Skip to main content

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ( ኦነግ) አመራር አባላት የቀረበለትን አቤቱታዎች አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ አመራር አባላት የአመራር ለውጥ እና እገዳን አስመልክቶ የተለያዩ አቤቱታዎች ሲደርሱት እንደነበር ይታወቃል፡፡
በአንድ በኩል በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ ነሐሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በቁጥር 06/ABO/12 እና 7/08/12 05/03/19 በቁጥር 08/ABO/12 በተፃፉ ሁለት ደብዳቤዎች የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በፓርቲው ሊቀመንበር በአቶ ዳውድ ኢብሳ ላይ የእግድ ውሣኔ አስተላልፏል ሲሉ ለቦርዱ በማሳወቅ ቦርዱ ውሳኔውን እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፡፡

Share this post

ሚዲያዎች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዝግጅትን ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጎብኝተዋል

ሚዲያዎች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዝግጅትን ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባዘጋጀው የሚዲያዎች ጉብኝት የምርጫ ኦፕሬሽን በቀድሞ ምርጫዎች እንዴት እንደነበረ እና አሁን የሚኖረው ሂደት ምን እንደሚመስል ገለፃ ተደርጓል።

ሁለት የማሳያ ምርጫ ጣቢያዎችን (Sample polling stations) በመገንባት ቀጣዩ ምርጫ ከቀድሞ የሚለይበት የምርጫ ሂደት በማሳያ ቀርቧል። በመጀመሪያው ማሳያ የቀድሞ ምርጫ ሂደትና ልምዶች፣ በሁለተኛው ማሳያ በቀጣዮ ምርጫ አንድ የምርጫ ጣቢያ ምን እንደሚመስል እና ዋና ዋና ለውጦቹ ለእይታ ቀርበዋል። የሚዲያ ባለሞያዎቹ በቦሌ ካርጎ መጋዘን የሚገኘውንም የቁሳቁስ እሸጋ፣ እንዲሁም በምርጫ ክልል ደረጃ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ጄኔሬተሮችን እና ላፕቶፓችንም ጎብኝተዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት ከድምፅ መስጫ ወረቀቶች ውጪ የቀሩ ግዢዎችን ማጠናቀቁን በተለያየ ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል። 

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት ለሚዲያ አካላት ለማስጎብኘት የተደረገ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለውን ዝግጅት ለሚዲያ አካላት ማስጎብኘት ይፈልጋል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተመዘገባችሁ ሚዲያዎች በሙሉ እንድትጎበኙ ተጋብዛችኃል።

የምርጫ ቁሳቁሶቹ በከፍተኛ ጥበቃ ስር የሚገኙ በመሆናቸው አንድ ሪፓርተር እና አንድ የካሜራ ባለሞያ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር እንዲሁም የሚድያውን ስም ወደ medianebe@gmail.com የኢሜል አድራሻ እስከ ነገ እረቡ ምሽት መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም 12 ሰአት ድረስ እንድትልኩልን እንጠይቃለን። በጉብኝቱ የሚሳተፉት ስማቸው የተላለፉ ባለሞያዎች ብቻ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post

የአሜሪካ የልማት ተራድዎ ድርጅት (USAID) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለግሷል፡፡

የአሜሪካ የልማት ተራድዎ ድርጅት (USAID) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ 2,626,780,00 ብር ዋጋ ተመን ያላቸው የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለግሷል፡፡ ቁሳቁሶቹም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ የእጅ ጓንት፣ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እና የሙቀት መለኪያ ናቸው፡፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአሜሪካን የልማት ተራድኦ ድርጅት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ 

 

 

Share this post

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲፈጸምለት ለቦርዱ ያቀረበውን ጥያቄ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

 ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም 

የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ኮቪድ 19ኝን እየተከላከለ 6ኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የወሰነ በመሆኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ምርጫውን እንዲያስፈፅም፣ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ውሳኔውን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቀን” ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡ በመላ አገሪቱ በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የሚደረጉ ምርጫዎችን የማስፈፀም ስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 102 (1) ላይ ተደንግጓል ፡፡ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የቦርዱን ስልጣን እና ሀላፊነት የወሰነው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 በአንቀጽ 7.1 ይህ የቦርዱ ስልጣን በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ምርጫዎች እና ህዝበ ውሳኔዎችን በሙሉ እንደሚሸፍን በተብራራ ሁኔታ ገልጾታል።

Share this post

የድምጽ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ነው

ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሃሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊያከናውነው አቅዶ ለነበረው አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ለድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ግዥን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቀድመው ወደመጋዘን ከገቡት የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ይገኛል፡፡ ለድምጽ መስጫ ቀን የተገዙ ቁሳቁሶች 

1. ከግልጽ የሆነ ድምጽ መስጫ ሳጥን - 213,622
2. የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያ - 156,600 
3. የድምጽ መስጫ ቀን የአስፈጻሚዎች ቁሳቁስ- 58,400 
4. ልዩ የምርጫ ቁሳቁሶች ማሸጊያ ፕላስቲክ ( plastic seal)  እና የእሸጋ ስራ ስቲከሮች - 798,300 

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ንብረት እንዲያጣሩ ሁለት ኦዲተሮችን ሾመ

ሰኔ 6 ቀን 2012 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ጥር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ኢሕአዴግ እንዲፈርስ እንዲሁም የቀድሞ ሶስቱ የግንባሩ አባላት ወራሽ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሐት) በስድስት ወር ውስጥ የንብረት ክፍፍል ተጠናቆ እንዲያቀርቡ ክፍፍሉም የሶስት ፓርቲዎች ወራሽ የሆነው ብልፅግና የሃብቱን ሶስት አራተኛ (3/4) በራሱ ህጋዊ እውቅና ያለው ህወሃት አንድ አራተኛ ( ¼) እንዲወስዱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በውሳኔውም ፓርቲዎቹ የጋራ ንብረት አጣሪ ሾመው የባለመብቶችን (creditors) መብት እንዲጠበቅ እንዲሁም በተገለጸው ቀመር መሰረትም የንብረት ክፍፍሉ እንዲፈጸም ወስኖ አሳውቆ ነበር፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ ያቀረበው ጥናት

ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ለህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ ያቀረበው ጥናት ከስር ማግኘት ይቻላል፡፡

ጥናቱ ቦርዱ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች፣ አሁን እየሰራቸው ያሉ ስራዎች እና ለወደፊቱ ለማድረግ የሚችላቸውን አማራጮች ያቀረበበት ሲሆን እነዚህ ጥናቱ ላይ የተጠቀሱ ሁኔታዎች ወደፊት በሚያጋጥሙ አዳዲስ ሁኔታዎች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት በሚገኙ ግብአቶች ሊቀየሩ የሚችሉ ናቸው፡፡

ከጥናቱ ጋር ተያይዞም ከድሮው የጊዜ ሰሌዳ አንጻር አዳዲስ ጊዜ ሰሌዳ አማራጭችም የቀረቡ ሲሆን ይህም ለጉባኤው ውሳኔ እንዲሁም በአጠቃላይ የምርጫ ኦፕሬሽንን ለመረዳት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡