Skip to main content

የሥራ ማስታወቂያ የሚዲያ ክትትል ባለሞያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቋቋም ላይ ላለው የሚዲያ ክትትል ቡድን (Media monitoring team) የተለያየ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሚዲያ ጋር የተገናኘ የሥራ ልምድ ያላቸው ወይም በሚዲያ ክትትልና ሥራ ላይ ያላቸውን ፍላጎት እና ችሎታ በበቂ ሁኔታ ማሳየት የሚችሉ ግለሰቦችን ከአውሮፓ ህብረት የምርጫ ድጋፍ ማእከል ጋር በመተባበር መቅጠር ይፈልጋል፡። 

የሚዲያ ክትትል ባለሞያ የመሆን ፍላጎት ያላችሁ እና መስፈርቱን የምታሟሉ ይህን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ ከአንድ ቋንቋ በላይ ችሎታ ያላቸው አመልካቶች እጅግ በጣም ይበረታታሉ፡፡ 

 

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 

 

የመራጮች ትምህርት መሰጠት ለሚፈልጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ

የመራጮች ትምህርት መሰጠት ለሚፈልጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ

ዜጎች በምርጫ ላይ ያላቸውን ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማረጋጋጥ ብሎም ተአማኒነትን ያተረፈ ሰላማዊ ምርጫ ለማድረግ የመራጮች ትምህርት አስፈላጊነት እሙን ነው፡፡ ይህንን አላማ በአገር ደረጃ ለማሳካትም የሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎ ትልቅ ስፍራ ይይዛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ዓለም አቀፍ ችግር የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስጋት በምርጫ ኦፕሬሽን ላይ ስለሚኖረው ተጽእኖ እንዲሁም ሊወሰዱ ስለሚችሉ አማራጭ እርምጃዎች ውይይት አከናውኗል

መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም.

የገዢው ፓርቲን ጨምሮ 45 የፖለቲካ ፓርቲዎች በሁለት የተለያየ ዙር በዚህ ጉዳይ ላይ በተደረገው ውይይት የተሳተፉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያለው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ለጥቂት ሳምንታት እንኳን ከቀጠለ በቀጣይ በዋናነት መፈጸም በሚገባቸው የመራጮች ትምህርት፣ የአስፈጻሚዎች ስልጠና፣ የቁሳቁስ ስርጭት ከፍተኛ የሰው ዝውውርን የሚያሳትፉ በመሆናቸው የመራጮች ምዝገባ ዝግጅት ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አቅርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ወረርሽኙ በዚሁ መልኩ ከቀጠለ የምርጫው ዝርዝር አፈጻጸም እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተጽእኖዎችን እና ሊፈጠሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን ግምገማ ከፓርቲዎች እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በተከታታይ እንደሚያደርግ አሳውቋል፡፡ 

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልል ካርታን መጋቢት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል

መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም.

ይፋ የማድረጊያ ስነ ስርአቱን በንግግር የከፈቱት ብዙወርቅ ከተተ የቦርዱ አመራር አባል ሲሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የሚዲያ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የህግ ባለሙያ ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር) የምርጫ ክልሎች አከላለል እና ህጋዊ ማእቀፍን አስመልክተው በህገ መንግሥቱ ስለተቀመጠው ምርጫ ክልል ምንነት፣ የምርጫ ክልሎችን መወሰኛ መስፈርትና ተያያዥ የህግ ማእቀፎችን አመላክተው ማብራሪያ አቅርበዋል።

Share this post

በምርጫ ሂደት የሚነሱ አለመግባባቶችና ክርክሮች አፈታት ላይ ለፌደራልና ለክልል ፍርድ ቤት ዳኞች ሥልጠና ተሰጠ

 መጋቢት 5  ቀን 2012 ዓ.ም.

አቶ ሰለሞን አረዳ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ ፕሮግራሙን የከፈቱ ሲሆን፤ ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና፣ የምርጫ እና የሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/11ን አስመልክተው ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።

ራኬብ አባተ የኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ፎር ኢሌክቶራል ሲስተምስ ካንትሪ ዳይሬክተር የምርጫ ዑደትን እና ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የምርጫ ዑደት እና ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 1162/11 ላይ በተሳታፊዎች የቡድን ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

Share this post