ጥያቄ - የቦርዱ ስራ ከዚህ በኃላ ምን ይሆናል?
መልስ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ሰራተኞቹ ከቤት ሆነው የቀረው ደግሞ በፈረቃ ስራውን በማከናውን ላይ ሲሆን መሰብሰብ የማያስፈልጋቸው ስራዎቹን ማህበራዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩ፣ሁኔታው ተቀይሮ ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ ሲመለስ በተገቢው ሁኔታ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያሥችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ ይቆያል፡፡ በዚህም መሰረት የፓለቲካ ፓርቲዎቸን ዲጂታል ኮምኒኬሽን መረጃ እየሰበሰበ ይገኛል፡፡ ከፓርቲዎች ጋር የሚኖረው ግንኙነትም በተቻለ መጠን በዲጂታል መንገድ ለማድረግ ጥረት ያደርጋል፡፡