የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ከታኅሣሥ 11 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በ3753 ምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው የሕዝበ ውሣኔ የመራጮች ምዝገባ 1,773,670 መራጮችን የመዘገበ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 217 የአካል ጉዳተኞች ይገኙበታል። አጠቃላይ የተመዝጋቢው ቁጥር በፆታ ሲገለጽ 943,076 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 830,594 ሴቶች ናቸው። ከተመዘገቡት የአካል ጉዳተኞች ውስጥም እንዲሁ 111 ሴቶች ሲሆኑ ቀሪ 106 ወንዶች ናቸው።

schedule

 

ማስታወቂያ