሴ ማወክ ወይም ማደናቀፍ ወይም
  • ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴ ማድረግ የለበትም

ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው?

ድምፅ ለመስጠት ብቁ የሆኑ እነማን ናቸው?

1. ድምፅ ለመስጠት በተመዘገበችበት የምርጫ ጣቢያ የተገኘች መራጭ፡-

ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ያላት፣

ለ) የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተረጋገጠበት ሌላ ሰነድ ያላት፣ወይም ማንነትዋ በምርጫ ምዝገባ ወቅት በምስክሮች ስለመረጋገጡ

በመራጮች መዝገብ ላይ የሰፈረላት፣

ሐ) የመራጮች መዝገብ ላይ ስሟ የሰፈረ፣

መ) ድምፅ ያልሰጠች መሆኑ ሲረጋገጥ ድምጿን የመስጠት መብት አላት

2. የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ የጠፋባት መራጭ ጉዳዩን ለምርጫ ጣቢያው በማስረዳት ማንነቷ እንዲሁም በመዝገቡ ላይ ስሟ የሰፈረና ያልመረጠች መሆኑ ሲረጋገጥ ጉዳዩ በቃለ ጉባኤ ተይዞ እንድትመርጥ ይደረጋል፡፡

ድጋፍ ስለሚፈልጉና ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው መራጮች

1. የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ነፍሰጡሮችን፣ ጨቅላ ህጻናት የያዙ ወላጆችን፣ መለዮ የለበሱ የመከላከያና የፖሊስ አባላትን ቅድሚያ በመስጠት ድምፅ እንዲሰጡ ማድረግ አለበት

2. በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ምልክት ለማድረግና የድምፅ መስጫ ወረቀቱን ወደሳጥን ለመክተት እገዛ የሚያስፈልገው መራጭ ራሱ የመረጠውን ሰው ይዞ የመምጣት መብት አለው

3. በዚህም መሰረት በድጋፍ ፈላጊው የሚመረጥ ሰው :-

ሀ) ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት

ለ) እጩ ተወዳዳሪ ወይም የእጩ ወኪል መሆን የለበትም

4. አንድ ድጋፍ የሚሰጥ ሰው ከአንድ በላይ መራጭ ለመደገፍ አይችልም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የፃፈዉ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ደብዳቤ በተገለጸው መሰረት ለሁሉም ደብዳቤ ለደረሳቸው ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች እስከ ነገ ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም እኩለ ቀን ድረስ ይህንን ማዘጋጀታቸውን በጽሁፍ እንዲያረጋግጡ እና በደብዳቤ፣ በኢሜይል፣ ወይም በማንኛውም ኤሌክትሮኒክ መንገድ እንዲያሳውቁ ለማሳሰብ ይወዳል።

ለአዲስ አበባ ከተማ

ለአፋር ክልል

አንድ መራጭ ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ ምን ያህል እጩዎችን መምረጥ ይችላል?

ለክልል ወይም ለከተማ ም/ቤት መቀመጫ አንድ መራጭ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት እንደየምርጫ ክልሉ ይለያያል ። አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 1 እጩ፣ እንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 3 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ላይ 9 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 14 እጩዎች ወይም ሌላ ቁጥር ያለው የመቀመጫ ብዛት ሊኖራቸው ይችላል።

ብዛቱ የሚወሰነው የምርጫ ክልሉ በክልል ም/ቤቱ ባለው የመቀመጫ ቁጥር ብዛት ነው ። በመሆኑም አንድ መራጭ በክልል ም/ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ መምረጥ የሚችለው የዕጩዎች ብዛት በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ከላይ ተፅፎ ይገኛል። በዚህም መሰረት አስፈጻሚዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጡ ለመራጩ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ እስከ ስንት እጩ መምረጥ እንደሚችል ያስረዳሉ።

ለምርጫ ክልል ምርጫ አስፈጻሚዎች በሙሉ

ሰኞ ሰኔ 14 ቀን ለሚከናውነው አጠቃላይ ምርጫ የፓርቲ ወኪሎችን እውቅና ባጅ የመስጠት ስራ እያከናወናችሁ እንደሆነ ይታወቃል። ካለው አጭር ጊዜ አንጻር የእጩ ወኪሎች ባጅ መስጠትን እስከ ነገ ማታ ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንድታከናውኑ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኦፕሬሽንስ የስራ ክፍል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እለታዊ መረጃዎችን ይሰጣል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እለታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ ከቀኑ 10:30 በስካይ ላይት ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
  • የቦርዱን ልዩ የዘገባ ባጅ ፊት ለፊት ማንጠልጠል
  • ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች (የፎቶ/የቪዲዮ ባለሙያን ጨምሮ) ብቻ መሣተፍ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. እለታዊ መረጃዎችን ይሰጣል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. እለታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ ከቀኑ 10:30 በስካይ ላይት ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

•በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣

•የቦርዱን ልዩ የዘገባ ባጅ ፊት ለፊት ማንጠልጠል

•ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች (የፎቶ/የቪዲዮ ባለሙያን ጨምሮ) ብቻ መሣተፍ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ