Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል እና ሰራተኞች የጋና ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን ተከታተሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር ፍቅሬ ገብረህይወት የተመራው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰራተኞች ቡድን የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን፣ የድምጽ መስጫ ቀን የተደረጉ ተግባራትን፣ የኮቪድ ወረርሽን በመከላከል የተከናወነውን የድምጽ መስጠት ሂደት ተከታትለዋል፡፡

በአራት ቀናት ቆይታቸውም ምርጫን የኮቪድ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ለማከናወን የተደረጉ ተግባራትን፣ የምርጫ አስፈጻሚው ተቋምን አሰራር፣ የምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት ቆጠራ፣ ድመራ እና ይፋ ማድረግን የተከታተሉ ሲሆን ከጋና ምርጫ ኮሚሽን አመራር አካላትም ጋር ተነጋግረዋል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልኡካን ምርጫውን ከመታዘብም በተጨማሪ በተለይ በኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ ሆኖ ምርጫ ማከናወን የሚያስፈልጉትን የበጀት እና የሎጄስቲክስ ዝግጅቶችን ከጋና ምርጫ ልምድ መቅሰም ችለዋል፡፡

የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 መካሄዱ ይታወሳል፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክሮችን አከናወነ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/ 2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ከመጽደቃቸው በፊት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ምክክሮችን እያደረገ ይገኛል፡፡ የምክክሮቹ አላማ በባለድርሻ አካላት የሚሰጡ ግብአቶችን ለማካተት እና መመሪያዎቹንም ለማስተዋወቅ ሲሆን ባለፈው አርብ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰአት ድልድል መመሪያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ የአየር ሰአት ድልድል ቀመር፣ ድልድሉ ከዚህ በፊት የተካሄደበት መንገድ እና የድልድሉ ማከናወኛ ቴክኖሎጂ በቦርዱ እና በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አማካኝነት ቀርበዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቦርዱ ያወጣቸውን መመሪያዎች አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለሁለት የተለያዩ ቀናት ያደረገውን ምክክር አጠናቀቀ

ሕዳር 03 እና 04 ቀን 2013 አም በተከናወኑት ምክክሮች ውይይት የተደረገባቸው መመሪዎች

- የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ
-የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ
-የምርጫ ውድድር ቅስቀሳ ስነ ምግባር መመሪያ
-የአለምአቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣ የአሠራር ሥርዓት እና የሥነ ምግባር መመሪያዎች ሲሆኑ ፓለቲካ ፓርቲዎች ከህግ፣ ከልምድ እና ከቀድሞ አሰራሮች በመነሳት የተለያዩ ግብአቶችን ሰጥተዋል፡፡

ምክክሩ ቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎችን ግብአት ለማካተት ከሚያደርጋቸው ተከታታይ ምክክሮች መካከል አንዱ ሲሆን በተከታዩ ሳምንትም በሌሎች መመሪያዎች ላይ በሚደረግ ውይይት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለተከታታይ ቀናት ሲያደርገው የነበረው ምክክር ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲያደርግ የነበረውን ውይይት ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ በውይይቱ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች፣ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ተገኝተዋል፡፡ በምክክር መድረኩ የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች የኮቪድ ወረርሽኝ ውስጥ በሚደረግ ምርጫ ዋና ዋና ዝግጅቶች ምን ይመስላሉ? ከባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል? የቦርዱስ ዝግጅት ምን ይመስላል? ዋና ዋና የምርጫ ተግባራት መቼ ይደረጋሉ? የምርጫ የጸጥታ ችግሮችስ እንዴት መታየት አለባቸው የሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስለመጪው አገራዊ ምርጫ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው አገራዊ ምርጫ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን አስመልክቶ ባሳለፍነው ሳምንት ከመንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ወቅት የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን ከእያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሚጠበቁ ዋና ዋና ትብብሮች ምን መሆን እንዳለባቸው ውይይት እና ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ተቋማት የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን እና የማእከላዊ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን ሲሆኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይቱን አስተባብሯል፡፡ በውይይቱ መሰረትም

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የገንዘብ ሚኒስቴር - በኮቪድ ወረርሽኝ ውስጥ የሚከናወን ምርጫ በመሆኑ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ በጀት በወቅቱ መልቀቅ፤ እና ለምርጫ አስፈጻሚዎች የግል መከላከለያ ቁሳቁሶች (PPE) ግዥ እና አቅርቦትን አስመልክቶ ልዩ እገዛ ማድረግ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ኦፕሬሽን ዝግጅቱን እና የፓርቲዎች ማእከልን ለፓለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት አስጎበኘ

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራር አባላት ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው ጉብኝት ላይ የተገኙ ሲሆን በምስረታ ላይ ያለው የሴት ፓለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት አባላትም ተሳታፊ ነበሩ፡፡

የምርጫ ኦፕሬሽን በቀድሞ ምርጫዎች እንዴት እንደነበረ እና የመጪው ምርጫ የሚኖረውን ሂደት ለማሳያነት የተዘጋጁ ምርጫ ጣቢያዎችን እና የምርጫ ቁሳቁስ መጋዘኖችን ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ቦርዱ ለፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት እና ለሴት ፓለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት ያዘጋጀውን ለተለያዩ የቢሮ ስራ እና ስብሰባዎችን ለማከናወን የሚውል የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ለፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና የሴት ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት አስረክቧል፡፡

Share this post

የመራጮችን ትምህርት ለማስተማር ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ፈቃድ መጠየቂያ ላቀረባችሁ የሲቪክ ማህበራት እና ትምህርት ተቋማት በሙሉ

 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዶክመንቶችን ማሟላት ያለባቸውን ሲቪል ማህበራት አስመልክቶ የሚከተለውን ጥሪ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲያስነግር ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በሚዲያ የተደረገውን ጥሪ ያልሰማችሁ እና የመራጮች ትምህርት ለማስተማር ማመልከቻ አስገብታችሁ የነበራችሁ ሲቪል ማህበራት ማስታወቂያውን ከስር ማግኘት ትችላላችሁ፡፡