Skip to main content

ጥያቄ - ከድጋሚ ድምጽ መስጠት ጋር የተያያዙ ስጋቶች እንዴት ይታያሉ?

መልስ - አንድ ሰው አንድ ቦታ በመራጭነት ለመመዝገብ በምርጫ ጣቢያው ነዋሪነቱን ተረጋግጦ ሲሆን መስፈርቱን አሟልቶ ለመመዝገቡ ደግሞ የመራጭነት መታወቂያ መያዝ አለበት። በአካባቢው ነዋሪ ያልሆነ መራጭ ተመዝግቧል የሚል ጥርጣሬ ካለ የመራጮች ምዝገባ መዝገብ በየምርጫ ጣቢ

ጥያቄ - የአዲስ አበባና የድሬዳዋ መስተዳደር ድምፅ መስጫ ቀን በተለያየ ቀን መሆኑ ምን ጥቅም አለው?

መልስ - ምርጫ አስፈጻሚዎች ለአንድ ምርጫ ክልል (constituency) ብቻ ደምረው ሪፓርት ያደርጋሉ፣ ይህም የውጤት ስህትት እንዳይፈጠር ያደርጋል፤ ድምፅ ሰጪዎች ያለምንም መምታታት ድምፅ መስጠት ይችላሉ፤ የምርጫ ታዛቢዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም የፓርቲ ወኪሎች አዲስ አበባ እና

ጥያቄ - የአዲስ አበባና የድሬዳዋ መስተዳደር ድምጽ አሰጣጥ እና ቆጠራው በአንድ ቀን ቢደረግ ችግሩ ምንድነው?

መልስ - ድምጽ ሰጪዎች ድምጽ የሚሰጡበት የምርጫ ክልሎች የተለያዩ በመሆናቸው በድምጽ አሰጣጥ ወቅት መምታታትን ያስከትላል፤ ምርጫ አስፈጻሚዎች ውጤት ቆጥረው ወደሚመለከተው የምርጫ ክልል የሚልኩ ሲሆን በአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ግን ለሁለት እና ለሶስት ምርጫ ክልሎች ውጤትን አከፋፍለው እንዲልኩ ይገደዳሉ ይህም በውጤቱ ድመራ ላይ መምታታት ሊያመጣ ይችላል፣ የምርጫውን አፈጻጸምም አስቸጋሪ ያደርገዋል፤ ምርጫ አስፈጻሚዎች ለተለያዩ የምርጫ ክልሎች ውጤትን በታትነው እንዲልኩ የተለየ የቆጠራ እና የውጤት ሪፓርት አደራረግ ስልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል ይህም ተጨማሪ የኦፕሬሽን ጫና ከመሆኑም በላይ ለዚህ የተለየ ህትመቶችን የማዘጋጀት ተጨማሪ ጫና ያስከትላል። 

የተሳትፎ ጥሪ - በምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን 6ተኛ አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የተለያዩ መመሪያዎችን በማጽደቅ ላይ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ ከነዚህም መመሪያዎች መካከል አንዱ በምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ 19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ ነው፡፡ የዚህ መመሪያ ዋና ዓላማ በምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ 19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር በቅድመ ምርጫ፣ በድምጽ መስጫ ቀን እና በድህረ-ምርጫ ወቅት ከምርጫ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተግባራት ሁሉ የኮቪድ 19 ስርጭትን እንዳይጨምሩ ማድረግ ነው፡፡ ለቦርዱ እና በምርጫ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የምርጫ አስፈፃሚ አካላት በሙሉ ሊሟሉላቸው የሚገቡ ሁሉም የኮቪድ 19 አስፈላጊ መስፈርቶች የዚህ ረቂቅ መመሪያ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረገ። መድረኩ የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ብርቱካን ሚደቅሳ ባደረጉት ንግግር የተከፈተ ሲሆን፤ በንግግራቸውም የፓርቲዎቹን መገኘት አመስግነው፤ ፓርቲዎቹ በረቂቅ መመሪያዎቹ ላይ የላቸውን ገንቢ አስተያየቶች እንዲያካፍሉ ጥሪ አድርገዋል። ረቂቅ መመሪያዎቹ ቦርዱ በኢትዮጲያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 4 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፤ የድምፅ አሰጣጥን፣ ቆጠራንና የምርጫ ውጤት አገላለጽ ሂደት አፈጻጸምን ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ፤ እንዲሁም የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ የዕጩ ወኪሎች፣ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች፣ የሀገር ውስጥና የዓለም ዐቀፍ ታዛቢዎች በነዚኽ ሂደቶች ላይ ወጥነት ያለው አሠራር እና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ተብሎ የረቀቁ ሲሆን፤ ይኽንንም የመድረኩ አቅራቢ የሆኑት ጌታቸው አሰፋ (ዶ/

Share this post

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ- ዳታ ኢንትሪ ኦፕሬተር፦ የአይሲቲ ቴክኒክ ኃላፊ፦ የዞን የምርጫ አስተባባሪ እና ምክትል የዞን የምርጫ አስተባባሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኤቢኤች ፓርትነርስ ቀጣሪነት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በነዚህ የስራ መደቦች ላይ ለማመልከት ፍላጎት ያላችሁ እና መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ከስር የሚገኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን 6ተኛ አገራዊ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የቦርዱ አመራሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት የመጪውን 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ አስመልክቶ አጠቃላይ የተሠሩ ሥራዎችና በመሠራት ላይ ያሉትን ሥራዎች ይፋ አድርጓል። የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ብርቱካን ሚደቅሳና የቦርዱ አመራር የሆኑት ብዙወርቅ ከተተ አጠቃላይ የቦርዱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስልና የመጪውን ምርጫ ሂደት የተቀላጠፈና የዘመነ ለማድረግ የተሠሩ ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ፤ በሂደቱም የነበሩት ተግዳሮቶች በዝርዝር አቅርበዋል። ቦርዱ መመሪያዎቹን አካታች ለማድረግም ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ እንደሠራባቸው ያስገነዘበ ሲሆን ቦርዱ በአጠቃላይ እንቀስቃሴዎቹ በሚያጋጥሙት ተግዳሮቶች ተስፋ የሚቆርጥ ሣይሆን የሚቻለውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝቧል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የብሔረሰብ ጥናት ኢንስትቲዩት መዛግብትን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ አስረክቧል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ታኅሣሥ 12 ቀን 2013 ዓ.ም የብሔረሰብ ጥናት ኢንስትቲዩት መዛግብትን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ አስረክቧል። ቦርዱ በቀድሞው መንግሥት አስተዳደር በመጋቢት 1975 ዓ.ም የተቋቋመውን የብሔረሰቦችን ጉዳይ የሚያጠናውን ተቋም ሠነዶች ወርሶ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን፤ በወቅቱ በተቋሙ የተሠሩ ጥናቶች አምስት የተለያዩ ዘርፎች ማለትም

• የታሪክ፣ የባሕልና የቋንቋ ጥናት
• የማኅበራዊ ዘርፍ
• የአስተዳደር ጥናት ቡድን
• የኢኮኖሚ ጥናት ቡድን እና
• የሕገ-መንግሥት ጥናት ቡድን ያካተተ ነበር።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በረቂቅ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሥርዓተ- ፆታ ኦዲት ሠነድ ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በረቂቅ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሥርዓተ- ፆታ ኦዲት ሠነድ ላይ ግብዓት ለመሰባሰብ የሚያስችለውን መድረክ፤ ሁሉም የቦርዱ አመራሮች እንዲሁም የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች በተገኙበት አካሂዷል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ዋና ሠብሳቢ የሆኑት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ኦዲቱ ያለንበትን የምናውቅበት ብቻ ሣይሆን ለምን እዛ ሆንን ብለን የምንጠይቅበት ጭምር ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

Share this post

የኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዓለም ዐቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃትና የአካል ጉዳተኝነት ቀንን አስመልክቶ ሁለት ተከታታይ የምክክር መድረኮችን አከናወነ

የኢትየጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአካታችነት እና ስርአት ጾታ የስራ በዚህ ሳምንት ሁለት ተከታታይ ሁነቶችን አካሂዷል፡፡ ሀሙስ ታኅሳስ 01 ቀን 2013 ዓ.ም የተካሄደው የምክክር መድረክ ዓለም ዐቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀንን የተመለከተ ሲሆን፤ የተለያዩ ፓርቲዎች ተወካዮችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈውበታል፡፡ የቦርድ አመራር በሆኑት አቶ ውብሸት አየለ የመክፈቻ ንግግር የተከፈተው መድረክ፤ የምርጫና የሥርዓተ ፆታ አማካሪ በሆኑት ጨረር አክሊሉና የኢትዮጲያ የሴቶች ማኅበር ተወካይ በሆኑት ኅብረት አባሆይ የፆታዊ ጥቃትን ከዓለም ዐቀፍ ተሞክሮ አንጻር የሚያሳዩ ጽሑፎች የቀረቡበት ሲሆን በምርጫ ዑደት ጊዜ የሚያጋጥሙ ፆታዊ ጥቃት ምን መልክ አላቸው የሚለው በዋና አጀንዳነት ተነስቶበታል። በቀረበው ጽሑፍ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር በሆኑት ብዙወርቅ ከተተ፣ እና በጽሑፍ አቅራቢዎች መሪነት ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተውበታል፡፡ በዛሬው ዕለት የተካሄደው ሁለተኛው መ

Share this post