Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post

የአሜሪካ የልማት ተራድዎ ድርጅት (USAID) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለግሷል፡፡

የአሜሪካ የልማት ተራድዎ ድርጅት (USAID) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ 2,626,780,00 ብር ዋጋ ተመን ያላቸው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለግሷል፡፡ ቁሳቁሶቹም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ የእጅ ጓንት፣ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እና የሙቀት መለኪያ ናቸው፡፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአሜሪካን የልማት ተራድኦ ድርጅት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ 

 

 

Share this post

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲፈጸምለት ለቦርዱ ያቀረበውን ጥያቄ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

 ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም 

የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ኮቪድ 19ኝን እየተከላከለ 6ኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የወሰነ በመሆኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ምርጫውን እንዲያስፈፅም፣ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ውሳኔውን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቀን” ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡ በመላ አገሪቱ በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የሚደረጉ ምርጫዎችን የማስፈፀም ስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 102 (1) ላይ ተደንግጓል ፡፡ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የቦርዱን ስልጣን እና ሀላፊነት የወሰነው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 በአንቀጽ 7.1 ይህ የቦርዱ ስልጣን በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ምርጫዎች እና ህዝበ ውሳኔዎችን በሙሉ እንደሚሸፍን በተብራራ ሁኔታ ገልጾታል።

Share this post

የድምጽ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ነው

ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሃሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊያከናውነው አቅዶ ለነበረው አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ለድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ግዥን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቀድመው ወደመጋዘን ከገቡት የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ይገኛል፡፡ ለድምጽ መስጫ ቀን የተገዙ ቁሳቁሶች 

1. ከግልጽ የሆነ ድምጽ መስጫ ሳጥን - 213,622
2. የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያ - 156,600 
3. የድምጽ መስጫ ቀን የአስፈጻሚዎች ቁሳቁስ- 58,400 
4. ልዩ የምርጫ ቁሳቁሶች ማሸጊያ ፕላስቲክ ( plastic seal)  እና የእሸጋ ስራ ስቲከሮች - 798,300 

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ንብረት እንዲያጣሩ ሁለት ኦዲተሮችን ሾመ

ሰኔ 6 ቀን 2012 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ኢሕአዴግ እንዲፈርስ እንዲሁም የቀድሞ ሶስቱ የግንባሩ አባላት ወራሽ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሐት) በስድስት ወር ውስጥ የንብረት ክፍፍል ተጠናቆ እንዲያቀርቡ ክፍፍሉም የሶስት ፓርቲዎች ወራሽ የሆነው ብልፅግና የሃብቱን ሶስት አራተኛ (3/4) በራሱ ህጋዊ እውቅና ያለው ህወሃት አንድ አራተኛ ( ¼) እንዲወስዱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በውሳኔውም ፓርቲዎቹ የጋራ ንብረት አጣሪ ሾመው የባለመብቶችን (creditors) መብት እንዲጠበቅ እንዲሁም በተገለጸው ቀመር መሰረትም የንብረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ወስኖ አሳውቆ ነበር፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ ያቀረበው ጥናት

ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ለህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ ያቀረበው ጥናት ከስር ማግኘት ይቻላል፡፡

ጥናቱ ቦርዱ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች፣ አሁን እየሰራቸው ያሉ ስራዎች እና ለወደፊቱ ለማድረግ የሚችላቸውን አማራጮች ያቀረበበት ሲሆን እነዚህ ጥናቱ ላይ የተጠቀሱ ሁኔታዎች ወደፊት በሚያጋጥሙ አዳዲስ ሁኔታዎች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት በሚገኙ ግብአቶች ሊቀየሩ የሚችሉ ናቸው፡፡

ከጥናቱ ጋር ተያይዞም ከድሮው የጊዜ ሰሌዳ አንጻር አዳዲስ ጊዜ ሰሌዳ አማራጭችም የቀረቡ ሲሆን ይህም ለጉባኤው ውሳኔ እንዲሁም በአጠቃላይ የምርጫ ኦፕሬሽንን ለመረዳት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሀያ ሰባት (27) ፓርቲዎችን ሰረዘ

ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና በቀድሞው ህግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ መቶ ስድስት (106) ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ከቦርዱ ደብዳቤ ከደረሳቸው መቶ ስድስት (106) የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሰባ (76) የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ ይገኛል፡፡ 

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 27 ፓርቲዎችን ሰረዘ

ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና በቀድሞው ህግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ 106 ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ከቦርዱ ደብዳቤ ከደረሳቸው 106 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 76 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ ይገኛል፡፡