Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ፓርቲዎች ያካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔን ተከትሎ ውሣኔዎች አሣለፈ

ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሞዴፓ) ላይ

የተወሠነበት ቀን ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም.

መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥር ሞዴ82/2014 በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ሪፖርት አቅርቧል።

ቦርዱ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ከሪፖርቱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሯል።

I. አግባብነት ያላቸው የዐዋጁ አንቀጾች ተፈጻሚ የሚሆኑባቸው ጉዳዮች፡-

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ) መጋቢት 03 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ ተከታዩን ውሣኔ አሣልፏል

የተወነበት ቀን ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም.

መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. በቁጥር ካአፓ/1052/ በተጻፈ ደብዳቤ ፓርቲው መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ሪፖርት አቅርቧል።

ቦርዱ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ከሪፖርቱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሯል።

ጠቅላላ ጉባዔውን በተመለከተ

• በፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ የተካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ፤ የቁጥጥር ኮሚሽንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ እጅ በማውጣት መደረጉ በዐዋጅ አንቀጽ 74(3) መሠረት ሚሥጥራዊ በሆነ መልኩ ያልተደረገ የሕጉን አስገዳጅ ድንጋጌ የተቃረነ በመሆኑ ፓርቲው ሕጉን መሠረት በማድረግ በድጋሚ ጠቅላላ ጉባዔ ሊካሄድ እንደሚገባ ቦርዱ ወሥኗል፡፡

የመተዳደሪያ ደንቡን በተመለከተ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ የኢትዮጵያ ሶሻል-ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ ተከታዩን ውሣኔ አሣልፏል

የተወነበት ቀን ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም.

ሚያዚያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥር ESDP/0223/2014 በተጻፈ ደብዳቤ ፓርቲው መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ሪፖርት አቅርቧል።

ቦርዱ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ከሪፖርቱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሯል።

የጠቅላላ ጉባዔ አካሄድን በተመለከተ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ፓርቲዎች ያቀረቡትን የምዝገባ ፍቃድ አስመልክቶ ተከታዩን ውሣኔ አሣልፏል

1. በእነአቶ መንግሥቱ ዩንካ ላይ

የተወሠነበት ቀን ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም.

ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት “የሲዳማ አርነት ግንባር (ሲአግ)” በሚል ስያሜ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ እንዲሰጠው ለቦርዱ አመልክተዋል።

ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ እነአቶ መንግሥቱ ዩንካ ያቀረቡትን የጊዜያዊ ዕውቅና ጥያቄ መርምሯል። በዐዋጁ አንቀጽ 86/1 የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ስያሜ ከተመሳሳይ የፖለቲካ ፓርቲ ስም ጋር የማይመሳሰል ወይም በመራጮች ዘንድ መደናገር የማይፈጥር የፓርቲው ብቸኛ መጠሪያ መሆን እንዳለበት ተደንግጓል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር እና የጽ/ቤት ሃላፊዎች ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከተባበሩት መንግሥታት የፍላጎት ግምገማ ልዑክ የምርጫ ድጋፍ አስተባባሪዎች ጋር ገንቢ ውይይት አካሄደ

ልዑኩ አላማውን የፖለቲካና የምርጫ ምኅዳሩን፣ የምርጫ ዑደቱ የሚተዳደርበት የሕግ እና ተቋማዊ ማዕቀፍን፣ እንዲሁም የባለድርሻ አካላትን ዐቅምና ፍላጎት በመገምገም ምርጫ ቦርዱ በጠየቀው መሠረት የተሻሉ አማራጮችን ማሳየትና ድጋፉ የሚያስፈልገው ምን ላይ ነው የሚለውን መለየት ሲሆን፤ ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ ልዑኩ ፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቭል ማኅበረሰብ ተቋማትን፣ ብዙኃን መገናኛ አካላትን ጨምሮ የምርጫ ባለድርሻ አካላትን አግኝቷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሚያዝያ 19 ቀን ብልጽግና ፓርቲ ያካሄደውን 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት በተመለከተ የፃፈዉ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሚያዝያ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ብልጽግና ፓርቲ ያካሄደውን 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አስመልክቶ ያቀረበው ሪፖርት ላይ ይጎድሉታል ያላቸውን ሠነዶች እና መረጃዎችን ዘርዝሮ ለፓርቲው አቅርቧል። በዚሁ መሠረት ፓርቲው ሚያዝያ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የተጠየቀውን መረጃ ማሟላቱን የሚገልጽ ሠነድ አቅርቧል። ቦርዱም ፓርቲው በድጋሚ የተጠየቀውን ማሟላቱን የገለፀበትን ሠነድ ተመልክቶ ከዚህ በታች የተያያዘውን ውሣኔ አሳልፏል።

ደብዳቤዉን ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

ማስታወቂያ

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመሥክ አሠልጣኝነት ለተሣተፉ ባለሞያዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመሥክ አሠልጣኝነት ለተሣተፉ ባለሞያዎች ለነበራቸው የላቀ ተሣትፎ እያመሰገነ፤ በምርጫው ላይ በአሠልጣኝነት የነበራቸውን ተሣትፎ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችል የምስክር ወረቀት መውሰጃ ፖርታል አዘጋጅቶ አቅርቧል።

የምስክር ወረቀቱ የሚመለከታቸው ባለሞያዎች ከሥር የሚገኘውን ሊንክ በመጫንና የምስክር ወረቀት ፖርታሉ ላይ የሚጠየቁትን የማንነት ማረጋገጫ መረጃ በማስገባት የምስክር ወረቀታቸውን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል።

እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርተፍኬት መስጠት ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለተሣተፉ ሠራተኞች፤ ማለትም የዞን አስተባባሪዎች፣ ምክትል የዞን አስተባባሪዎች፣ የምርጫ ክልል ኃላፊዎች፣ የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዳታ ኢንኮደሮችና የአይ.ሲ.ቲ ባለሞያዎች ለነበራቸው ተሣትፎ ቦርዱ እያመሰገነ፤ በምርጫው ላይ የነበራቸውን ተሣትፎ የሚያረጋግጠውን የምስክር ወረቀት በቀላሉ ለመውሰድ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ፖርታል አዘጋጅቶ አቅርቧል። የምስክር ወረቀቱ የሚመለከታቸው ሠራተኞችም የምስክር ወረቀት ፖርታሉ ላይ የሚጠየቁትን መረጃዎች በማስገባት የምስክር ወረቀታቸውን መውስድ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ ይገልጻል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት እንዲሁም ሰርተፍኬትዎ እንዲደርስዎ እዚህ ላይ ይጫኑ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ዙሪያ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሔደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ዙሪያ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ምክክር አካሄደ፡፡ በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ንግግር የተከፈተው የምክክር መድረኩ፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ተቋማት የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ተሣትፎ ምርጫ በሚደረግባቸው ዓመታት ላይ ብቻ ተወሥኖ እንዳይቀር ግንዛቤ እንዲወሰዱ ለማድረግና በሥነ ዜጋ ትምህርት ቀጣይነት ላይ የቦርዱ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ግንዛቤ መፍጠር ዐላማው ያደረገ ሲሆን፤ መድረኩ ላይ ከቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ በተጨማሪ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት አበራ ደገፋን (ዶ/ር) ጨምሮ የቦርዱ የጽ/ቤት ኃላፊዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ተገኝተውበታል። ከባለድርሻ አካላትም ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችና የዘርፉ ባለሞያዎች፤ እንዲሁም የብዙኃን መገናኛ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት የመንግሥት ድጋፍ አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 100 ንዑስ አንቀጽ ሁለት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለመወሠን መመሪያ አጽድቆ በሥራ ላይ በማዋል በ2013 በጀት ዓመት በመመሪያው መሠረት በማከፋፈል የፓርቲዎቹን ድርሻ ፓርቲዎቹ በከፈቱት የተለየ የባንክ ሒሣብ ቁጥር ገቢ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት ፓርቲዎቹ በባንክ ሒሣብ ቁጥራቸው ገቢ የሆነውን የፋይናንስ ድጋፍ በመመሪያው አንቀጽ 10 መሠረት በአግባቡና ለታለመለት ተግባር ብቻ የፋይናንስ ሕጉን በመከተል በሥራ ላይ በማዋል የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር በማስመርመር በወቅቱ ለቦርዱ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተደንግጓል፡፡