Skip to main content

ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ

የቦርድ ሰብሳቢ


ሜላትወርቅ ኃይሉ በተለያዩ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶች ከ30 ዓመታት በላይ በማገልገል ልምድ ያላቸው ሲሆን፤ ከባለሞያነት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ አመራርነት ሠርተዋል።

  • ነሲም አሊ e18
    ነሲም አሊ የቦርድ አባል
    ነሲም አሊ በመንግሥት ሥራ (በሕዝብ አገልግሎት) ለ10 ዓመት ገደማ በተለያዩ የፍርድ ቤት ዕርከኖች በዳኝነት በማገልገል ለሀገራቸው የፍትሕ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
  • አቶ ተክሊት ይመስል e18
    ተኽሊት ይመሰል የቦርድ አባል
    አቶ ተኽሊት በመንግሥት ሥራ (በሕዝብ አገልግሎት) ከ25 ዓመታት በላይ የካበተ ልምድ አላቸው፡፡ አቶ ተክሊት በነዚኽ ዓመታት የዐቃቤ ሕግ መመሪያ ኃላፊ፣ የከፍተኛ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የሠበር ሰሚ ችሎት ዋና ሰብሳቢ ዳኛ፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባል፣ እንዲሁም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል፡፡
  • አቶ ተስፋዬ ንዋይ e18
    ተስፋዬ ንዋይ የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ
    አቶ ተስፋዬ ነዋይ በመንግሥት ሥራ (በሕዝብ አገልግሎት) ከ17 ዓመታት በላይ ማለትም በዐቃቤ ሕግነት፣ በሰብሳቢ ዳኝነት፣ በሕግ ጉዳዮች ተመራማሪነት እንዲሁም በዩንቨርስቲ መምህርነት አገልግለዋል፡፡ የኢትዮጵያ
  • በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬትና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች

    ጥር 13 ቀን 2012 ዓ.ም.   

    በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬትና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፦

    1. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣
    2. አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣
    3. አማራ ጊዮናዊ ንቅናቄ፣
    4. እናት ፓርቲ፣

    አገው ብሔራዊ ሸንጎ እና ብልጽግና ፓርቲም የሙሉ እውቅና ምዝገባ ፈቃድ ማግኘታቸው ይታወሳል። ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ምንድነው?

    Share this post

    ጨረታ

    የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ለሚቀጥለው ብሔራዊ ምርጫ በተለያየ መልኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠ ፍቃድ የሚከተሉት አገልግሎትና አቅርቦት ላይ ለመስራት አቅምና ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶችን የማሰባሰቢያ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ በመሆኑም ከስር በሚገኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ዝርዝሩን መመልከት እና ማመልከት ትችላላችሁ፡፡  

    ማስታወቂያውን በሪፓርተር፣ በፎርቹን፣ በአዲስ ዘመን እንዲሁም በካፒታል ጋዜጣ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

    ለሚዲያዎች በሙሉ መረጃ ማስተካከያ

    ታኅሣሥ 28 ቀን 2012 ዓ.ም.    

    የተለያዮ የመንግሥትና የግል ሚዲያዎች የቀጣዮ ብሔራዊ ምርጫ ቀን ሰኔ 21 (June 28) ነው የሚል መረጃ ደርሶናል ትክክል ነው ወይ ብለው ጥያቄ እያቀረቡልን ይገኛሉ። በመሆኑም የሚቀጥለው ምርጫ ቀን ሰኔ 21 (June 28) ነው የሚለው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

    Share this post

    ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ

    ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች በሙሉ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ላካሄደው ህዝበ ውሳኔ በህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚነት የተሳተፋችሁ በሙሉ የምስክር ወረቀታችሁ ስለተዘጋጀ ሳሪስ ከሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ቅርንጫፍ ከዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በስራ ቀንና ሰአት በመገኘት የምስክር ወረቀታችሁን መውሰድ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ