የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ከሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ጎን ለጎን በቡሌ ምርጫ ክልል ላይ የድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ በወሠነው መሠረት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ምርጫው በጋራ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ስለሆነም ከዚህ በፊት በቡሌ ምርጫ ክልል ላይ ለመምረጥ የተመዘገባችሁ ወይንም ምርጫው ላይ የተሣተፋችሁ ግለሰቦች በሙሉ በድጋሚው ምርጫ ላይ እንድትሣተፉ እየጠየቅን፤ በድጋሚ ምርጫው ላይ ለመሣተፍ የሕዝበ ውሣኔው የመራጮች ምዝገባ ላይ የተመዘገባችሁ መሆን የማይጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ሕዝበ ውሣኔው ከድጋሚ ምርጫው ጋር አይገናኝም። በተጨማሪም ድምፅ ወደ’ምትሰጡበት ምርጫ ጣቢያ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ካርድ መያዝ፤ ከዚህ በፊት በምሥክር የተመዘገባችሁ ከሆነ ደ’ሞ የምሥክርነት ሠነዱን መያዝ፤ ሠነዱ በእጃችሁ የማይገኝ ከሆነ ደ’ሞ በዕለቱ ነዋሪነታችሁን የሚያረጋግጡ የቀበሌው ነዋሪዎችን በመያዝ ምርጫውን መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጎን ለጎን በሚካሄዱት ሕዝበ ውሣኔ እና የድጋሚ ምርጫ ላይ በምርጫ አስፈጻሚነት የምትሣተፉ ሠራተኞች፤ ቀደም ሲል በወሰዳችሁት ሥልጠናና በሕጉ መሠረት መራጮችን እንድታስተናግዱ ቦርዱ ያሳውቃል።

ማስታወቂያ