ፍቅሬ ገ/ሕይወት


ፍቅሬ ገ/ሕይወት ከአምስቱ የቦርዱ ሥራ አመራር አባል አንዱ ሲሆኑ፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሕግ እንዲሁም በታሪክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በልማት ጥናት እንዲሁም በፕሮጀክት አስተዳደር ሠርተዋል። ከ2000 ዓ.ም. አንሥቶ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያስተማሩ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከማስተማር በተጨማሪ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። ፍቅሬ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን የሠሩ ሲሆን፤ አጫጭር ሥልጠናዎችንም እንዲሁ ሰጥተዋል። የዜና-ልሣን (Journal of the Academy of Ethiopian Languages and Cultures) አስተዳዳሪነትና አርታዒነት (Managing Editor) ከሠሯቸው ሥራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።