Skip to main content

የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በጀመረባቸው ምርጫ ክልሎች መራጮች ምዝገባ ተጠናቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርደ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባን በአጠቃላይ ያጠናቀቀ ቢሆንም ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል። በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ላይ ያለው የመራጮች ምዝገባ ትላንትና ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት የመራጮች ምዝገባ በትላንትና ግንቦት 13 ቀን 2013 የተጠናቀቀባቸው ቦታዎች

Share this post

ለ2013 ጠቅላላ ምርጫ አዲስ የታዛቢነት ፈቃድ ለሚጠይቁ የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበራት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ «የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011» እንዲሁም «የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012» በሚደነግገው መሠረት፣ ምርጫ ለመታዘብ ፍላጎት ያላቸውን የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይፋዊ ማስታወቂያ በማውጣትና በመመልመል በአንደኛ ዙር ለ36 ድርጅቶችን እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።

Share this post

በ6ተኛ አጠቃላይ ምርጫ በአስፈጻሚነት ለመሳተፍ የምትፈልጉ በሙሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 130 ሺህ በላይ አስፈጻሚዎችን መልምሎ የመራጮች ምዝገባን እንዳጠናቀቀ ይታወቃል። በሰኔ 14 ቀን 2013 ለሚካሄደው የድምጽ መስጫ ቀን ተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መመልመል ይፈልጋል በመሆኑም

በዚህም መሰረት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመከናወን ላይ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅና ተያያዥ የሥራ ሂደቶችን አስመልክቶ ቦርዱ በነገው ዕለት ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ በልዩ ሁኔታ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የኦፕሬሽን ሥራዎችን ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ዛሬ ላይ መድርሱ ይታወቃል።

Share this post

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ተራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል። በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሚደገረው መራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ቦርዱ ወስኗል። በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ድረስ https://www.ovrs.gov.et በሚገኘው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ይህንን የኦንላየን ምዝገባ በማስታወስ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ እንድታደርጉ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

Share this post

የመራጮች መዝገብ ለህዝብ ግልጽ የሚደረግበት ሂደት

የመራጮች ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ ተግባራዊ ከሚሆኑ ዋና ዋና የምርጫ ተግባራት አንዱ የመራጮች መዝገብን ለህዝብ ይፋ ማድረግ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መዝገብ ይፋ የማድረግን ሂደት ከቅዳሜ ግንቦት 7 ቀን 2013 - ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ያከናውናል።

በዚህም ወቅት ምርጫ ጣቢያዎች ክፍት ሆነው መዝገቡ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ሲሆን በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች መረጃቸውን ለማጣራት፣ መታወቂያ የወሰዱ ወኪሎች ያሏቸው ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እና ታዛቢዎች ሂደቱን ሊያዩት ይችላሉ። ይፋ የማድረግ ሂደቱም እንደሚከተለው ሲሆን በዚህ ሂደት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች ወይም አስተያየቶች ካሉ ለማሻሻል ይረዳን ዘንድ በነጻ የስልክ መስመራችን 778 በመደወል እንዲያሳውቁን ቦርዱ በአክብሮት ይጠይቃል።

የመራጮችን መዝገብ ለህዝብ ግልፅ የማድረግ ሂደቶች

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የመራጮች ምዝገባ ሂደት አፈጻጸምና አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሂደቶች እንዲሁም መጪ ሁነቶችን የተመለከተ ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የመራጮች ምዝገባ ሂደት አፈጻጸምና አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሂደቶችን እንዲሁም ቀጣይ የምርጫ ተግባራትን የተመለከተ ብዙኃን መገናኛ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተከፈተው መድረክ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት፣ የሎጀስቲክ ማጓጓዝ፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደትና የተለያዩ ተግዳሮቶች ከነተሰጡባቸው መፍትሔዎች ጭምር ቀርበውበታል። በሎጀስቲክ ማጓጓዝ ወቅት የተፈጠሩ መስተጓጎሎች፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የተስተዋሉ የምርጫ ጣቢያዎች በጊዜ አለመከፈትና የተከፈቱት ሲሞሉም በአፋጣኝ ንዑስ ጣቢያዎችን ለመክፈት ከክልልና ከከተማ መስተዳደሮች ጋር በመነጋገር መፍትሔ ለመስጠት እንደተሞከረ ሆኖም ግን በሚፈለገው ፍጥነት ቦታዎቹን ማግኘቱ ቀላል እንዳልነበረ ተገልጿል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ወረቀት የኅትመት ሂደትንና የደኅንነት አጠባበቅ ሥርዓቱን ለፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አስጎበኘ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች የተወጣጣ የልኡካን ቡድን ወደደቡብ አፍሪካ በመላክ የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመትን እንዲጎበኙ አደረገ። በቦርዱ ከፍተኛ አመራር ፍቅሬ ገብረ ሕይወት ለተመሩት ከፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ለተውጣጡ ተወካዮች የድምፅ መስጫ ወረቀት የኅትመት ሂደቱን፣ የቴክኒክና የደኅንነት አጠባበቅ ሥርዓቱን በዝርዝር ማሳየት ችሏል። ቦርዱ የፍትሐዊ አሠራሩ አንዱ ማሳያ አድርጎ ከሚወስደው የድምፅ መስጫ ወረቀት የዕጩዎች አደራደር ቅደም ተከተል መወሠኛ ሎተሪን በይፋ ካስጀመረበት ከመጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመቱ የተጀመረ ሲሆን፤ ይህንንም ሥራ ከሚያካሂዱት ሁለት የኅትመት ድርጅቶች አንዱ በሆነውና በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን የሬን-ፎርም ኅትመት ማኅበር ከፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች የተወጣጡ የታዛቢ ቡድኑ አባላት ጎብኝተውታል።

Share this post

የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል

በመላው አገሪቱ በ11 ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል። በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር ክልል፣በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል, በሲዳማ ክልል እንዲሁም ሶማሌ ክልል የድምጽ መስጫ ካርድ የመውሰጃ የመጨረሻ ቀን ዛሬ በመሆኑ ድምጽ መስጫ ካርድ ያልወሰዳችሁ ዜጎች እንድትወስዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለዜጎች መረጃ የምታቀርቡ ሚዲያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች እና የፓለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች የምዝገባ የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በማስታወስ ዜጎች ካርዳቸውን እንዲወስዱ እንድታበረታቱ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ለሚገኙ አስፈጻሚዎች የስራ ዉል በተመለከተ የፃፈዉ ደብዳቤ

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የስራ ውል ያላችሁ በየደረጃው የምትገኙ አስፈጻሚዎች የስራ ውላችሁ መራዘሙን የሚያሳየው ደብዳቤ ከስር የተያያዘ ሲሆን ለየምርጫ ክልሎቹ እና ዞን አስተባባሪዎች የተላከው ይህ ደብዳቤ እንደ ህጋዊ ሰነድ የሚቆጠር መሆኑን እናሳውቃለን።

ደብዳቤዉን ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ ለአይ.ሲ.ቲ ቲም ሊደሮች       ለምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈፃሚዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post