Skip to main content

ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ

የቦርድ ሰብሳቢ


ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ በተለያዩ የመንግስትና የግል ዘርፎች ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱ ሲሆን በተለያዩ የአመራር ስፍራዎችም ላይ ሠርተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ድርጅቱን ለሁለት ዓመታት በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ያገለገሉ ሲሆን በ2013 ዓ.ም. በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫም ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።

ብዙወርቅ ከተተ

የቦርድ አባል


በ1952 ዓ.ም. የተወለዱት ብዙወርቅ ከተተ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በግሪክ፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኩባ ሐቫና ዩኒቨርሲቲ የውጪ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል በሥነ ቋንቋ የሁለተኛ ደረጃ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

አበራ ደገፋ (ዶ/ር)

የቦርድ አባል


ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ በህግ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሠሩት በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሶሻል ወርክ እና ሶሻል ዴቨሎፕመንት ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

ውብሸት አየለ

የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ


አቶ ውብሸት አየለ፣ በ1947 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1980 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል

በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬትና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች

ጥር 13 ቀን 2012 ዓ.ም.   

በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬትና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣
2. አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣
3. አማራ ጊዮናዊ ንቅናቄ፣
4. እናት ፓርቲ፣

አገው ብሔራዊ ሸንጎ እና ብልጽግና ፓርቲም የሙሉ እውቅና ምዝገባ ፈቃድ ማግኘታቸው ይታወሳል። ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ምንድነው?

Share this post

ጨረታ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ለሚቀጥለው ብሔራዊ ምርጫ በተለያየ መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠ ፍቃድ የሚከተሉት አገልግሎትና አቅርቦት ላይ ለመስራት አቅምና ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶችን የማሰባሰቢያ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ በመሆኑም ከስር በሚገኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ዝርዝሩን መመልከት እና ማመልከት ትችላላችሁ፡፡  

ማስታወቂያውን በሪፓርተር፣ በፎርቹን፣ በአዲስ ዘመን እንዲሁም በካፒታል ጋዜጣ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለሚዲያዎች በሙሉ መረጃ ማስተካከያ

ታኅሣሥ 28 ቀን 2012 ዓ.ም.    

የተለያዮ የመንግሥትና የግል ሚዲያዎች የቀጣዮ ብሔራዊ ምርጫ ቀን ሰኔ 21 (June 28) ነው የሚል መረጃ ደርሶናል ትክክል ነው ወይ ብለው ጥያቄ እያቀረቡልን ይገኛሉ። በመሆኑም የሚቀጥለው ምርጫ ቀን ሰኔ 21 (June 28) ነው የሚለው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post