Skip to main content

የቦርድ አባላት ጥቆማን ስለመስጠት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባላት ጥቆማን ለመስጠት የሚከተለውን መረጃ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በአዲሱ አዋጅ 1133/2011 መሰረት የአዳዲስ የቦርድ አባላት ምልመላ የሚመራው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በቋቋሙት እጩ ቦርድ አባላት መልማይ ኮሚቴ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ከአውሮፓ ህብረት ተወካይና የህብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል

ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም.            

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ከአውሮፓ ህብረት ተወካይና የህብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ወቅት የምርጫ ቦርድን አዲስ አደረጃጀት፣ የምርጫ ቦርዱን አዳዲስ የቦርድ አባላት ምልመላ፣ የምርጫ በጀትና የፋይናንስ ድጋፍ፣ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበውሳኔ፣ የቤትና የሕዝብ ቆጠራ መራዘም እና ከምርጫ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ የተፈናቀሉ ዜጎች እና የመምረጥ መብቶቻቸውን፣ የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሮቹ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱም የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የህብረቱ አባል አገራት ቦርዱን ተአማኒ እና ብቃት ያለው ተቋም ለማድረግና መጪው ምርጫ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ እንዲሆን የሚደረገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡፡

Share this post

ለፓርቲዎች የዕለት ተዕለት ሥራ ማገዣ በሚል መንግሥት የመደበውን 10 ሚሊየን ብር ሥራ ላይ እንዳላዋለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተናገረ

ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓ.ም.   

ለፓርቲዎች የዕለት ተዕለት ሥራ ማገዣ በሚል መንግሥት የመደበውን 10 ሚሊየን ብር ሥራ ላይ እንዳላዋለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተናገረ። ገንዘቡ ሥራ ላይ ቢውል ኖሮ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ብቻ የሚጠቀምበት ይሆን ነበር። ፍትሃዊ ባልሆነ ምርጫ የምክር ቤቶችን ወንበር ሙሉ በሙሉ ለተቆጣጠረው ገዢው ፓርቲ ብቻ ገንዘቡን መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም ብሏል ምርጫ ቦርድ። የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንዳሉት ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር መንግሥት ፓርቲዎችን ለማገዝ በሚል የሚመድበውን 10 ሚሊዮን ብር ፓርቲዎች በምክር ቤቶች ውስጥ ባላቸው መቀመጫ ልክ ገንዘቡ ይከፋፈላል የሚል አሠራር ነበር።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያይተዋል

ሚያዝያ 29 ቀን 2011 ዓም    

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም የጃፓን መንግሥት ለቦርዱና ለቀጣዩ ምርጫ ስለሚያደርገው ድጋፍ ውይይት ያደረጉ ሲሆን አምባሳደሩ የጃፓን መንግሥት ለምርጫ ቦርዱ የሚያደርገውን ድጋፍ በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል።

Share this post