የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ - ለድምፅዎ የሚያምኑን https://nebe.org.et/am am የስራ ማስታወቂያ የቢሮ ኃላፊ https://nebe.org.et/am/node/194  የስራ ማስታወቂያ የቢሮ ኃላፊ admin ቲዩ, 09/17/2019 - 15:09

መግቢያ፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ ምርጫን እንዲያስፈጽም እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድር ሥልጣን የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ ይህን ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ ተቋሙን በአዲስ መልክ በሚወጡ ሕጎች መሠረት እንደገና ማደራጀት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑ ታምኗል፡፡ ተቋሙን በአዲስ መልክ የማደራጀት ዋናው ዓላማ የተቋሙን ተዓማኒነት እና ብቃት ከፍ ማድረግ እንዲሁም ነፃ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ የሆነ ምርጫ ማካሄድ እንዲቻል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1133/2011 አምስት የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ የሆኑ የቦርድ አመራሮች እንዲኖሩት የተደረገ ሲሆን፤ በተጨማሪም አዲሱ ሕግ ቦርዱ በአንድ ዋና ኃላፊና በአንድ ምክትል ዋና ኃላፊ የሚመራ ጽ/ቤት እንደሚኖረውም ደንግጓል ፡፡
በመሆኑም የምርጫ ቦርድ ለዚህ ኃላፊነት ብቃትና ሙያው ያለው ሰው በሙሉ ጊዜ የሥራ መመደብ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
የስራ መደቡ መጠሪያ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቢሮ ኃላፊ
ተጠሪነቱ፡- የጽ/ቤት ኃላፊው/ኃላፊዋ ተጠሪነቱ /ተጠሪነቷ ለቦርዱ ሊቀመንበር ነው፡፡
ዋና ዋና ተግባሮች፡-
•የቦርዱን የድጋፍ ሰጭ የሥራ ዘርፍ (ፋይናንስ፣ ግዥ፣ ሰውሃይል አስተዳደር፣ ንብረት አስተዳደር) በኃላፊነት ይመራል/ትመራለች፤
•የቦርዱን የድጋፍ ሰጭ ተግባራት አፈጻጸም ውጤታማ የሚያደርግ ስትራቴጂያዊ እቅድ ያወጣል/ታወጣለች፣
•የቦርዱን የድጋፍ ሰጪ የስራ ዘርፍ አመታዊ እቅድ ያወጣል/ታወጣለች፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል/ትከታተላለች፤
•የድጋፍ ሰጪ ዘርፉ ሥራ አፈጻጸም ዋና ዋና ተግባራት ከቦርዱ ዋና ዋና የስራ ሃላፊነት ጋር በተቀናጀ መልኩ መከናወናቸውን ያረጋግጣል/ታረጋግጣለች፤
•ከቦርዱ ሰብሳቢ ጋር በመመካከር የቦርዱን የስብሰባ አጀንዳ ያዘጋጃል/ታዘጋጃለች፤
•የቦርዱን ቃለጉባዔና ሌሎች ሰነዶች በአግባቡ ይይዛል/ትይዛለች፤
•የቦርዱን ውሣኔዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች እንዲተላለፉ ያደርጋል/ታደርጋለች፤
•ቦርዱ ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ያስተባብራል/ታስተባብራለች፤
•ስለ ጽሕፈት ቤቱ የሥራ እንቅስቃሴ በየጊዜው የሥራ አፈጻጸምን እና በጀትን ሪፖርት አዘጋጅቶ/አዘጋጅታ ለቦርዱ ሰብሳቢ ያቀርባል/ታቀርባለች፤
•በቦርዱ ስብሳቢ የሚሰጡ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል/ታከናውናለች፡፡
የሚጠበቅ አጠቃላይ ብቃት ፡-
•ቦርዱ የሚመራባቸውን በነፃነት፣ በገለልተኝነት እና በፍትሐዊነት የመሥራት መርህዎች የሚያከብር/የምታከብር፤
•የዴሞክራሲ ተቋማት የአሠራር ሥርዓትና መርሆዎችን የሚያውቅ/የምታውቅ፤
•የብዝሃነት እና የአካታችነት መርሆዎችን የመተግበር ዝግጁነት ያለው/ያላት ፤
•የፌደራል የስራ ቋንቋ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጻፍና እና የመናገር ችሎታ ያለው/ያላት ተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ቋንቋ የሚያውቅ/የምታውቅ ቢሆን/ብትሆን ይመረጣል፤
•በሥራ አመራር፣ በሰው ሃብት አስተዳደር፣ በፋይናንስና የግዢ ሥርዓት እና ደንብ ላይ በቂ እውቀትና ልምድ ያለው/ያላት፤
•የመንግሥት ተቋማትን የአሠራር ሥርዓት እና ትብብር የሚያውቅ/የምታውቅ ሂደቱንም ለማመቻቸት ዝግጁነት ያለው/ያላት፤
•ሃሳብን የመግለጽ ችሎታ፣ ከሰዎች ጋር ተባብሮ የመሥራት አቅም፤ አስቻይ የሥራ ግንኙነት እና አጋር የመፍጠር ክህሎት ያለው/ያላት
•መሰረታዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የኮምፒውተር አጠቃቀም ክህሎት ያለው/ያላት
•ከሥራ ኃላፊነቱ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ቦርዱን የመወከልና የመደራደር በጣም ጥሩ የሆነ ችሎታ ያለው/ያላት፣
•መረጃ እና ትንታኔን መሠረት ያደረገ ውሣኔ የማስተላለፍ ችሎታ ያለው/ያላት፣
•በቦርዱ የስነ ምግባር መመሪያ ለመገዛት ዝግጁነት ያለው/ያላት
•አዳዲስ ሃሳቦችን የማስተናገድና ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን የመምራት ችሎታ ያለው/ያላት፣
•በሥራ ብዛት የሚኖርን ጫና ወይም ተጽዕኖ የመቋቋምና ሥራ በተሰጠ የጊዜ ገደብ ውስጥ ባልተመቻቹ ሁኔታዎች ሁሉ የመጨረስ ችሎታ ያለው/ያላት፣
•እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የማደራጀት እውቀትና ልምድ እንዲሁም በቡድን ወይም /በጋራ/ በአስተማማኝ ሁኔታ ሥራ ሠርቶ ማድረስ የሚችል/ የምትችል፣
•በሥራ አመራር፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር፣ በሎጅስቲክስ እና ሌሎች አግባብነት ባላቸው ተያያዥ ዘርፎች የማስተርስ ዲግሪ እና ቢያንስ የ12 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፣
•በመንግሥት ተቋማት፣ በሲቪል ማኀበራት ወይም በዓለም አቀፍ ተቋማት የሠራ/የሠራች ቢሆን/ብትሆን ይመረጣል
•በፋይናንስ፣ በሰው ኃይልና አስተዳደር እንዲሁም በሎጅስቲክስ ጠንካራ ቴክኒካል እውቀት ያለው/ያላት፤
•የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፤
•መልካም ሥነምግባር ያለው/ያላት፤
•ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁነት ያለው/ያላት፤
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾች ከስር የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በኢሜል አድራሻ - electionsethiopia [at] gmail.com መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
አስፈላጊ ማስረጃዎች
•የትምህርት ማስረጃ፤
•የሥራ ልምድ፤
•አመልካቹ/አመልካቿ ለሥራው ተገቢነትና የሚያመለክትበትን ፍላጐት የሚገልጽ ከአንድ ገጽ ያልበለጠ መግለጫ እና ካሪኩለም ቪቴ (CV)፣
•ስለ ሥራ አፈጻጸማቸውና ስለ ሥነምግባራቸው የሚገልፁ (REFERNCE) የሁለት ሰዎች ስምና የስልክ አድራሻ፤
ደመወዝ፡- በስምምነት
የቅጥር ሁኔታ፡- በኮንትራት
ውድድር ውስጥ ለመግባት ማመልቻ ዶክመንቶች ሁሉ በአንድ ኢሜይል ተጠናቀው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

The English version of the post requirement can be found on the following link.
http://www.ethiojobs.net/…/NEBE-Chief-Operations-Officer--S…

የስራ ማስታወቂያ

መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም.
Tue, 17 Sep 2019 12:09:53 +0000 admin 194 at https://nebe.org.et የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርተፍኬት መስጠት ጀመረ https://nebe.org.et/am/node/745 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርተፍኬት መስጠት ጀመረ admin ቲዩ, 06/07/2022 - 18:28

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ ሠራተኞች፤ ማለትም የዞን አስተባባሪዎች፣ ምክትል የዞን አስተባባሪዎች፣ የምርጫ ክልል ኃላፊዎች፣ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዳታ ኢንኮደሮችና የአይ.ሲ.ቲ ባለሞያዎች ለነበራቸው ተሣትፎ ቦርዱ እያመሰገነ፤ በምርጫው ላይ የነበራቸውን ተሣትፎ የሚያረጋግጠውን የምስክር ወረቀት በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ፖርታል አዘጋጅቶ አቅርቧል። የምስክር ወረቀቱ የሚመለከታቸው ሠራተኞችም የምስክር ወረቀት ፖርታሉ ላይ የሚጠየቁትን መረጃዎች በማስገባት የምስክር ወረቀታቸውን መውስድ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት እንዲሁም ሰርተፍኬትዎ እንዲደርስዎ እዚህ ላይ ይጫኑ

Blog Display

Thumbnail

Tue, 07 Jun 2022 15:28:55 +0000 admin 745 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/745#comments የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ዙሪያ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሔደ https://nebe.org.et/am/node/742 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ዙሪያ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሔደ  admin Fri, 06/03/2022 - 14:49

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ዙሪያ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ምክክር አካሄደ፡፡ በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ንግግር የተከፈተው የምክክር መድረኩ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ተቋማት የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ተሣትፎ ምርጫ በሚደረግባቸው ዓመታት ላይ ብቻ ተወሥኖ እንዳይቀር ግንዛቤ እንዲወሰዱ ለማድረግና በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ላይ የቦርዱ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ግንዛቤ መፍጠር ዐላማው ያደረገ ሲሆን፤ መድረኩ ላይ ከቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ በተጨማሪ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት አበራ ደገፋን (ዶ/ር) ጨምሮ የቦርዱ የጽ/ቤት ኃላፊዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ተገኝተውበታል። ከባለድርሻ አካላትም ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችና የዘርፉ ባለሞያዎች፤ እንዲሁም የብዙኃን መገናኛ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

ምክትል ሰብሳቢው በመክፈቻ ንግግራቸው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች በመምረጥ ተሣትፈው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቦርዱ ባደረጋቸው ጥረቶች ላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የመገናኛ ብዙኃኑ አስተዋጽዖ ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህ አስተዋጽዖ በምርጫ ወቅት ብቻ ሳይወሠን ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም የትምህርት ተቋማት በመራጮች እና በሥነ ዜጋ ትምህርት አሰጣጥ የቦርዱ አንደኛው አጋር መሆናቸው በዐዋጅ መደንገጉን ጠቅሰው፤ የትምህርት ዘርፍ ዋነኛ ባለቤት የሆኑት ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ከቦርዱ ጋር አብረው የሚሠሩበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹም ጠይቀዋል።

ምክትል ሰብሳቢውን ተከትሎ የተናገሩት የቦርድ አመራር የሆኑት አበራ ደገፋ (ዶ/ር) የመራጮች ትምህርት በምርጫ ወቅት ብቻ ሊወሠን እንደማይገባ በድጋሚ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። በመድረኩ ላይ የሕግ ባለሞያው ደበበ ኃይለገብርኤል በሥነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ሚና በተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቦርዱ የሥነ ዜጋና መራጮች ትምህርት ክፍል አማካኝነት በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ተቋማት የሥነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ተሣትፎ ምን ይመስል እንደነበር ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሥነ ዜጋ ትምህርትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በአፈጻጸም ደረጃ ከማን ምን ይጠበቃል በሚለው ላይ ደግሞ ሽመልስ ሲሳይ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት መለኪያውን ምርጫ ቦርድ ቢያወጣውም የዲሞክራሲ ተቋማት ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖራቸው፤ በደንብ የተደራጁ ሲሆኑ ደግሞ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ታች ወርዶ ማኅበረቡን በማወቅና በማንቀሳቀስ ረገድ ትልቅ ዐቅም አላቸው ብለዋል። ብዙኃን መገናኛ አካላቱም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ከቻሉ በአንድ ጊዜ ብዙ አካላትን በመድረስ ሥነ ዜጋን በማስተማር የሚኖራቸውን ትልቅ አበርክቶንም እንዲሁ አስረድተዋል። የዓለም ዐቀፍ ተሞክሮዎችንም ሲያብራሩም መገናኛ ብዙኃኑ ላይ የሥነ ዜጋ ትምህርት ለሚሠሩ አካላት የዓየር ሰዓት መስጠት በሕግ ግዴታ የሚጥሉ ሀገራት እንዳሉ ጠቅሰው፤ ፓለቲከኞችም የተለያዩ አጀንዳዎቻቸው እንዳሉ ሆነው ዜጎች መሠረታዊ መብቶቻቸውን እንዲያውቁ ከማድረግ አንጻር ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በካሪኩለሙ ላይ ከተቀመጠው አልፈው በስፋት ሊሠሩበት እንደሚገባ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ባለሞያዎቹ፤ ባለድርሻ አካላቱ እነማን ናቸው የሚለው በደንብ ተለይቶ ዕቅድ በማውጣት ትምህርቱን ምርጫ ከመድርሱ በፊት ገንዘብና ጊዜን ባገናዘበ ሁኔታ በምን ያህል ጊዜ ምን ያህል ዜጎችን መድረስ እንችላለን የሚለውን በመለየት መሥራት እነደሚገባ ያስረዱ ሲሆን፤ በየጊዜውም የክትትልና ግምገማ ሥርዓት በማበጀት ውጤቱን መመዘን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሣታፊዎች በበኩላቸው ቦርዱ በምርጫ ወቅት ሳይወሠን የሥነ ዜጋ እና የመራጮችን ትምህርትን የተመለከተ መድረክ ማዘጋጀቱን በበጎ በማንሣት፤ በቀጣይ ቢስተካከሉ ያሏቸውን ጉዳዮች እንዲሁም ቦርዱና መንግሥት ቢያደርጓቸው ያሏቸውን ድጋፎች ዘርዝረዋል፡፡ የሥነ ዜጋ ትምህርት፤ በተለይም ለመራጮች ትምህርት የሚሰጠው ጊዜ በጣም ያነሰ እንደሆነና እንዲጨመር፣ ለዘርፉ የሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፉም በቂ ባለመሆኑ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሆነባቸው፣ በመንግሥትም የሚሰጣቸው ትኩረት የሚያበረታታ መሆን እንደሚገባውና የሥነ ዜጋ ትምህርት ተቋማዊ ሆኖ ባልተቋረጠ ሁኔታ መሰጠት እንዳለበት ከተሣታፊዎች ከተሰጡ አስተያየቶች ይጠቀሳሉ።

ለተሣታፊዎች አስተያየት ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች፤ ቦርዱ ዐቅሙ በፈቀደው መጠን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመው፤ ለሚፈለገው መሻሻልና ለውጥ ተቋማቱ የሚያደርጉት ጥረት ወሣኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Image

Blog Display

Gallery

Fri, 03 Jun 2022 11:49:30 +0000 admin 742 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/742#comments የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት የመንግሥት ድጋፍ አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ https://nebe.org.et/am/node/734 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት የመንግሥት ድጋፍ አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ admin ቲዩ, 05/17/2022 - 18:18

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 100 ንዑስ አንቀጽ ሁለት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለመወሠን መመሪያ አጽድቆ በሥራ ላይ በማዋል በ2013 በጀት ዓመት በመመሪያው መሠረት በማከፋፈል የፓርቲዎቹን ድርሻ ፓርቲዎቹ በከፈቱት የተለየ የባንክ ሒሣብ ቁጥር ገቢ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት ፓርቲዎቹ በባንክ ሒሣብ ቁጥራቸው ገቢ የሆነውን የፋይናንስ ድጋፍ በመመሪያው አንቀጽ 10 መሠረት በአግባቡና ለታለመለት ተግባር ብቻ የፋይናንስ ሕጉን በመከተል በሥራ ላይ በማዋል የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር በማስመርመር በወቅቱ ለቦርዱ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተደንግጓል፡፡

ይሁንና የተለያዩ ፓርቲዎች በ2013 በጀት ዓመት በመሥፈርቱ መሠረት ተከፋፍሎ በፓርቲው የተለየ የባንክ ሒሣብ ቁጥር ገቢ የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ አስመልክቶ በሕጉ መሠረት የኦዲት ሪፖርት እና የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ማቅረብ ቢኖርባቸውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ፓርቲዎች ግን የኦዲት ሪፖርቱን በተሟላ መልኩ ያላቀረቡ መሆናቸው ታውቋል፡-

ሀ/ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ አቅርበው የኦዲት ሪፖርታቸውን ያላቀረቡ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ራዴፓ)

የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋሕነን)

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ (አሕፓ)

የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ)

ኅዳሴ ፓርቲ (ኅዳሴ)

ለ/ የኦዲት ሪፖርት እና የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ያላቀረበ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)

የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (ኦነን)

ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኅብር ኢትዮጵያ)

የምዕራብ ሶማሌ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ምሶዲፓ)

የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ጌሕዴድ)

የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ)

ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት (ዓረና)

የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ሐዲድ)

ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሞዴፓ)

የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)

የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን)

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ)

የአገው ብሔራዊ ሸንጎ (ሸንጎ)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ)

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

ሐ/ የኦዲት ሪፖርት አቅርቦ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ያላቀረበ

1. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕነዴን)

በመሆኑም የተያዘው የ2014 በጀት ዓመት ሊጠናቀቅ ሁለት ወራት የማይሞላ ጊዜ ስለቀረው፤ ለበጀት ዓመቱ የተመደበው ድጋፍ በባንክ ሒሣብ ቁጥር ገቢ እንዲደረግ ያለፈው የ2013 በጀት ዓመት ድጋፍ የኦዲት ሪፖርትና ገንዘቡ ለፓርቲዎቹ ገቢ የተደረገበትን የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ በአስቸኳይ እንዲያቀርቡ ቦርዱ ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወቂያ

ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም.
Tue, 17 May 2022 15:18:20 +0000 admin 734 at https://nebe.org.et የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ፓርቲዎች የሚያካሄዱትን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ የተሰጡ ማብራሪያዎችን ተመልክቶ ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳለፈ https://nebe.org.et/am/node/737 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ፓርቲዎች የሚያካሄዱትን ጠቅላላ ጉባዔ በተመለከተ የተሰጡ ማብራሪያዎችን ተመልክቶ ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳለፈ admin Thu, 05/12/2022 - 09:58

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ፓርቲዎች ከሚያካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ ጋር በተያያዘ ተከታዮቹን ውሳኔዎች አሳልፎ ለፓርቲዎቹ አሳውቋል።

1. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር/ኦብነግ

የተወሰነበት ቀን፦ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔውን ከሚያዝያ 22-24 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚያደርግ ለቦርዱ በመግለጽ የጠቅላላ ጉባዔውን ዝግጅት የሚያሳይ መረጃ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ቢያቀርብም፣ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 8.5 መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ መወሰን ያለበት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በመሆኑ የማዕከላዊ ኮሚቴው ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ የወሰነውን ውሳኔ ዝርዝር የሚያሳይ ቃለ ጉባዔ ደብዳቤ በደረሳቸው በ5 ቀን ውስጥ አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ ለፓርቲው ሊቀመንበር በጽሑፍ አሳውቋል።

በሌላ በኩል የኦብነግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሕመድ ያሲን መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የፓርቲው ሊቀመንበር የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠሩ በ19 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በቀረበ ጥያቄ በየካቲት 19 ቀን 2014 ዓ.ም (Feb 25/2022) በኢሜል ብንልክም ሊቀመንበሩ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸው መተዳደሪያ ደንቡን ይጥሳል ሲሉ ለቦርዱ ነጥቡን ያስረዳል በሚል ያቀረቡት ሰነድ በርግጥም የኢሜል ልውውጥ በጉዳዩ መደረጉን የማያሳይ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የፓርቲው ም/ሊቀመንበር፣ ሊቀመንበሩ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠሩ ተጠይቀው ፍቃደኛ አለመሆናቸውን በተመለከተ አለ የተባለውን ማስረጃ ደብዳቤ በደረሳቸው በ5 የስራ ቀን አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አሳውቋል።

2. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)

የተወሰነበት ቀን፦ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ፣ በመጪው ሰኔ ወር 2014 መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሄድ በመግለጽ የፓርቲው መሪ እና ምክትል መሪ የኃላፊነት ጊዜያቸው ቢያበቃም የመሪ እና የምክትል ምርጫውን በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ለማካሄድ የሚያስቸግር ስለሆነ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 7.1.1፣ 18.3.3 እና 18.3.2 ለጊዜው ከመፈጸም ታግደው እንዲቆዩ እና የፓርቲው መሪ እና ምክትል መሪ ለአንድ ጊዜ ብቻ እንደ ሌሎች የጉባኤ ተመራጭ ኃላፊዎች እንዲመረጡ በሙሉ (የተባበረ) ድምጽ ስለወሰነ በሚል ሥራ አስፈጻሚው ለጠቅላላ ጉባኤው ለማቅረብ ያዘጋጀውን የውሳኔ ሐሳብ ሰነድ ለቦርዱ አያይዞ አቅርቧል።

ቦርዱ ጉዳዩን መርምሮ ከዚህ የሚከተሉት በፓርቲው እንዲፈጸሙ አሳውቋል፦

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከላይ የተገለጸውን ውሳኔ ያሳለፈበትን ቃለ ጉባኤ እንዲቀርብ

ለቦርዱ ከቀረበው በተጨማሪ ለጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ የሚቀርብ የደንብ ማሻሻያ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጸድቆ ከሆነ ሰነዱ እንዲቀርብ

ቦርዱ ፓርቲው መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ያደረገውን የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ በተመለከተ የሰጣቸውን የውሳኔ ነጥቦች፣ የተወሰዱ ርምጃዎች እና የተዘጋጀ የደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ካለ ሰነዱ እንዲቀርብ

ቦርዱ ታዛቢዎችን በአዋጁ አንቀጽ 79/2 መሠረት መላክ ይችል ዘንድ ጠቅላላ ጉባኤ የሚደረግበት እንዲገለጽ

3. ለዎላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ሊቀመንበር

የተወሰነበት ቀን፦ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም

የፓርቲው የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የፓርቲው አመራሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት የፓርቲው ሊቀመንበር ጉባኤውን ለመጥራት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እንዲሁም የተፈጠረው አለመግባባት የግንባሩን ሕልውና የሚያናጋ እና አስጊ ወደሆነ አቅጣጫ የሚያመራ በመሆኑ ችግሩን በጉባኤ ለመፍታት ጉባኤ መጥራት የወሰነ እና የቦርዱ ታዛቢ እንዲላክለት በተለያየ አቤቱታ አሳውቋል፡፡

በፓርቲው ደንብ መሠረት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የሚችለው ለፓርቲው ሊቀመንበር በቅድሚያ አስቸኳይ ጉባኤውን እንዲጠራ ካሳሰበ እና ሊቀመንበሩም ይህን ተከትሎ አስቸኳይ ጉባኤውን ለመጥራት ፍቃደኛ ያልሆነ ከሆነ ነው፡፡

በመሆኑም ቦርዱ የፓርቲው ሊቀመንበር በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እስከ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲጠሩ፥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ስላደረጉት ዝግጅት እንዲሁም ጉባኤውን ለመጥራት ያለውን ዝርዝር እቅድ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ለቦርዱ እንዲያሳውቁ ይህ ካልተፈፀመ በፓርቲው መተዳደሪያ መሠረት የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ አስመራጭ ኮሚቴና ጊዜያዊ ሊቀመንበር በመሠየም ጠቅላላ ጉባኤ የመጥራት ሥልጣን ያለው መሆኑን ቦርዱ ለፓርቲው ሊቀመንበር እና ለኢንስፔክሽን ኮሚሽኑ ቦርዱ ገልጿል፡፡

4. ለአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ)

የተወሰነበት ቀን፦ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም

አትፓ ከቦርዱ በተጻፈ ደብዳቤ ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የተወሰኑ ውሳኔዎች በፓርቲው ደንብ መሠረት መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ በየትኛው አካል እንደተወሰነ ማብራሪያ እና የውሳኔው ቃለ ጉባኤ እንዲሁም የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የተመረጡበት ዝርዝር ሥርዐት እና የጉባኤ አጀንዳ እንዲያቀርብ ተገልጾለታል፡፡

ፓርቲው በበኩሉ ጠቅላላ ጉባኤውን አስመልክቶ መሟላት ያለባቸው ነጥቦችን በተመለከተ አስቸኳይ የማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ መጋቢት 10 እና ሚያዝያ 5 ቀን 2014 ዓ.ም እንዳደረገ ገልጾ የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ እና የለቀቁ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ዝርዝር አያይዞ አቅርቧል፡፡

ሆኖም የቀረቡት ቃለ ጉባኤዎች በቦርዱ እውቅና ባገኙ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምልዐተ ጉባኤ በማሟላት የተደረገ ስብሰባ አለመሆኑን መመልከት ተችሏል፡፡ ቦርዱ ጉዳዩን መርምሮ በደንቡ መሠረት የተሟላ የማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ በመስጠት እስከ ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደረግና ከጠቅላላ ጉባኤ አንድ ሣምንት በፊት የጠቅላላ ጉባኤውን ዝግጅት በሚመለከት የማዕከላዊ ኮሚቴው ያደረገውን ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ተያይዞ እንዲቀርብ በጽሑፍ አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም.

Blog Display

Thumbnail

Thu, 12 May 2022 06:58:44 +0000 admin 737 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/737#comments certificate https://nebe.org.et/am/node/731 certificate admin Wed, 05/04/2022 - 13:55 Wed, 04 May 2022 10:55:17 +0000 admin 731 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/731#comments የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ላይ የተደረገ የግምገማ ውጤት እንዲሁም የተገኙ ትምህርቶችን ማስተዋወቂያ እና ማጠናቀቂያ ዐውደ-ጥናት ዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማካሄድ ጀምሯል፡፡ https://nebe.org.et/am/node/730 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ላይ የተደረገ የግምገማ ውጤት እንዲሁም የተገኙ ትምህርቶችን ማስተዋወቂያ እና ማጠናቀቂያ ዐውደ-ጥናት ዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማካሄድ ጀምሯል፡፡  admin Thu, 04/28/2022 - 14:25

ቦርዱ የ6ተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ በምርጫ ሂደቱ ላይ ከተገበራቸው የተለያዩ ተግባራት የተገኙ ትምህርቶችን የመሠነድ ተግባር ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በሂደቱ የምርጫ ቦርድ አባላት፣ ሠራተኞች፣ የክልል ጽ/ቤት ሃላፊዎች፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ታዛቢ ቡድኖች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የፊደራል እና የክልል የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፍትሕ አካላት፣ የፀጥታ እና ሕግ አስከባሪ አካላት በተጨማሪም ከአጋዥ ድርጅቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ፎር ኤሌክቶራል ሲስተምስ (IFES) እና ዩሮፕያን ሴንተር ፎር ኤሌክቶራል ሰፓርት (ECES) በአጠቃላይ ከ400 በላይ ተሳታፊዎች ከተለያዩ የባላድርሻ አካላት በማካተት በየካቲት እና በመጋቢት ወራት ላይ ከ50 በላይ አነስተኛ የቡድን ውይይቶች፣ የምክክር መድረኮች፣ የቃል እና የጽሑፍ መጠይቆች ተከናውነዋል፡፡

የግምገማ ሂደቱ የተካሄደበት ሥነ-ዘዴ ዓለም ዐቀፋዊ ተቀባይነት ያላቸው ዋና ዋና የምርጫ መርሆችን ማለትም ነፃነት፣ ገለልተኝነት፣ ግልጽነት፣ የሙያ ብቃት አካታችነት እና ዘለቄታዊነትን መሠረት ባደረገ መልኩ ነው፡፡ በሂደቱም ትኩረት የተደረገባቸው ዋና ዋና የምርጫ ዑደቶች የሆኑት የሕግ እና ተቋማዊ መዋቅር፣ የምርጫ ኦፕሬሽን ዕቅድ እና ትግበራ፣ የመራጮች ምዝገባ፣ የዕጩዎች ምዝገባ፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ፣ የድምፅ አሰጣጥ እና ቆጠራ፣ የውጤት አያያዝ፣ የምርጫ ክርክር አፈታት፣ ምርጫን የመታዘብ ሂደት፣ የመራጮች ትምህርት፣ የሥርዓተ ፆታና አካታችነት የመሳሰሉት ጉዳዮች ናቸው፡፡

በዚህ ለሁለት ቀን በሚቆየው ዐውደ-ጥናት ላይ የተገኙ ግኝቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ውጤታማ ተሞክሮዎችን በማካተት ተተንትኖ በዛሬ እና በነገው እለት ከላይ የተጠቀሱት ባለድርሻ አካላት በተከኙበት ይቀርባል፡፡ በዐውደ-ጥናቱ ላይ የተገኙ ትምህርቶችና ተግባራዊ የመፍትሄ ሀሳቦች ማጠቃለያ ሪፖርት ቦርዱ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ ሲሆን ሪፓርቱ በቀጣይ ለሚያከናወኑ ምርጫዎችም ሆነ አጠቃላይ ተግባራት ገንቢ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Image

Blog Display

Gallery

Thu, 28 Apr 2022 11:25:42 +0000 admin 730 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/730#comments የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብልፅግና ፓርቲ (ብልፅግና) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ https://nebe.org.et/am/node/729 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብልፅግና ፓርቲ (ብልፅግና) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ admin Wed, 04/27/2022 - 13:19

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብልፅግና ፓርቲ (ብልፅግና) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ; ሙሉ መግለጫዉን ለማግኘት እዚህ ላይ የጫኑ

Blog Display

Thumbnail

Wed, 27 Apr 2022 10:19:07 +0000 admin 729 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/729#comments የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ https://nebe.org.et/am/node/728 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ admin ቲዩ, 04/26/2022 - 13:13

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ ሙሉ መግለጫዉን ለማግኘት እዚህ ላይ የጫኑ

Blog Display

Thumbnail

Tue, 26 Apr 2022 10:13:29 +0000 admin 728 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/728#comments የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱን ተከትሎ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ባደረገዉ ማሻሻያ ላይ ቦረዱ ያሳለፈዉ ዉሳኔ https://nebe.org.et/am/node/727 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱን ተከትሎ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ባደረገዉ ማሻሻያ ላይ ቦረዱ ያሳለፈዉ ዉሳኔ  admin Thu, 04/14/2022 - 14:36

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱን ተከትሎ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ለቦርዱ ሪፓርት አቅርቧል፡፡ ቦርዱም ፓርቲው ያወጣውን ማሻሻያ ደንብ በመመርመር ያልተሟሉ ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ እንዲያደርግ ውሳኔውን ያሳወቀበት ደብዳቤ ከስር ያገኙታል፡፡

እዚህ ላይ ይጫኑ

Blog Display

Thumbnail

Thu, 14 Apr 2022 11:36:32 +0000 admin 727 at https://nebe.org.et https://nebe.org.et/am/node/727#comments