የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሀያ ሰባት (27) ፓርቲዎችን ሰረዘ
ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በቀድሞ ህግ ሰርተፍኬት የነበራቸው እና በቀድሞው ህግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ መቶ ስድስት (106) ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ከቦርዱ ደብዳቤ ከደረሳቸው መቶ ስድስት (106) የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሰባ (76) የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰነዶችን ያቀረቡ ሲሆን በሕጉ መሠረት ተሟልቶ የቀረበ ስለመሆኑ እየተመረመረ ይገኛል፡፡