የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክሮችን አከናወነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/ 2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ከመጽደቃቸው በፊት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ምክክሮችን እያደረገ ይገኛል፡፡ የምክክሮቹ አላማ በባለድርሻ አካላት የሚሰጡ ግብአቶችን ለማካተት እና መመሪያዎቹንም ለማስተዋወቅ ሲሆን ባለፈው አርብ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰአት ድልድል መመሪያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ የአየር ሰአት ድልድል ቀመር፣ ድልድሉ ከዚህ በፊት የተካሄደበት መንገድ እና የድልድሉ ማከናወኛ ቴክኖሎጂ በቦርዱ እና በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አማካኝነት ቀርበዋል።