የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል በ6 ዞን እና በ5 ልዩ ወረዳዎች ላይ የሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሕዝበ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ ሰራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጥር ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲዮ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ አሌ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነጻ የሆናችሁ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከጥቅምት 12-20 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ እንድታመለከቱ ቦርዱ ይጠይቃል።
የምልመላ መስፈርት፡
- እድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፤
- የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፤
- መኖሪያ አድራሻ፦ ህዝበ ውሳኔው በሚካሄድበት ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች
- የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፤
- የስራ ቦታ፦ ህዝበ ውሳኔው በሚካሄድባቸው ዞን እና ልዩ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያ ነው።
- የቅጥር ጊዜ፡- ለ27 ቀናት፤
- የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን ብር 250 በድምሩ 6750 ብር ነው፤
- ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪነት በየአካባቢዎቹ በሚነገሩ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆን ይመረጣል፤
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የስራ ማስታወቂያ
ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም