Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ቦ. ዴ. ፓ) መጋቢት 10 እና 11 ቀን 2014 ዓ.ም ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲዉ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ቦ. ዴ. ፓ) መጋቢት 10 እና 11 ቀን 2014 ዓ.ም ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለመዘገብ ከቦርዱ ዕውቅና ላገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ የሚያካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ ለመዘገብ አመልክተው ከቦርዱ ዕውቅና ለተሰጣቸው የመገናኛ ብዙኃን ባሙያዎች ታኅሣሥ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰጠውን ሥልጠና በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ቦርዱ እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚደረገው ሕዝበ ውሣኔ ሦስተኛው እንደሆነ አስታውሰው፤ መገናኛ ብዙኃኑ በሕዝበ ውሣኔው ሂደት በሚሠሯቸው ዘገባዎች ከወገንተኝነትና ከጥቅም ግጭት ነፃ ሆነው ኃቅንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን መሠረት ባደረገ መልኩ መዘገብ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 እስከ ታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያካሄድ የነበረውን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን ተከትሎ የመራጮችን መዝገብ ለአምስት ቀናት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ።

ቦርዱ የመራጮችን መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ያደረገው ከዛሬ ታኅሣሥ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. (ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ሳይጨምር) እስከ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታዛቢነት የመሣተፍ ፍላጎት ላላቸው የሀገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሥልጠና እና ዕውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ በታዛቢነት የመሣተፍ ፍላጎት ላላቸው የሀገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት ስድስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማመልከቻቸውን አስገብተው የተገመገሙ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አራቱ ግምገማውን አልፈውና አስፈላጊውን ሥልጠና ወስደው ዕውቅና አግኝተዋል። ዕውቅና ያገኙት ታዛቢ ድርጅቶች ባመለከቱት መሠረት ለጠቅላላው የምርጫ ዑደት 5,274 ታዛቢዎችን እንደሚያሰማሩ ይጠበቃል።

ግምገማውን ያለፉት ታዛቢ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች

• የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE)፣

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢ.ሰ.መ.ኮ) የሰብአዊ መብት ተከታታዮች እውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ እና በቡሌ ምርጫ ክልል የሚፈፀመው የድጋሚ ምርጫ ሂደት የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ እንዲከታተሉ ለ 17 የኢ.ሰ.መ.ኮ ሰራተኞች የሰብአዊ መብት ተከታታይነት (Human Rights Monitors) እውቅና ሰጠ።

Share this post

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምዝገባ የተሰረዘባቸውን ምርጫ ጣቢያዎች በተመለከተ የተሰጠ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ እያከናወነ ባለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት፤ በቦርዱ የኦፕሬሽን ሥራ ክፍል በተዋቀሩ የክትትልና የቁጥጥር ቡድን አማካኝነት በዎላይታ እና በጎፋ ዞኖች በሚገኙ የተወሠኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን ማረጋገጡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ቦርዱ ባሳለፈው ውሳኔ ጣቢያዎቹ ላይ የተደረገው ምዝገባ እንዲሠረዝ፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱም ሙሉ በሙሉ እንዲቆምና እንዲሁም የጣቢያዎቹ ሠራተኞች ከኃላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የመራጮች ምዝገባውም አዲስ ሠራተኞች ተመልምለው በድጋሚ እንዲደረግ መመሪያ በሰጠው መሠረት፤ የመራጮች ምዝገባው በተሠረዘባቸው ጣቢያዎች ከታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም.

ከታኅሣሥ 11 እስከ ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የተከናወነው የመራጮች ምዝገባ ሪፖርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ከታኅሣሥ 11 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በ3753 ምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው የሕዝበ ውሣኔ የመራጮች ምዝገባ 1,773,670 መራጮችን የመዘገበ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 217 የአካል ጉዳተኞች ይገኙበታል። አጠቃላይ የተመዝጋቢው ቁጥር በፆታ ሲገለጽ 943,076 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 830,594 ሴቶች ናቸው። ከተመዘገቡት የአካል ጉዳተኞች ውስጥም እንዲሁ 111 ሴቶች ሲሆኑ ቀሪ 106 ወንዶች ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎችን አቋቋመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ከዚሁ ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሕዝበ ውሣኔው የሚሣተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ በአሁኑም ሰዓት በአንድ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማቆያ ካምፕ ውስጥ ላሉ መራጮች፤ ሰባት ልዩ ምርጫ ጣቢያዎችን ማለትም በኮንሶ 3፣ በአሌ 3 እና በዲራሼ 1 ምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም፤ የመራጮች ምዝገባን የተመለከተ “ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች” ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች የተዋረድ ሥልጠና ሰጥቷል፤ ለመራጮች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች ሥርጭቱንም እንዲሁ አጠናቋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ውሣኔ በሚካሄድባቸው አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተፈጸሙ የሕግ ጥሠቶችን በተመለከተ የወሰዳቸው የዕርምት ዕርምጃዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያከሂደው ሕዝበ ውሣኔ የምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም የመራጮች ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህንንም የምዝገባ ሂደት ለመከታተትልና ለመቆጣጠር ከቦርዱ የኦፕሬሽን ሥራ ክፍል የተዋቀረ ቡድን ከታኅሣሥ 16 - ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባደረገው የክትትል ሥራ፤ በዎላይታ እና በጎፋ ዞኖች በሚገኙ ከታች በዝርዝሩ ላይ በተጠቀሱት የምርጫ ጣቢያዎች ላይ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን አረጋግጧል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በደብረ-ብርሃን ከተማ ያካሄደውን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ አስመልክቶ ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰጠዉ የዉሳኔ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በደብረ-ብርሃን ከተማ ያካሄደውን 2ኛ መደበኛ ጉባዔና ውጤቱን ከሕጉና ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንጻር መርምሮ ሕጉን ያልተከተሉ ውሣኔዎች በማግኘቱ ያላጸደቀ መሆኑን ገልጾ፤ ቦርዱ ዕውቅና የሚሰጠው ሰኔ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የፀደቀውን የፓርቲውን ሕገ-ደንብ፤ ብሔራዊ ምክር ቤት እና ሌሎች የፓርቲው አካላትን ብቻ እንደሆነ ማሳወቁን ተከትሎ፤ ፓርቲው የቦርዱ ውሣኔ አግባብነት እንደሌለው ገልጾ ሥራ አመራር ቦርዱ ጉዳዩን መርምሮ የዕርምት ውሣኔ እንዲሰጥልን ሲል ታኅሣሥ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ለቦርዱ በላከው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡

Share this post