የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ባልተካሄደባቸው የተወሠኑ ምርጫ ክልሎች ላይ በተያዘው ዓመት ምርጫውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሠረት በአማራ ክልል በሮቢት፣ በኤፌሶን፣ በማጀቴ፣ በሞላሌ እና በአርጎባ ልዩ ምርጫ ክልሎች ለሚያካሄደው ምርጫ፤ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት በተጠቁሱት አካባቢዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንድታመለከቱ ቦርዱ ይጠይቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡-

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣

• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣

• መኖሪያ አድራሻ፦ በምርጫ ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች፣

• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣

• የሥራ ቦታ፦ በተጠቀሱት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች፣

• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን ብር 250 በድምሩ፣

• በክልሉ የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆኑ ይመረጣል፣ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

በመሆኑም ከዚህ በላይ የቀረበውን መሥፈርት የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ከታች በተያያዘውን ማስፈንጠሪያ አማካኝነት ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ለስምንት ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል።

https://pollworkers.nebe-elections.org/recruitment

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

የስራ ማስታወቂያ
ጥር 8 ቀን 2015 ዓ.ም.