የግልም ሆነ የፓርቲ እጩዎች በመጪው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የእጩ ወኪሎችን በየምርጫ ጣቢያው መመደብ እንደሚችሉ ይታወቃል። በመሆኑም የእጩ ወኪሎቻችሁን ዝርዝር እና አይነት እነዲሁም መስፈርቱን ማሟላታቸውን ከሚገልጽ ከሸኚ ደብዳቤ ጋር በየምርጫ ክልሉ ጽኅፈት ቤት እንድታቀርቡ እና የእጩ ወኪሎች መታወቂያ እንድትወስዱ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወቂያ
ጷግሜ 05 ቀን 2013 ዓ.ም