የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት የተሳትፎ ጥሪ ማስታውቂያ
በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው ተቋማት የቀረበ ጥሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዜጎች በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ አካታች እና ተደራሽ የሆኑ የኪነጥበብ ሥራዎችን በተለይም የማህበረሰብ አቀፍ ቲአትር እና ሙዚቃ ነክ የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ጥሪ ያቀርባል። በመሆኑም በዚሁ ጉዳይ ላይ ፍላጎት እና ልምዱ ያላችሁ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት በተናጠል ወይም በጋራ በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማቅረብ ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ወረቀት (Expression of interest) እንዲሁም የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ ለቦርዱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል።