Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች ለቀረቡለት አቤቱታዎች ምላሽ ሰጠ

የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ፓለቲካ ፓርቲዎች ከመመዝገብ በተጨማሪ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሰሞኑን ከተለያዩ ፓርቲዎች የቀረበለትን አቤቱታ አስመልክቶ ምላሾችን ሰጥቷል። በዚህም መሠረት፣ አቤቱታ ያቀረቡ ፓርቲዎች እና ያቀረቧቸው አቤቱታዎች፦

1. ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ትዴፓ/ - እስር፣ ማስፈራራትና ቢሮ መዘጋት፣

2. ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ / - ስብሰባዎች መሰናከል፣ በጎንደር በደብረብርሃን እና የጸጥታ ኃይሎች ለመሰናከሉ ትብብር ማድረጋቸው፣

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ጋር ምክክር አካሄደ

የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም.                                                                                                          

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ሂደት ስላላቸው ተሳትፎ እንዲሁም ስለ አዲሱ የምርጫ ህግ አካታችነት ከቦርዱ አመራሮችና ሠራተኞች፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተወጣጡ ሠራተኞች፣ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢአጉብማፌ) እንዲሁም ከተለያዩ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ተወካዮች ጋር ምክክር እያካሄደ ይገኛል።
በምክክሩ ከተነሱት ዋና ዋና ሀሳቦች መካከል፦

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ትምህርትና ምርጫ መታዘብ ዙሪያ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት አከናወነ

የካቲት 7 ቀን 2012 ዓ.ም.       

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ትምህርትና ምርጫ መታዘብ ዙሪያ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት እያከናወነ ይገኛል። የውይይቱ ዋና ዋና ዓላማዎች የመራጮች ትምህርት እና ምርጫ መታዘብ ላይ ያለውን ልምድ መዳሰስ፣ የመራጮች ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥና የሥነ ምግባር መመሪያ ላይ የተሰጡትን ግብአቶች ማስተዋወቅና ማወያየት፣ የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሰራርና ሥነ ምግባር መመሪያ ላይ ውይይት ማድረግ ናቸው።

በውይይቱ ላይ የሲቪል ማህበራት ተወካዮች የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔን ጨምሮ የተለያዩ የቀድሞ ልምዶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ይህ ምክክር መድረክ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት ብቻ ካደረጋቸው ውይይት መድረኮች ሶስተኛው ነው።

Share this post

የምርጫ ቦርድ አዲሱ የምርጫ ህግ፣ መመሪያዎች፣ ህጋዊ ማዕቀፍ ነክ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል

የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም.    

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ እያከናወነ ያለውን ተቋማዊ ግልጽነትን እና ተአማኒነትን የሚያሳዩ እንዲሁም የተቋም ማንነት ለውጥን የሚወክሉ መገለጫዎችን በማካተት የተቋሙን አዲስ አርማ አዘጋጅቷል። ይህም አርማ የተዘጋጀው የቦርዱን ግልጽነት በሚያሳይ እና አንድ ወጥ የሆነ የተቋም ማንነት ምስል በሚፈጥር መልኩ ነው። የዛሬው ስብሰባ አንዱ ዓላማም ይህንኑ የቦርዱን አዲስ አርማ ለባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለሕዝብ ማስተዋወቅ ነው።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲሱን አርማ ለሕዝብ ይፋ አደረገ

የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም.

የኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ የሚያደርገው ውይይት ከመስከረም 27 እና 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ከተደረገው የመጀመሪያው የባለድርሻ አካላት ኮንፈረንስ ቀጣይ ሲሆን የውይይቱም ዋና ዓላማ የመጪው አገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ማድረግ፣ ስለ ምርጫ ቦርዱ የሥራ እንቅስቃሴዎች እና ስለ 2012 አጠቃላይ ምርጫ ዝግጅት መረጃ ማካፈል፣ የምርጫ ዋና ዋና ተሳታፊዎች እና የትብብር ኃላፊነቶች እንዲሁም ስለቦርዱ ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት ማድረግ ነው።

Share this post

​​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከካናዳ መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም "የምርጫ ሥራ ድጋፍ ፕሮጄክት" የተሰጠውን ድጋፍ ዛሬ በጋራ ተፈራርሟል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከካናዳ መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም "የምርጫ ሥራ ድጋፍ ፕሮጄክት" የተሰጠውን ድጋፍ ዛሬ በጋራ ተፈራርሟል። በፊርማ ሥነ ስርዓቱ የቦርዱ አመራር አባላት ብዙወርቅ ከተተ እና አበራ ደገፋ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ) ህጋዊ ሰውነት ማጣትን በተመለከተ ውሳኔ ሰጠ

ኢህአዴግ በሊቀመንበሩ በኩል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ ግንባሩ መፍረሱን ለቦርዱ ያሳወቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) በሊቀመንበሩ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ ግንባሩ በመፍረሱ የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄ አቅርበዋል። የግንባርን መፍረስ የመወሰን ሥልጣን የቦርዱ በመሆኑ ግንባሩም ሆነ ህወሃት ግንባሩ መፍረሱን መጥቀሳቸው የማይገባ ቢሆንም ቦርዱ ሁለቱ ሊቀመንበራት ያቀረቧቸውን የጽሁፍ ጥያቄዎ መሠረት በማድረግ ግንባሩ መፍረስ አለበት ወይ?

Share this post