ኢትዮጵያ የምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት
ሐምሌ 10 ቀን 2011 ዓ.ም.
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈ ለባለሞያዎች ዝርዝር (Professionals roster) ውስጥ ማካተቻ ጥሪ
ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከጣልያንዋ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል በውይይቱም ወቅት የሚቀጥለውን ምርጫ አስመልክቶ በጣልያን መንግሥት እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መካከል ሊኖር ስለሚችለው ትብብር ተነጋግረዋል። ሚኒስትሯ በበኩላቸው የጣልያን መንግሥት የሚቀጥለውን ምርጫ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።
ሰኔ 13 ቀን 2011 ዓ.ም.
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በትላንትናው ዕለት ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት እና ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር በመሆን የጋራ የፕሮጄክት ሰነድ ፈርመዋል። የ40 ሚልዮን ዶላር በጀት ያለው የፕሮጄክት ሰነዱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚቀጥለውን አገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ እንዲሆን የምርጫ ቦርድን አቅም ማሳደግን ጨምሮ ለተለያዩ ከምርጫ ጋር ግንኙነት ላላቸው ተግበራት መሳካት የሚውል ሲሆን ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ጃፓን፣ ኔዘርላንድ፣ ኒውዚላድ፣ ኖርዌይ እና ስዊድን ለበጀቱ አስተዋእጾ አድርገዋል።
ሰኔ 1 ቀን 2011 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን ለመሾም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካኝነት የተቋቋመው እጩዎችን መልማይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ስምንት እጩዎችን ይፋ አድርጓል። ስምንቱ እጩዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጨረሻ ውሳኔ የቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሚቀጥሉት ሳምንታት አራቱን የቦርድ አባላት ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚዲያዎች ሚና” በሚል ርዕስ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አደረገ። ቦርዱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምክክር አውደጥናት ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡
ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተአማኒነት ያለው ተቋም ለመገንባት ካስተዋወቃቸው የተለያዩ ለውጦች መካከል አንደኛው የፓለቲካ ፓርቲዎች ውይይት (Political Parties Dialogue) አንዱ ነው፡፡ በቦርዱ አስተባባሪነት የሚካሄደው ውይይቱ የተለያዩ ውጤቶችን ያፈራ ሲሆን እስካሁን፦
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባላት ጥቆማን ለመስጠት የሚከተለውን መረጃ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በአዲሱ አዋጅ 1133/2011 መሰረት የአዳዲስ የቦርድ አባላት ምልመላ የሚመራው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በቋቋሙት እጩ ቦርድ አባላት መልማይ ኮሚቴ ነው፡፡
ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ከአውሮፓ ህብረት ተወካይና የህብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ወቅት የምርጫ ቦርድን አዲስ አደረጃጀት፣ የምርጫ ቦርዱን አዳዲስ የቦርድ አባላት ምልመላ፣ የምርጫ በጀትና የፋይናንስ ድጋፍ፣ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበውሳኔ፣ የቤትና የሕዝብ ቆጠራ መራዘም እና ከምርጫ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ የተፈናቀሉ ዜጎች እና የመምረጥ መብቶቻቸውን፣ የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሮቹ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱም የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የህብረቱ አባል አገራት ቦርዱን ተአማኒ እና ብቃት ያለው ተቋም ለማድረግና መጪው ምርጫ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ እንዲሆን የሚደረገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡፡