የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የድጋሚ ህዝብ ውሳኔ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ነው።

በዚሁ መሠረት በዎላይታ ዞን ስር በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ህዝበ ውሳኔ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም የዎላይታ አካባቢ ነዋሪ የሆናችሁ፣ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ አመልካቾች ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ እንድታመለከቱ ቦርዱ ያሳውቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡-

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣

• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣

• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣

• የሥራ ቦታ፦ በዎላይታ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣

• የስራ ቆይታ ፦ ከ8 እስከ 10 ቀን

• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤

በመሆኑም ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መሥፈርቶች የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ አማካኝነት ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ፣ ለ7 ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያስተላልፋል።

https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም.

የስራ ማስታወቂያ
ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም.