የ6 ኛው ዙር ቀሪና የድጋሚ ምርጫ የሚካሄድባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር
ሀ) መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ ያሉ መረጃዎች
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ምርጫ የሚያካሂድባቸው ክልሎች ዝርዝር ከስር በሚገኝዉ ማስፈንጠሪያ ላይ ማግኘት ይቻላል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት የሚከናወንባቸውን የምርጫ ክልሎች ዝርዝር ከስር በሚገኙት ማስፈንጠሪያዎች ላይ ማግኘት ይቻላል
ለ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ ያሉ መረጃዎች
የምርጫ ክልል ቢሮዎች አድራሻ ከነልዩ የቦታ መጠሪያ ስማቸው
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ
የምርጫ ክልሎች ዝርዝር
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ ምርጫ የሚከናወንባቸው የምርጫ ክልሎች ከስር በሚገኙት ማስፈንጠሪያዎች ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን እያንዳንዱ ክልል ውስጥ ለፌዴራል (የተወካዮች ምክር ቤት) መቀመጫ እና ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ የሚመረጥባቸው የምርጫ ክልሎች እና የመቀመጫዎች ብዛት ዝርዝር ማግኘት ይቻላል። በአጠቃላይ አሁን የጊዜ ሰሌዳ በወጣለት 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ 673 የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ ይደረጋል።
የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር
ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሎች እና በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር የሚከተለው ሲሆን የእያንዳንዱ ክልል የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር ከስር ባሉት ሊንኮች ላይ ይገኛል።
የምርጫ ጣቢያ ዓይነት አጠቃላያ መግለጫ - 49,407
አዲስ አበባ ከተማ - 1,848
አፋር ክልል - 1,432
አማራ ክልል -12,199
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 699
ድሬዳዋ ከተማ -305
ጋምቤላ ክልል - 431
ሐረር ክልል - 285
ኦሮሚያ ክልል - 17,623
ሲዳማ ክልል - 2,247
ደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ህዝቦች ክልል - 8,281
ሶማሊ ክልል - 4,057
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎችን እና የምርጫ ጣቢያዎችን በመላው ሀገሪቱ እንዲያቋቁም በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀፅ 7 ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ መሠረት የተቋቋሙ የምርጫ ክልሎች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 14 መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሥልጣን እና ተግባር ይኖራቸዋል። አንድ የምርጫ ክልል፦
- ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፦
- የምርጫ ቁሳቁሶችን ለምርጫ ጣቢያዎች ያሰራጫል፣
- ዕጩዎችን ይመዘግባል፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ዕጩዎች የመታወቂያ ካርድ ይሰጣል፣
- ከምርጫ ጣቢያዎች የሚመጡ ሰነዶችና የምርጫ ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው መምጣታቸውን ያረጋግጣል፣ ይረከባል፣ በጥንቃቄ እንዲያዙ ያደርጋል፤
- ምርጫ ጣቢያዎች ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል፤
- በህግ መሠረት ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ውሳኔ ይሰጣል፤
- ከምርጫ ጣቢያ የመጡ የምርጫ ውጤቶችን በመደመር አሸናፊዎችን ከለየ በኋላ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ በማድረግ አስፈላጊ ቅጾችን በመሙላት ለቦርዱ ይልካል፤
- የዕጩ ወኪሎችን ዝርዝር ለምርጫ ጣቢያዎች ያስተላልፋል፤
- የምርጫ ክልሉን ሦስት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን በዚህ አዋጅና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ያስመርጣል፤
- በምርጫ ክልሉ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን የጋራ ምክክር ያስተባብራል፤
- የምርጫ ሂደትንና ውጤትን በተመለከተ ከምርጫ ጣቢያ ለሚመጡ አቤቱታዎች አፋጣኝ ምላሽ ወይም ውሳኔ ይሰጣል፤
- ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የተመራጭነት መታወቂያ ለአሸናፊዎች ይሰጣል፤
- ከቦርዱ ወይም ከክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በቦርዱ የሚቋቋም አንድ የምርጫ ጣቢያ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 16 መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሥልጣን እና ተግባር ይኖሩታል፡-
- መራጮችን ይመዘግባል፤
- ከምርጫ ክልሉ የሚላኩ የምርጫ ቁሳቁሶችን ተቀብሎ በጥንቃቄ ይይዛል፤
- በህጉ መሠረት ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ምርጫ ያካሂዳል፣
- በህጉ መሠረት የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች ያስተናግዳል፣
- የተሰጠውን ድምፅ ቆጠራ በማካሄድ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመለጠፍ ለህዝብ ያሳውቃል፣
- የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው እና ተጠብቀው ለምርጫ ክልሉ እንዲላኩ ያደርጋል፣
- በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 (10) እና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የምርጫ ጣቢያውን አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሁለት አባላት ያስመርጣል፣
- በምርጫ ሂደት ለሚከሰቱ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣
- ከቦርዱ፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ወይም ከምርጫ ክልል የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 17 መሠረት ቦርዱ ከምርጫ ክልላቸው ርቀው በካምፕ ለሚኖሩ ወታደሮች፣ ሲቪል ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ዜጎች፣ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲሁም በእስር ቤት ለሚገኙ የመምረጥ መብታቸው ያልተገፈፈ ዜጎች በምርጫ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መራጮቹ በሚገኙበት ቦታ ወይም አካባቢ ልዩ ምርጫ ጣቢያ ሊያቋቁም ይችላል፡፡
ቦርዱ ስለ ምርጫ ክልሎች እና ስለ ምርጫ ጣቢያዎች ከታች የተረዘረዘሩትን የተለያዩ መመሪያዎች በማርቀቅ ላይ ይገኛል፡-
- የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ አደረጃጀት እና የምርጫ ዝግጅት መመሪያ
- በልዩ ሁኔታ የሚቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መመሪያ እና
- ተንቀሳቃሽ የምርጫ ጣቢያዎች እና የመራጮች ምዝገባ መመሪያ
ስለ ምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 12 ጀምሮ እስከ አንቀጽ 17 ይመልከቱ፡፡