የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲን በተመለከተ ከቦርዱ የተሰጠ መግለጫ
የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር ከሀገር መውጣታቸውንና ፓርቲውንም የሚመራ ሰው መወከላቸውን ከውጭ ሀገር ሆነው ለቦርዱ ሲያሳውቁ ከፓርቲው አመራሮች መኃል ይህ በሊቀመንበሩ የተሰጠው የውክልና ሥልጣን ደንቡን የተፃረረ ነው የሚል ቅሬታ ለቦርዱ አቀረቡ፡፡ ቦርዱም ሊቀመንበሩ የሰጡት የውክልና ሥልጣን ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንፃር የተፈፀመ መሆን አለመሆኑን መረመረ፡፡ የፓርቲው መተዳደያ ደንብ አንቀጽ 22/1/ የፓርቲው ሊቀመንበር በማይኖሩበት ወቅት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ ሊቀመንበሩን ተክተው እንደሚሰሩ ደንግጓል፡፡ በዚሁ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ከሀገር በወጡት የፓርቲው ሊቀመንበር የተሰጠው ውክልና ደንቡን የተፃረረ በመሆኑ ቦርዱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 22/1/ መሠረትም እንዲፈፅም ወስኗል፡፡ ይሁንና በፓርቲው አመራሮች መኃል አለመግባባቱ እየጨመረ በመሄዱ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 74 (6) መሠረት ጉዳያቸው በባለሙያዎች ጉባኤ እንዲታይ ቦርዱ ወስኖ የባለሙ