Skip to main content

የዕጩዎችን ዝርዝር ይፋ ስለማድረግ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣አፋር ሶማሌ እና መስቃን እና ማረቆ-2 የምርጫ ክልሎች ላይ የእጩዎች ምዝገባ ከሚያዝያ 21 አስከ ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ማከናወኑ ይታወቃል። በመሆኑም የምርጫ ሕጉ ተወዳዳሪ እጩዎችን ቦርዱ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ በደነገገው መሰረት ቦርዱ በቦርዱ የተረጋገጡ የእጩዎችን ዝርዝር ከዚህ በታች ይፋ አድርጓል፡፡

 PDFለተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ዝርዝር

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 2016 ዓ.ም. በሚያካሂደው ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል የሚወሥነውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት አካሄደ ::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር፣ የሶማሌ እና የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሚያካሂደው ምርጫ የተለያዩ የቅድመ-ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። ከነዚህም ተግባራት አንዱ የዕጩዎች ምዝገባ ሲሆን፤ በትላንትናው ዕለት ማለትም ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የተመዘገቡ ዕጩዎችን በድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ የሚኖራቸውን የአደራደር ቅደም ተከተል የሚወሥነውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።

በዚህ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ላይ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢን ጨምሮ ሁሉም የቦርድ አመራር አባላትና በምርጫው ላይ የሚሣተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዩች የተገኙ ሲሆን፤ ሥነ-ሥርዓቱም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ተከፍቷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባላት ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የምርጫ ሥራዎችን በተመለከተ የመስክ ምልከታና ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሁለት ቀናት የቆየ ምክክር አካሄዱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር፣ የሶማሌ እና የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሚያካሂደው ምርጫ የተለያዩ የቅድመ-ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ የመራጮች ምዝገባ ከሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በመከናወን ላይ በሚገኝባቸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የቦርዱ የበላይ ኃላፊዎች የመሥክ ጉብኝት እና ውይይት ከግንቦት 7-8 ቀን 2016 ዓ.ም. አካሂደዋል፡፡

በመስክ ጉብኝቱ በምርጫ ክልሎቹ ላይ እየተከናወነ ያለውን የምርጫ ነክ ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ ከመመልከታቸው በተጨማሪ፤ በምርጫ ጣቢያዎቹ በመከናወን ላይ ያለውን የመራጮች ምዝገባ አጠቃላይ ሁነትን የተመለከቱ ሲሆን በየምርጫ ጣቢያዎቹ በሥራ ላይ ከነበሩ ከመራጮች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።

Share this post

NEBE study visit in Berlin

The Board of NEBE was invited to Germany by its long-standing partner: the Netherlands Institute for Multiparty Democracy (NIMD). The study visit was in Berlin from the 15th to the 19th of April 2024.

The study visit focused on: Germany's electoral system (legal framework, institutions and management); learning about political party registration, administration/regulation; and getting an understanding of the Berlin State Election Commission's relations with other Governmental organs (Federal Parliament and Regional Parliaments)

Share this post

የእጩዎች የመጨረሻ ዙር የማጣራት ሂደት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደሚያከናውን ይታወቃል ነገር ግን ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ግለሰቦች በ 2013 ዓ.ም በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ወቅት እጩ የነበራችሁ ሲሆን አሁን በምናደርገው ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ እንድትሳተፉ በቦርዱ የመረጃ ቋት ውስጥ ባላችሁ ስልክ ቁጥር በመደወል ለማግኘት የተደረገው ጥረት ስልካችሁ ሊሰራ ባለመቻሉ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም። ይሁን እንጂ ቦርዱ በምርጫ አዋጁ 1162/2011 አንቀጽ 39 (2) መሰረት የእጩዎችን የመወዳደር መብት ለመጠበቅ የመጨረሻ ማጣራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረው ግለሰቦች አስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. እስከ ጠዋቱ አራት ሰዓት ድረስ በስልክ ቁጥር 0995003794 በመደወል እንድታሳውቁ ቦርዱ ጥሪ ያቀርባል፡፡

Share this post

እጩ ከነበራችሁበት ፓርቲ መልቀቃችሁን ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደሚያከናውን ይታወቃል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የዕጩ ምዝገባ ከሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጹት የፓርቲያችሁ አባላት በዚህ ምርጫ እንደማይሳተፉ እና በሌላ እጩ መተካታቸውን አሳውቃችሁናል፡፡ ይሁን እንጂ ቦርዱ በምርጫ አዋጁ 1162/2011 አንቀጽ 39 (2) መሰረት የእጩዎችን የመወዳደር መብት ለመጠበቅ የመጨረሻ ማጣራት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ግለሰቦችን በቦርዱ የመረጃ ቋት ውስጥ ባላቸው ስልክ ቁጥር በመደወል ለማግኘት የተደረገው ጥረት ስልካቸው ሊሰራ ባለመቻሉ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረው ግለሰቦች ከፖለቲካ ፓርቲያችሁ መልቀቃቸሁን ለፓርቲያችሁ እንድታሳውቁ እና መልቀቃችሁን የሚገልጽ ሰነድ ለቦርዱ እንድትልኩ እንጠይቃለን።

Share this post

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚካሄደውን ምርጫ መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን የቀረበ ጥሪ

የመገናኛ ብዙኃን ቀጣዩ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ምርጫው ፍትሐዊ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ እንዲሆን የሚያበረክቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ፤ የመገናኛ ብዙኃኑና ጋዜጠኞች በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ለመዘገብ የሚያስችል የፍቃድ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ይህንን ጥሪ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ በዚህ መሠረት ለመዘገብ ጥያቄ የሚያቀርቡ የመገናኛ ብዙኃን፡

Share this post