የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23 ቀን 2014 ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር በአዋጅ ቁጥር 1162/11 እና በመመሪያ ቁጥር 3/2011 መሠረት ከ6ተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ በምክክሩ ወቅትም ለፓርቲዎች መገለጹ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው እለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ ከስር ስማችሁ የተዘረዘረ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንድታስገቡ እናሳስባለን።

አገራዊ ፓርቲዎች

  1. የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ
  2. የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ
  3. የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ
  4. ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
  5. የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ
  6. አዲስ ትውልድ ፓርቲ
  7. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
  8. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
  9. ብልፅግና ፓርቲ
  10. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ
  11. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
  12. ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
  13. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ

ክልላዊ ፓርቲዎች

  1. የሲዳማ አርነት ንቅናቄ
  2. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
  3. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
  4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
  5. ኅዳሴ ፓርቲ
  6. የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
  7. የአፋር ሕዝቦች ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
  8. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ
  9. ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
  10. ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ ሉዓላዊነት
  11. የአርጎባ ብሔረ ሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
  12. የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
  13. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

ማስታወቂያ
የካቲት 09 ቀን 2014 ዓ.ም