Skip to main content

ማብራሪያ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ባስታወቀው መሰረት የፓርቲዎች የጠቅላላ ጉባኤ ሲያካሂዱና ለማካሄድም ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በዚህም መሰረት የፓርቲዎች የጠቅላላ ጉባኤ ሁኔታ ማጠቃለያ የሚከተለውን ይመስላል።

ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄዱ ፓርቲዎች

  1. ብልጽግና ፓርቲ
  2. ህዳሴ ፓርቲ
  3. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
  4. የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ

ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ በጊዜ ገደቡ መሰረት ቀን ያሳወቁ ፓርቲዎች

Share this post

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23 ቀን 2014 ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር በአዋጅ ቁጥር 1162/11 እና በመመሪያ ቁጥር 3/2011 መሠረት ከ6ተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ በምክክሩ ወቅትም ለፓርቲዎች መገለጹ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው እለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ ከስር ስማችሁ የተዘረዘረ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንድታስገቡ እናሳስባለን።

አገራዊ ፓርቲዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አካሄደ። ምክክሩን የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳና የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ የመሩት ሲሆን፤ በምክክሩም የፖለቲካ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ተከትሎ በአባላቶቻቸውና በአመራሮቻቸው አግባብ ያልሆነ እሥር እና እንግልት እንደተፈፀመ በመግለፅ ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት የቦርዱ ተወካይ ሰብሳቢ፣ የአቤቱታ አቅራቢ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች እና የብልጽግና ፓርቲ ተወካይ አባል የተካተቱበት አጣሪ ቡድኖች ተቋቁመው የቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት አቤቱታ ወደቀረበባቸው ክልሎች በመንቀሳቀስ እንዲያጣሩ መደረጉን ተከትሎ የተገኙ ውጤቶችን ተመልክተዋል።

Share this post

የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባን አስመልክቶ ቦርዱ የሰጣቸው አዳዲስ ውሳኔዎች አጭር መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 65 መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎችን ምዝገባ እና ድጋሚ ምዝገባ ሲያከናውን እንደነበር ይታወቃል። በዚህም መሰረት ምዝገባቸው የታደሰላቸው ፓርቲዎች እንዳሉ ሁሉ ምዝገባ መስፈርቱን ያላሟሉ ከ27 በላይ ፓርቲዎችን መሰረዙ ይታወሳል። በህጉ መሰረትም በቦርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኙ የተለያዩ ፓርቲዎች ወደፍርድ ቤት በመሄድ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ከነዚህ ፓለቲካ ድርጅቶች መካከል

1. ኦሮሞ ኦቦ ነጻነት ግንባር ( ኦአነግ)

2. የኦሮሞ አንድነትና ዴሞክራሲ የፌዴራል የሰላም ለውጥ ( ኦአዴፌሰለ)

3. የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር ( ኦነአግ)

4. ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ( ኦዳ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አካሄደ፣ የተለያዩ ውሳኔዎችንም አስተላለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ያደረገ ሲሆን ምክክሩም ፓርቲዎች በማስከተል (ከምርጫ ማግስት) ሊያሟሏቸው ስለሚገባቸው መስፈርቶች፣ ከመንግስት ስለሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ እና እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ ስላጋጠማቸው ገደቦች ያካተተ ነበር፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሰቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ በተመራው ይህ ውይይት ላይ በቦርዱ ተመዝግበው የሚገኙ የፓለቲካ ፓርቲዎች ተገኝተዋል።

ለፓርቲዎች ከመንግስት ስለተሰጠው ድጋፍ እና ድጋፉን አስመልክቶ ማቅረብ ስለሚገባው ሪፓርት ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ ስለጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም ፓርቲዎች አባላት እና ደጋፊዎቻቸው ላይ ስላጋጠሟቸው ችግሮች ምክክር ተደርጓል።

በመሆኑም ምክክሩን ተከትሎ ቦርዱ የሚከተሉት ውሳኔዎችን አስተላልፏል፤

Share this post

መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድምጽ አሰጣጥ ተከናውኖባቸው በአቤቱታ ምክንያት ይፋ ያልተደረጉ የምርጫ ክልሎችን አስመልክቶ የተሰጠ መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሶማሌ፣ በሃረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ድምጽ አሰጣጥን በመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ያከናወነ ሲሆን በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የአቤቱታዎች ዝርዝር ታይቶ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ይፋ ያልተደረጉ የምርጫ ክልሎች እንደነበሩ ይታወቃል። ቦርዱ የነበሩ አቤቱታዎችን በዝርዝር በማየት በምርጫ ክልሎቹ የተከናውነው የድምጽ አሰጣጥ እና ቆጠራ ላይ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

ሶማሌ ክልል

Share this post

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በሚገኙ 17 ምርጫ ክልሎች ( በአብዛኛው የክልል ምክር ቤት) ምርጫ ያልተከናወነ መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ፓርቲዎች፣ የክልል መስተዳደር እና የጸጥታ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እና ምክክሮችን ሲያደርግ ቆይቶ፣ የሚያስፈልገውን የጸጥታ ፍላጎቶች ከተሟሉ ምርጫው ሊከናወንበት የሚችለውን ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ለፓርቲዎች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አቅርቧል። ከስር በሚገኘው ማስፈንጠሪያ የሚያስፈልገውን የፀጥታ ሃይል ሁኔታ፣ የዝግጅት ማጠቃለያ እና የቀረበውን የጊዜ ሰሌዳ መመልከት ይቻላል።

1. የጊዜ ሰሌዳ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው 6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ እና ድጋሚ ምርጫ ለተሳተፋችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች በሙሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ባላካሄደባቸው እና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው ምርጫ ክልሎች እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሣኔ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት ቦርዱ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ አቤቱታ ያላችሁ ከሆነ ከመስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ እስከ መስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የአቤቱታ ማቅረቢያ ቅፅ በመሙላት በስካይላይት ሆቴል በሚገኘው የቦርዱ ዴስክ እንድታቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡