የመራጮች ትምህርት መሰጠት ለሚፈልጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረበ ጥሪ

ዜጎች በምርጫ ላይ ያላቸውን ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማረጋጋጥ ብሎም ተአማኒነትን ያተረፈ ሰላማዊ ምርጫ ለማድረግ የመራጮች ትምህርት አስፈላጊነት እሙን ነው፡፡ ይህንን አላማ በአገር ደረጃ ለማሳካትም የሲቪል ማህበረሰብ ተሳትፎ ትልቅ ስፍራ ይይዛል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሀገሪቱ ሕገ መንግሥትና ቦርዱን ባቋቋመው አዋጅ ቁጥር 1133/2011 በተሠጠው ሥልጣን መሠረት የመራጮች ትምህርት ለሚሠጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ የመስጠት፤ የመከታተልና ሀላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችለውን መመሪያ አርቅቆ እንዲሁም በጉዳዩ ከሲቪል ማህበራት ወኪሎች ጋር ባደርገው ውይይት ያገኘውን ግብአት በማካተት የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና የሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 04/2012ን አጽድቋል፡፡ በመሆኑም የመራጮች ትምህርት መሰጠት ለሚፈልጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ በማድረግ ትምህርቱን ለመስጠት ብቃት ላላቸው ማህበራት ፈቃድ ሠጥቶ ማሰማራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በዚህ መሠረት፡-
• በህግ ተመዝግባችሁ የምትንቀሳቀሱ ፤የማስተማሩን ተግባር ለመወጣት የሚያስችል ብቃት ያላችሁ፤
• ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ገለልተኛ የሆናችሁ፤
• ለመራጮች ትምህርት በመመሪያው የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ እና በተለያየ ሁኔታ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት የምትፈልጉ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከቦርዱ በዝርዝር የሚጠየቁትን አግባብ ያላቸው ሰነዶችን በማያያዝ ማመልከቻችሁን ለዋናው መ/ቤት ወይም ለቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ይህ ማስታወቂያ በመገናኛ ብዙሀን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ቀናት ውስጥ እንድታቀርቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ 
አመልካቾች ከማመልከቻቸው ጋር አያይዘው የሚቀርቡአቸውን ሰነዶች ዝርዝር፣ የማመልከቻ እና ለሎች ተያያዥነት ያላቸውን ፎርሞች ከስር ከሚገኙ ማስፈንጠሪያዎች፣ ከዋናው መሥሪያ ቤት እና ከክልል ጽህፈት ቤቶች ማግኘት እንደሚቻል እየገለጽን ከዚህ በፊት ጥያቄ ያቀረባችሁ ማህበራትም ማመልከቻችሁን በመመሪያው መሰረት አሟልታችሁ ማቅረብ እንደሚገባ እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ


  የመራጮች ትምህርት መመሪያ 

   የማመልከቻ ቅጽ 

   የአሰልጣኞች መመዝገቢያ ቅጽ

የጥሪ ማስታወቂያ
መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም.