Skip to main content
  • Fikre Gebrehiwot member
    ፍቅሬ ገ/ሕይወት የቦርድ አባል
    አቶ ፍቅሬ ገ/ሕይወት ከአምስቱ የቦርድ አመራር አንዱ ናቸው። አቶ ፍቅሬ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሕግና በታሪክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያገኙ ሲሆኑ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በልማት ጥናቶችና በፕሮጀክት አስተዳደር አግኝተዋል።
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስጋት ከግምት ውስጥ ያስገባ ምርጫ ለማከናወን እየሰራ ነው

    ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ሊከናወን አለመቻሉ ይታወሳል። ቦርዱ በአሁኑ ወቅት በምርጫ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭትን በመከላከል ረገድ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን ለማከናወን ይረዳ ዘንድ የኮቪድ-19 አስተባባሪ ቀጥሮ የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸመ ነው።

    ከእነዚህም ውስጥ በምርጫ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር አዘጋጅቶ ያጸደቀው መመሪያ አንዱ ሲሆን በዚህ መመሪያ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ የጋራ ምክክር መድረክ አከናወኗል። ከዚህም በተጨማሪ የሰራቸው ስራዎች የሚከተሉት ናቸው።

    Share this post

    ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለመመልመል የወጣ ማስታወቂያ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎቸን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ አንደሆነ ይታወቃል።

    ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል።

    በዚህም መሰረት

    - ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ

    - ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ

    - ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ

    - የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ምዝገባ ሂደትና የቴክኒክ ሥራዎችን የተመለከተ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አደረገ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትላንትና የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ምዝገባ ሂደትና የቴክኒክ ሥራዎችን የተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መገናኛ ብዙኃን በተገኙበት ውይይት አድርጓል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ በተገኙበት የተደረገው ውይይት በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ላይ ያጋጠሙ የተለያዩ ግኝቶች የቀረቡበት ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ሂደት የቀረቡ አቤቱታዎችና የተሰጡ መፍትሔዎች በዝርዝር በቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ቀርበዋል።

    Share this post

    የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው የሲቪል ማህበራት እና ሚዲያዎች የተደረገ ጥሪ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል፣ በዚህም መሰረት የተወሰኑ ተቋማት በተወዳዳሪዎች መካከል የምርጫ ክርክር ለማከናወን ከቦርዱ ፍቃድና አቅጣጫ ለማግኘት ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

    ይህንን እንዲሁም ሌሎች ልምዶችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ ተጠናቆ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ከታወቁ በኋላ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርን ለማስተባበር ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በፊት ጥያቄ/ ማብራሪያ ያስገባችሁም ሆነ በዚሁ ጉዳይ ላይ ፍላጎት ያላችሁ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት እና ሚዲያዎች በተናጠል ወይም በጋራ የምርጫ ክርክር ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ወረቀት (Expression of interest) ለቦርዱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል።

    የፍላጎት መግለጫ ማካተት የሚገባቸው ዋና ዋና ሃሳቦች

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአውሮፓ ኅብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረከበ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው ዕለት የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም. የአውሮፓ ሕብረትና የጀርመን መንግሥት በጋራ ያበረከቱለትን 22 መኪኖች ተረከበ። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በተገኙበት የተፈጸመው ርክክብ 12 ሃርድ ቶፕ እና 10 ፒክ አፕ መኪኖችን ያካተተ ነው። ዋና ሰብሳቢዋ ቦርዱ የሎጀስቲክ እንቅስቃሴ ላይ ያለበትን ውስንነት ገልጸው ለተደረገው ድጋፍ ያላቸውን ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል። ቦርዱ በመንግሥትም ሆነ በአውሮፓ ሕብረት የሚደረጉለት ድጋፎች አስፈላጊነት ገልጸው፤ ለዛም ቦርዱ አመስጋኝ ነው ብለዋል።

    Share this post

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ምዝግባ እና ተያያዥ የምርጫ ሁነቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ለፖለቲካ ፓርቲዎች አቀረበ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ምዝገባ እና ተያያዥ የምርጫ ሁነቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶች ለፖለቲካ ፓርቲዎች የመገናኛ ብዙኃን በተገኙበት አቀረበ። ሪፖርቱ ሦስት አጀንዳዎችን መሠረት ያደረገ ሲሆን፤ በቅድመ ምርጫ ጊዜ፣ በምርጫው ጊዜና በድኅረ-ምርጫ ጊዜ የሚኖረውን የመረጃ አሰጣጥ ሂደት የተመለከተ ሪፖርት በቦርዱ የመራጮች ትምህርት ክፍል ባልደረባ አማካኝነት ሲቀርብ፤ ቦርዱ የተለያዩ የምርጫ ክልሎች በሚከፍትበት ወቅት ያጋጠሙትን የኦፕሬሽን እና የሎጂስቲክ ፍሰትን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች በቦርዱ የኦፕሬሽን ክፍል ባልደረባ ቀርቧል።

    Share this post