የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዶክመንቶችን ማሟላት ያለባቸውን ሲቪል ማህበራት አስመልክቶ የሚከተለውን ጥሪ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲያስነግር ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በሚዲያ የተደረገውን ጥሪ ያልሰማችሁ እና የመራጮች ትምህርት ለማስተማር ማመልከቻ አስገብታችሁ የነበራችሁ ሲቪል ማህበራት ማስታወቂያውን ከስር ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ 

ማስታወቂያ - የመራጮችን ትምህርት ለማስተማር ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ፈቃድ መጠየቂያ ላቀረባችሁ የሲቪክ ማህበራት እና ትምህርት ተቋማት በሙሉ
ጥቅምት 02 ቀን 2013 ዓ.ም  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እንዲሁም የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና የሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 04/2012 በሚደነግገው መሠረት የመራጮች ትምህርት ለሚሠጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና የትምህርት ተቋማት ፈቃድ ለመስጠት ይችል ዘንድ ድርጅቶቹ ማመልከቻቸውን እንዲያቀርቡ በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ 

ይህንንም አስመልክቶ የቀረቡትን ማመልከቻዎች ቦርዱ በመመርመር በአዋጁ እና በመመሪያው መሠረት መሟላት ከሚገባቸው ሰነዶች እና መረጃዎች በከፊል አለማሟላታችሁን ተመልክቶ ያልተሟሉ ሰነዶችን በዝርዝር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም መሟላት የሚገባቸው ሰነዶች እና መረጃዎች ተሟልተው እንዲቀርቡ ቦርዱ በነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው ጥሪ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ምላሽ መስጠት ያልቻላችሁ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የጊዜ ገደቡ ተራዝሟል፡፡ በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በሚዲያ ከወጣበት ከጥቅምት 02 ቀን 2013 ጀምሮ ለ10 ቀናት ማለትም እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2013  ድረስ በቦርዱ የፌዴራል እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመምጣት ቀሪ ሰነዶቻችሁን በመዝገብ ቤት እንድታስገቡ እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወቂያ
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም