Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረገ። መድረኩ የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ብርቱካን ሚደቅሳ ባደረጉት ንግግር የተከፈተ ሲሆን፤ በንግግራቸውም የፓርቲዎቹን መገኘት አመስግነው፤ ፓርቲዎቹ በረቂቅ መመሪያዎቹ ላይ የላቸውን ገንቢ አስተያየቶች እንዲያካፍሉ ጥሪ አድርገዋል። ረቂቅ መመሪያዎቹ ቦርዱ በኢትዮጲያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 4 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፤ የድምፅ አሰጣጥን፣ ቆጠራንና የምርጫ ውጤት አገላለጽ ሂደት አፈጻጸምን ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ፤ እንዲሁም የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ የዕጩ ወኪሎች፣ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች፣ የሀገር ውስጥና የዓለም ዐቀፍ ታዛቢዎች በነዚኽ ሂደቶች ላይ ወጥነት ያለው አሠራር እና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ተብሎ የረቀቁ ሲሆን፤ ይኽንንም የመድረኩ አቅራቢ የሆኑት ጌታቸው አሰፋ (ዶ/

Share this post

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ- ዳታ ኢንትሪ ኦፕሬተር፦ የአይሲቲ ቴክኒክ ኃላፊ፦ የዞን የምርጫ አስተባባሪ እና ምክትል የዞን የምርጫ አስተባባሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኤቢኤች ፓርትነርስ ቀጣሪነት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በነዚህ የስራ መደቦች ላይ ለማመልከት ፍላጎት ያላችሁ እና መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ከስር የሚገኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን 6ተኛ አገራዊ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ታኅሣሥ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የቦርዱ አመራሮችና ፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት የመጪውን 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ አስመልክቶ አጠቃላይ የተሠሩ ሥራዎችና በመሠራት ላይ ያሉትን ሥራዎች ይፋ አድርጓል። የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ብርቱካን ሚደቅሳና የቦርዱ አመራር የሆኑት ብዙወርቅ ከተተ አጠቃላይ የቦርዱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስልና የመጪውን ምርጫ ሂደት የተቀላጠፈና የዘመነ ለማድረግ የተሠሩ ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ፤ በሂደቱም የነበሩት ተግዳሮቶች በዝርዝር አቅርበዋል። ቦርዱ መመሪያዎቹን አካታች ለማድረግም ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ እንደሠራባቸው ያስገነዘበ ሲሆን ቦርዱ በአጠቃላይ እንቀስቃሴዎቹ በሚያጋጥሙት ተግዳሮቶች ተስፋ የሚቆርጥ ሣይሆን የሚቻለውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝቧል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የብሔረሰብ ጥናት ኢንስትቲዩት መዛግብትን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ አስረክቧል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ታኅሣሥ 12 ቀን 2013 ዓ.ም የብሔረሰብ ጥናት ኢንስትቲዩት መዛግብትን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ አስረክቧል። ቦርዱ በቀድሞው መንግሥት አስተዳደር በመጋቢት 1975 ዓ.ም የተቋቋመውን የብሔረሰቦችን ጉዳይ የሚያጠናውን ተቋም ሠነዶች ወርሶ እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን፤ በወቅቱ በተቋሙ የተሠሩ ጥናቶች አምስት የተለያዩ ዘርፎች ማለትም

• የታሪክ፣ የባሕልና የቋንቋ ጥናት
• የማኅበራዊ ዘርፍ
• የአስተዳደር ጥናት ቡድን
• የኢኮኖሚ ጥናት ቡድን እና
• የሕገ-መንግሥት ጥናት ቡድን ያካተተ ነበር።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በረቂቅ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሥርዓተ- ፆታ ኦዲት ሠነድ ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በረቂቅ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሥርዓተ- ፆታ ኦዲት ሠነድ ላይ ግብዓት ለመሰባሰብ የሚያስችለውን መድረክ፤ ሁሉም የቦርዱ አመራሮች እንዲሁም የፓለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች በተገኙበት አካሂዷል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ዋና ሠብሳቢ የሆኑት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ኦዲቱ ያለንበትን የምናውቅበት ብቻ ሣይሆን ለምን እዛ ሆንን ብለን የምንጠይቅበት ጭምር ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

Share this post

የኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዓለም ዐቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃትና የአካል ጉዳተኝነት ቀንን አስመልክቶ ሁለት ተከታታይ የምክክር መድረኮችን አከናወነ

የኢትየጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአካታችነት እና ስርአት ጾታ የስራ በዚህ ሳምንት ሁለት ተከታታይ ሁነቶችን አካሂዷል፡፡ ሀሙስ ታኅሳስ 01 ቀን 2013 ዓ.ም የተካሄደው የምክክር መድረክ ዓለም ዐቀፍ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀንን የተመለከተ ሲሆን፤ የተለያዩ ፓርቲዎች ተወካዮችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈውበታል፡፡ የቦርድ አመራር በሆኑት አቶ ውብሸት አየለ የመክፈቻ ንግግር የተከፈተው መድረክ፤ የምርጫና የሥርዓተ ፆታ አማካሪ በሆኑት ጨረር አክሊሉና የኢትዮጲያ የሴቶች ማኅበር ተወካይ በሆኑት ኅብረት አባሆይ የፆታዊ ጥቃትን ከዓለም ዐቀፍ ተሞክሮ አንጻር የሚያሳዩ ጽሑፎች የቀረቡበት ሲሆን በምርጫ ዑደት ጊዜ የሚያጋጥሙ ፆታዊ ጥቃት ምን መልክ አላቸው የሚለው በዋና አጀንዳነት ተነስቶበታል። በቀረበው ጽሑፍ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር በሆኑት ብዙወርቅ ከተተ፣ እና በጽሑፍ አቅራቢዎች መሪነት ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተውበታል፡፡ በዛሬው ዕለት የተካሄደው ሁለተኛው መ

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል እና ሰራተኞች የጋና ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን ተከታተሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር ፍቅሬ ገብረህይወት የተመራው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰራተኞች ቡድን የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን፣ የድምጽ መስጫ ቀን የተደረጉ ተግባራትን፣ የኮቪድ ወረርሽን በመከላከል የተከናወነውን የድምጽ መስጠት ሂደት ተከታትለዋል፡፡

በአራት ቀናት ቆይታቸውም ምርጫን የኮቪድ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ለማከናወን የተደረጉ ተግባራትን፣ የምርጫ አስፈጻሚው ተቋምን አሰራር፣ የምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት ቆጠራ፣ ድመራ እና ይፋ ማድረግን የተከታተሉ ሲሆን ከጋና ምርጫ ኮሚሽን አመራር አካላትም ጋር ተነጋግረዋል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልኡካን ምርጫውን ከመታዘብም በተጨማሪ በተለይ በኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ ሆኖ ምርጫ ማከናወን የሚያስፈልጉትን የበጀት እና የሎጄስቲክስ ዝግጅቶችን ከጋና ምርጫ ልምድ መቅሰም ችለዋል፡፡

የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 መካሄዱ ይታወሳል፡፡

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጃቸው የተለያዩ መመሪያዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክሮችን አከናወነ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1162/ 2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተለያዩ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ከመጽደቃቸው በፊት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ምክክሮችን እያደረገ ይገኛል፡፡ የምክክሮቹ አላማ በባለድርሻ አካላት የሚሰጡ ግብአቶችን ለማካተት እና መመሪያዎቹንም ለማስተዋወቅ ሲሆን ባለፈው አርብ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ የአየር ሰአት ድልድል መመሪያ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ የአየር ሰአት ድልድል ቀመር፣ ድልድሉ ከዚህ በፊት የተካሄደበት መንገድ እና የድልድሉ ማከናወኛ ቴክኖሎጂ በቦርዱ እና በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አማካኝነት ቀርበዋል።

Share this post

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቦርዱ ያወጣቸውን መመሪያዎች አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለሁለት የተለያዩ ቀናት ያደረገውን ምክክር አጠናቀቀ

ሕዳር 03 እና 04 ቀን 2013 አም በተከናወኑት ምክክሮች ውይይት የተደረገባቸው መመሪዎች

- የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ
-የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ
-የምርጫ ውድድር ቅስቀሳ ስነ ምግባር መመሪያ
-የአለምአቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ፍቃድ አሰጣጥ፣ የአሠራር ሥርዓት እና የሥነ ምግባር መመሪያዎች ሲሆኑ ፓለቲካ ፓርቲዎች ከህግ፣ ከልምድ እና ከቀድሞ አሰራሮች በመነሳት የተለያዩ ግብአቶችን ሰጥተዋል፡፡

ምክክሩ ቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎችን ግብአት ለማካተት ከሚያደርጋቸው ተከታታይ ምክክሮች መካከል አንዱ ሲሆን በተከታዩ ሳምንትም በሌሎች መመሪያዎች ላይ በሚደረግ ውይይት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post