Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎችን አቋቋመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ከዚሁ ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሕዝበ ውሣኔው የሚሣተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ በአሁኑም ሰዓት በአንድ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማቆያ ካምፕ ውስጥ ላሉ መራጮች፤ ሰባት ልዩ ምርጫ ጣቢያዎችን ማለትም በኮንሶ 3፣ በአሌ 3 እና በዲራሼ 1 ምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም፤ የመራጮች ምዝገባን የተመለከተ “ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች” ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች የተዋረድ ሥልጠና ሰጥቷል፤ ለመራጮች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች ሥርጭቱንም እንዲሁ አጠናቋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ውሣኔ በሚካሄድባቸው አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተፈጸሙ የሕግ ጥሠቶችን በተመለከተ የወሰዳቸው የዕርምት ዕርምጃዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያከሂደው ሕዝበ ውሣኔ የምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም የመራጮች ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህንንም የምዝገባ ሂደት ለመከታተትልና ለመቆጣጠር ከቦርዱ የኦፕሬሽን ሥራ ክፍል የተዋቀረ ቡድን ከታኅሣሥ 16 - ታኅሣሥ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባደረገው የክትትል ሥራ፤ በዎላይታ እና በጎፋ ዞኖች በሚገኙ ከታች በዝርዝሩ ላይ በተጠቀሱት የምርጫ ጣቢያዎች ላይ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን አረጋግጧል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በደብረ-ብርሃን ከተማ ያካሄደውን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ አስመልክቶ ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰጠዉ የዉሳኔ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በደብረ-ብርሃን ከተማ ያካሄደውን 2ኛ መደበኛ ጉባዔና ውጤቱን ከሕጉና ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንጻር መርምሮ ሕጉን ያልተከተሉ ውሣኔዎች በማግኘቱ ያላጸደቀ መሆኑን ገልጾ፤ ቦርዱ ዕውቅና የሚሰጠው ሰኔ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የፀደቀውን የፓርቲውን ሕገ-ደንብ፤ ብሔራዊ ምክር ቤት እና ሌሎች የፓርቲው አካላትን ብቻ እንደሆነ ማሳወቁን ተከትሎ፤ ፓርቲው የቦርዱ ውሣኔ አግባብነት እንደሌለው ገልጾ ሥራ አመራር ቦርዱ ጉዳዩን መርምሮ የዕርምት ውሣኔ እንዲሰጥልን ሲል ታኅሣሥ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ለቦርዱ በላከው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አሰመልክቶ ታህሣሥ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. የተሰጠዉ ምላሽ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ታኅሣሥ 3 እና 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ለቦርዱ በተጻፉ ደብዳቤዎች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማድረግ የሚያስችሉትን የቅድመ ጉባዔ ሥራዎች ማጠናቀቁን ገልጾ፤ ጉባዔውን ታኅሣሥ 22 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ መወሠኑን አሳውቋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለማስፈጸም ለተመለመሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለማስፈጸም ለተመለመሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች የመራጮች ምዝገባ ማስፈጸም ተግባራትን የተመለከተ ሥልጠና ከታኅሣሥ 4 እስከ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ሰጠ።

ሥልጠናው በስድስቱ ዞኖችና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚገኙ 31 ማዕከላት ለሁለት ቀናት በተለያዩ ዙሮች የተሰጠ ሲሆን፤ ሥልጠናውም የመራጮች ምዝገባን ለማካሄድ የሚያስችሏቸውን መሠረታዊ የፅንሰ ሃሳብና የተግባር ልምምድ አካቷል ።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ቦርዱ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

በውሣኔውም ፓርቲው ሐምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያሻሻለው መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ጋር የሚቃረኑ አንቀጾችን የለየ ሲሆን፤ አንቀጾቹ ተፈጻሚ እንዳይሆኑ እንዲሁም ጠቅላላ ጉባዔው በቀጣይ ስብሰባው አስፈላጊውን ማስተካከያ አድርጎባቸው ሪፖርት እንዲያቀርብ ሲል መወሠኑን ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ደብዳቤዉ እዚህ ላይ ያገኙታል

የሕዝበ ውሣኔ ምልክት ስለመቀየር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ እና ዲራሼ) በአንድ ክልል መደራጀታቸውን አልደግፍም ለሚለው የሕዝበ ውሣኔ አማራጭ ሃሣብ ነጭ ላም ምልክት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁንና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለቦርዱ የዚህ ሕዝበ ውሣኔ አማራጭ ምልክት ነጭ ላም መሆኑ ቀርቶ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መስተዳድር ዐርማ የሆነው ጎጆ ቤት እንዲሆን ጥያቄ በማቅረቡ፤ ቦርዱም የምክር ቤቱን ጥያቄ ተቀብሎ ከላይ የተጠቀሱትን ስድስቱ ዞኖች እና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል መደራጀታቸውን አልደግፍም ለሚለው የሕዝበ ውሣኔ አማራጭ ሃሣብ ምልክት ጎጆ ቤት እንዲሆን መወሠኑን ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ አስመልክቶ ለደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፃፈዉ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኅዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፓርቲውን ወክለው በ6ኛው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ ተወዳድረው የክልል ምክር ቤት አባል የሆኑትን አባሉ ኅዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን፤ ኅዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ ደ’ሞ በተያዙበት ወቅት አካላዊ ጉዳት ስለደረሰባቸው የሕክምና ዕርዳታ የሚያገኙበት መንገድ እንዲመቻች በመጠየቅ ለቦርዱ አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ፤ ቦርዱም በዐዋጁ በተጣለበት ኃላፊነት መሠረት ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እስከ ኅዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲሰጠው አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ፤ የመራጮች ትምህርት በመስጠት ከሚሠማሩ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ምክክር እና የስልጠና መድረክ አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኅዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከሲቪል ማኅበራቱ ጋር ያደረገውን ምክክር በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ውብሸት አየለ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ሕዝበ ውሣኔው በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ድምፅ በመስጠት ለመሣተፍ ቅድመ ሁኔታውን የሚያሟሉ ዜጎች በነፃነትና በሰላማዊ መንገድ ፍላጎታቸውን የሚገልጹበትን ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ዐውድ ለማረጋገጥ እንዲቻል ቦርዱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ እንደሚገኝና በዕለቱም በመራጮች ትምህርት ላይ ከተሠማሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር የሚካሄደው ምክክር የዚሁ አንድ አካል እንደሆነ ተናግረዋል። የቦርድ አመራር አባል የሆኑት አበራ ደገፉ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዜጎች በንቃት እንዲሣተፉና ፍላጎታቸውንም በነፃነት እንዲገልጹ ማሰተማር አሰፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና ቦርዱ እንዳዲስ ከተቋቋመ በኋላ በተካሄዱት ሁለቱ ሕዝበ ውሣኔዎች ላይ የሲቪል ማኅበራቱ እና የትምህርት ተቋማት የነበራቸው ሚና የላቀ እንደ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለማስፈጸም የተመለመሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ለሚያሠለጥኑ የመሥክ አሠልጣኞች ኅዳር 27-29 ቀን 2015 ዓ.ም. ሥልጠና ሰጠ

በቦርዱ የስልጠና ስራ ክፍል ለ299 የመሥክ አሠልጣኞች በሁለት ዙር የተሰጠው ሥልጠና በአርባ ምንጭ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፤ ሥልጠናውም በሕዝበ ውሣኔው የመራጮች ምዝገባ ሂደት የተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚከናወኑ ተግባራትና ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን የተመለከተ የንደፈ ሃሳብና የተግባር ልምምድ አካቷል።

Share this post