የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሥሩ ለሚገኙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ጀማሪ ባለሙያዎችን /Intern/ በኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
በዚሁም መሠረት
- በህግ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ፣ በሶሺዎሎጂ፣ ሶሻል ወርክ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በሰው ኃብት አስተዳደር፣ በቢዝነስ ሊደርሺፕ፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በግዢ እና ንብረት አስተዳደር፣ በጋዜጠኝነት እና ስነጽሁፍ፣ በግራፊክስ ዲዛይን፣ በፖለቲካል ሳይንስ እና አለምአቀፍ ግንኙነት እንዲሁም ተያያዥ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው/ያላት
- አማካይ የመመረቂያ ውጤታቸው 3.5 እና ከዛ በላይ የሆነ፤
- ጥሩ የሆነ የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ቋንቋን ክህሎት (መናገር፣ መጻፍ እና ማንበብ) ያለው/ያላት፤
- የማይክሮሶፍት ኦፊስ (MS Word, Excel, Outlook, and PowerPoint) እውቀት እና በአግባቡ የመጠቀም ችሎታ ያላት/ ያለው፤
- የተቋሙን ደንብና መመሪያ የሚያከብር/ የምታከብር፤
- የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፤
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
- ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን መናገር፣መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉ አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ