ነሲም አሊ


ነሲም አሊ በመንግሥት ሥራ (በሕዝብ አገልግሎት) ለ10 ዓመት ገደማ በተለያዩ የፍርድ ቤት ዕርከኖች በዳኝነት በማገልገል ለሀገራቸው የፍትሕ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ነሲም በፍርድ ቤቶች ከነበራቸው የዳኝነት ኃላፊነት አስቀድሞ በፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደር ፍ/ቤት የመንግሥት አስተዳደር ሕጎች ላይ በማተኮር አስተዳደራዊ አለመግባቶችን መፍታት ላይ አተኩሮ በሚሠራው ተቋም በዳኝነት ከማገልገላቸውም ባሻገር ሕግ ነክ ጉዳዮችን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማስተማር ልምድ አላቸው፡፡

ነሲም የመጀመሪያ ዲግሪያቸው በሕግ ትምህርት ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በፌደራሊዝም እና አካባቢያዊ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል:: <./p>