Skip to main content

መረጃ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፉት ቀናት እንዳሳወቀው በአዲስ አበባ የመራጮች መዝገባ እስከሚያዝያ 29 ቀን 2013 የተራዘመ ሲሆን ያንን ተከትሎ 1500 ሰው በሞላባቸው ቦታዎች ተጨማሪ 32 ምርጫ ጣቢያዎችን ከፍቷል። የምርጫ ጣቢያዎቹ ዝርዝር የሚከተለው ነው። ይመዝገቡ ካርድዎቸን ይውሰዱ።

1. የካ ክ/ከ የምርጫ ክልል 16 ወረዳ 05 ም/ጣ/01-01 ንኡስ ጣቢያ

2. የካ ክ/ከ የምርጫ ክልል 16 ወረዳ 05 ም/ጣ/03-01 ንኡስ ጣቢያ

3. የካ ክ/ከ የምርጫ ክልል 16 ወረዳ 05 ም/ጣ/04 ንኡስ ጣቢያ

4. የካ ክ/ከ የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ አያት -1 ንኡስ ጣቢያ

5. ቦሌ ክ/ከ የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ ኮንደሚኒም 4-1

6. ቦሌ ክ/ከ የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ መሪ ሀ-3 ንኡስ ጣቢያ

7. ቦሌ ክ/ከ የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ አያት 3 ንኡስ ጣቢያ

Share this post

ከአትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ የተሰጠ አጭር ማሳሰቢያ

በፓርቲዎች ዘንድ አንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተልን አጠናቆ ለህትመት ዝግጁ በማድረግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም ፓለቲካ ፓርቲዎች ከእጩዎች ጋር የተገናኙ ማንኛውንም አቤቱታዎች በአስቸኳይ ማጠናቀቅ ይኖርበታል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመረጮች ምዝገባና አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሂደቶችን ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች ሪፓርት አቀረበ

መድረኩን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የመሩት ሲሆን፤ ምርጫ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የሚያሣትፍ መድረክ እንደሆነና ከባለድርሻ አካላቱ መካከልም ፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ እንደመሆናቸው መጠን ስሕተቱንም ስኬቱንም እንዲያውቁ በማድረግ እየተራረሙ ለመሄድ በተከታታይ እየተዘጋጁ ያሉት መድረኮችን ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ገልጸዋል። የሰብሳቢዋን ንግግር ተከትሎ የቦርዱ የኦፕሬሽን ክፍል ባልደረቦች ለምርጫ ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች የግዢ አፈጻጸም፤ ሥርጭትና የሰው ኃይል ሥምሪትን፣ የቁሳቁሶች ጥራትና ደኅንነት አጠባበቅን፣ እንዲሁም ከምርጫ ጣቢያዎች አከፋፈት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።

Share this post