Skip to main content

የስራ ማስታወቂያ የቢሮ ኃላፊ

መግቢያ፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ ምርጫን እንዲያስፈጽም እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲያስተዳድር ሥልጣን የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ ይህን ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ ተቋሙን በአዲስ መልክ በሚወጡ ሕጎች መሠረት እንደገና ማደራጀት ተገቢና አስፈላጊ መሆኑ ታምኗል፡፡ ተቋሙን በአዲስ መልክ የማደራጀት ዋናው ዓላማ የተቋሙን ተዓማኒነት እና ብቃት ከፍ ማድረግ እንዲሁም ነፃ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ የሆነ ምርጫ ማካሄድ እንዲቻል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫና በድኅረ ምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ አስጠንቶ ባጠናቀቀው ጥናት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ እና በድህረ ምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ አስጠንቶ ባጠናቀቀው ጥናት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ውይይት አካሄደ። ከጥናቱ መጠናቀቅ አስቀድሞ ፤ላለፉት ወራት ጥናቱን መሠረት ያደረጉ ውይይቶች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያካሄደ ሲሆን፤ በዚሁ በተጠናቀቀው ጥናት ላይ መጋቢት 12 በተደረገው ውይይት ደግሞ ከዚህ በፊት ያልተሳተፉ ግን የሚመለከታቸው ሲቪል ማኅበራትን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ሩጫ ላይ ተሳትፎ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በተካሄደው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሴቶችና እና የአካል ጉዳተኞች ሩጫ ላይ ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን በተለይ የአካል ጉዳተኞች ውድድር ላይ ትኩረት በማድረግ ለአባላቱ ያለውን አጋርነት አጠናክሯል። በዕለቱ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሁለት ተኩል የቀጠለው የሴት አካል ጉዳተኞች የሩጫ ውድድር ‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአካል ጉዳተኞች ውድድር' በሚል ስያሜ የተካሄደ ሲሆን በውድድሩ ላይ ከተለያዩ በአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ላይ ከሚሠሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አባላት የተውጣጡ ሴት የአካል ጉዳተኞች ተሳትፈዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ ‘አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ በ 2015 ዓ.ም በቦርዱ የተደረገለትን የበጀት ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ እንዳላዋለ እና ከፍተኛ ገንዘብ በፓርቲው አመራሮች እና ሌሎች አባላት ለግል ጥቅም እንዲውል መደረጉን በመገንዘቡ ፓርቲው እና አመራሮቹ እንዲታገዱ፤ተገቢው የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር እና አላግባብ ወጪ የሆነውን ገንዘብ በተመለከተ የፍ/ብሄር ክስ እንዲመሰረትና ገንዘቡ ለቦርዱ ተመላሽ እንዲደረግ የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ውሳኔ አሳልፋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

Share this post

ድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ባልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች ምርጫውን ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በአፋር ክልል በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣ በቡሬሞዳይቱ ፣ ገዋኔ ፤ በዳሎል እና በጉሊና የምርጫ ክልሎች ላይ እንዲሁም በቤንሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ ነዋሪ የሆኑ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ቦርዱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል በዚህም መሰረት፤

• ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ

• ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገላችሁ

• የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆናችሁ

• የ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላችሁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከታዛቢ ሲቪል ማኅበራት እና የሰብአዊ መብቶች ተከታታይ ድርጅቶች ጋር በተያዘው ዓመት የሚካሄደው ምርጫን አስመልክቶ ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ለሚያከናውነው የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ቀሪና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ ጊዜያዊ የጊዜ ሠሌዳ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይኽንንም ተከትሎ ቦርዱ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከታዛቢ ሲቪል ማኅበራት እና የሰብአዊ መብቶች ተከታታይ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በተከናወነው የታላቁ ሩጫ ፕሮግራም ማስተዋወቂያ ላይ በመገኘት ለታዳጊ ተማሪዎች ስለምርጫ ምንነትና የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተግባር የተደገፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ አደረገ፡፡

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ሩጫ አስተባባሪዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለመነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ፕሮግራሙን አስተዋውቋል፡፡ በዚህ መርሀ ግብር ላይ የተጋበዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተለይም ለታዳጊ ተማሪዎች ስለምርጫ ምንነት እና በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ዙሪያ በተግባር የተደገፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ አድርጓል፡፡

Share this post

በስነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት ላይ ለሚሳተፉ የሲቪል ማህበራት የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በመራጮች ትምህርት እውቅና አሰጣጥ እና ስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2020 በተደነገገው መሰረት በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የመራጮች ትምህርት መስጠት እንዲችሉ እውቅና የመስጠት ኃላፊነት አለበት።

Share this post

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲሁም መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫው ባልተካሄደባቸው በ አፋር፤ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 ዓ.ም. በጀት ምርጫውን ለማከናወን በዝግጅት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት በ አፋር ክልል (በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣በ ዞን 3 ቡሬሞዳይቱ እና ገዋኔ፤ በዞን 2 ዳሎል እንዲሁም በዞን 4 ጉሊና) የምርጫ ክልሎች ላይ እንዲሁም በ ቤንሻንጉልጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል፤ በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ቦርዱ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል በዚህም መሰረት፤

•ከ 18 አመት በላይ የሆናችሁ