የምርጫ ቀን በምስል
ዜጎች በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ድምጽ እየሰጡ ሲሆን ከምርጫ ጣቢያዎች የተወሰኑት ይህንን ይመስላሉ
6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም መከናወኑ ይታወሳል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በእለቱ የፓለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ዴስክ በማቋቋም በስልክ፣ በአጭር መልእክት፣ በደብዳቤ አቤቱታዎችን ሲቀበል እና በእለቱ መፈታት የሚችሉትን ችግሮችም ሲፈታ መቆየቱ ይታወሳል።>/p>
ቦርዱ ከድምፅ መስጫው ቀን በማስከተል በተለያየ ሁኔታ የቀረቡትን አቤቱታዎች ሲመለከት እና ሲመረምር ቆይቷል። አንዳንዶቹ አቤቱታዎች በየደረጃው በሚከናወነው የምርጫ ሂደት መቅረብ የነበረባቸው እና በምርጫ ክልሎች እና ጣቢያዎች ደረጃ የሚቀርቡ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ቦርዱ በምርመራ የሚያያቸው ናቸው። ቦርዱ ከአቤቱታዎቹ የተቆራረጡ፣ ሙሉ መረጃ ያልያዙ እና መካተት የሚገባውን መረጃዎች ያካተቱ ባለመሆናቸው ምርመራውን አስቸጋሪ መሆኑን ተረድቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. እለታዊ የሚዲያ ማብራሪያ ይሰጣል። በመሆኑም ከታች የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ ብዙኃን መገናኛ ከቀኑ 10:30 ስካይላይት ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
•በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን የተመዘገበ የብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን፣
•የቦርዱን ልዩ የዘገባ ባጅ ፊት ለፊት ማንጠልጠል
•ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች (የፎቶ/የቪዲዮ ባለሙያን ጨምሮ) ብቻ መሣተፍ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ክልል ደረጃ የውጤት ድመራ ተጠናቆ ምርጫ ክልል ሃላፊዎች ወደ ማእከል ሰነዶችን ይዘው እንዲመጡ እንደሚያደርግ ይታወቃል። በመሆኑም የክልል መስተዳድሮች የምርጫ ክልል ሃላፊዎች እና የውጤት ሰነዶቻቸውን ወደማእከል በሚያመጡበት ወቅት ሊሰጣቸው የሚገባውን ትብብር አስመልክቶ ቦርዱ ያቀረበው ደብዳቤ
እንደሚታወቀው የ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ እየተከናወነ ይገኛል።
1, የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዘግይቶ የተጀመረባቸው ቦታዎች በመኖራቸው
2, የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቁሳቁስ ስርጭት የዘገየባቸው ቦታዎች በመኖራቸው
3, ድምፅ ለመስጠት ረጅም ሰልፉች ላይ ያሉ ዜጎች በመኖራቸው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ድረስ መራዘሙን ቦርዱ ያሳውቃል። በዚህም መሰረት የምርጫ አስፈፃሚዎች እስከ 3 ሰአት ድረስ የሚመጣ ማንኛውንም መራጭ እንዲያስተናግዱ ጥሪ እናስተላልፋለን። ነገር ግን የመራጮች መዝገባቸው ላይ ያሉ ዜጎች መርጠው ያጠናቀቁባቸው እና ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋት እና የቆጠራ ስራ መጀመር ይችላሉ።
በድምፅ አሰጣት ሂደት ወቅት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች 778 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
በድምጽ መስጫ ቀን የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው?
ወደ ምርጫ ጣቢያ የማይገቡ ነገሮች ምንድናቸው?
1. ድምፅ ለመስጠት በተመዘገበችበት የምርጫ ጣቢያ የተገኘች መራጭ፡-
ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ያላት፣
ለ) የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም በመራጮች ምዝገባ ወቅት የተረጋገጠበት ሌላ ሰነድ ያላት፣ወይም ማንነትዋ በምርጫ ምዝገባ ወቅት በምስክሮች ስለመረጋገጡ
በመራጮች መዝገብ ላይ የሰፈረላት፣
ሐ) የመራጮች መዝገብ ላይ ስሟ የሰፈረ፣
መ) ድምፅ ያልሰጠች መሆኑ ሲረጋገጥ ድምጿን የመስጠት መብት አላት
2. የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ የጠፋባት መራጭ ጉዳዩን ለምርጫ ጣቢያው በማስረዳት ማንነቷ እንዲሁም በመዝገቡ ላይ ስሟ የሰፈረና ያልመረጠች መሆኑ ሲረጋገጥ ጉዳዩ በቃለ ጉባኤ ተይዞ እንድትመርጥ ይደረጋል፡፡
1. የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ነፍሰጡሮችን፣ ጨቅላ ህጻናት የያዙ ወላጆችን፣ መለዮ የለበሱ የመከላከያና የፖሊስ አባላትን ቅድሚያ በመስጠት ድምፅ እንዲሰጡ ማድረግ አለበት
2. በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ምልክት ለማድረግና የድምፅ መስጫ ወረቀቱን ወደሳጥን ለመክተት እገዛ የሚያስፈልገው መራጭ ራሱ የመረጠውን ሰው ይዞ የመምጣት መብት አለው
3. በዚህም መሰረት በድጋፍ ፈላጊው የሚመረጥ ሰው :-
ሀ) ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
ለ) እጩ ተወዳዳሪ ወይም የእጩ ወኪል መሆን የለበትም
4. አንድ ድጋፍ የሚሰጥ ሰው ከአንድ በላይ መራጭ ለመደገፍ አይችልም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ደብዳቤ በተገለጸው መሰረት ለሁሉም ደብዳቤ ለደረሳቸው ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች እስከ ነገ ሰኔ 13 ቀን 2013 ዓ.ም እኩለ ቀን ድረስ ይህንን ማዘጋጀታቸውን በጽሁፍ እንዲያረጋግጡ እና በደብዳቤ፣ በኢሜይል፣ ወይም በማንኛውም ኤሌክትሮኒክ መንገድ እንዲያሳውቁ ለማሳሰብ ይወዳል።