የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በሰሌዳው ላይ የተጠቀሱ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ሲተገብር ቆይቷል። ከዚህም ውስጥ ዋናው እና ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተገናኘው የምርጫ ምልክት መረጣ እና እጩዎች ምዝገባ ነው።
ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 ፓርቲዎች 49 (አርባ ዘጠኝ) የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶችን ወስደዋል።
1. የእጩዎች ምዝገባ ቀናት
የመጀመሪያ ዙር የካቲት 08-21 ለአራት ቀን የተራዘመ (አ.አ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ቤኒሻንጉል ፣ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ (ከምእራብ ወለጋ፣ ከምስራቅ ወለጋ፣ ከቄለም ወለጋ እና ሆሮጉድሩ ውጪ)
ሁለተኛ ዙር የካቲት15- 26 ለተጨማሪ አራት ቀናት የተራዘመ (በአማራ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እና በሲዳማ ክልሎች) የተከናወኑ ሲሆን የእጩዎች ምዝገባ በአጠቃላይ ለ22 ቀናት በ673 የምርጫ ክልልሎች ላይ ሲፈጸም ቆይቷል። በዚህም ወቅት የተለያዩ ሂደቱን ያጓተቱ ዋና ዋና ችግሮች ያጋጠሙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ
• የምርጫ ቁሳቁስ ለማጓጓዝ የትራንስፓርት ትብብር ማነስ
• የምርጫ ክልል ጽ/ቤት ስራው ከተጀመረ በሁዋላም ቢሆን ቢሮዎች እና ቁሳቁስ ማዘጋጃ ቦታዎች ሳይዘጋጅ በመቅረቱ መዘግየት እና የአስፈጻሚዎች መንገላታት
• አስቀድሞም ግጭቶች የነበሩባቸው ቦታዎች ልዩ የሆነ የቁሳቁስ እንቅስቃሴም ሆነ ዝግጅት ማስፈለጉ እና ጊዜ መውሰዱ (ቤኒሻንጉል መተከል ዞን፣ ኦሮሚያ አራት ዞኖች)
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ቦርዱ ትብብር ከሚሰጡት አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ማካሄድ፣ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የኦፕሬሽን ዴስክ በማቋቋም፣ የመረጃ መስጫ ማእከል (665) በማቋቋም ለመፍታት ጥረቶችን አድርጓል።
2. ከተሳታፊ ፓርቲዎች አቤቱታዎቹ የሚቀርቡበት መንገድ
በእጩዎች ምዝገባ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ሲሰራ ቆይቷል። ከነዚህም መካከል
ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባጋጠማቸው ችግር ዙሪያ ምክከሮችን ማካሄድ - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎችን ምዝገባ አስመልክቶ ሶስት ምክክሮችን በማዘጋጀት ግልጽነት የጎደላቸውን ሂደቶች ማብራራት፣ ለቀረቡ አቤቱታዎቸች ምላሽ መስጠት እና በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ያሉ ያሰራር ጉድለቶችን ለማረም ችሏል።
የፓርቲዎች አቤቱታ መፍቻ ዴስክ - የፓርቲዎች አቤቱታ ማቅረቢያ እና ፈጣን ምለሽ መስጫ ዱስክ እንዲሁም በስልክ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች፣ አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽ ለመስጠት ችሏል።
አቤቱታ ማቅረቢያ የስልክ መስመሮች - በእያንዳንዱ ክልል ለሚያጋጥሙ ችግሮች የተመደቡ የስልክ መስመሮችን በማዘጋጀት በስልክ ጥሪ አቤቱታዎቸን ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
እስካሁን አቤቱታ/ጥያቄ/ ጥቆማ ያቀረቡ ፓርቲዎች - ከ 16 በላይ ፓርቲዎች ከላይ በተጠቀሰው መንገድ አቤቱታዎችን አቅርበው መፍትሄዎች ተሰጥቷቸዋል።
3. የአቤቱታዎቹ የጥቆማዎቹ አይነቶች
በእጩዎች ምዝገባ ላይ ያጋጠሙ የአፈጻጸም ችግሮችን የተመለከቱ
1. አስፈጻሚዎች የሌሉባቸው ቦታዎች
2. የምርጫ ክልል ቢሮዎች መከፈት መዘግየት
3. አስፈጻሚዎች መመሪያውን ሲያስፈጽሙ ያጋጠሙ የመረዳት ችግሮች
4. በየወረዳው ተንቀሳቅሶ እጩዎች የማስመዝገብ የፀጥታ ችግር
5. የምርጫ ክልል ቢሮዎች አለመታወቅ እና የልዩ አድራሻ ጥያቄ
6. በተለያየ ምክንያት ለአጭር ጊዜ በፀጥታ ሃይሎች የተያዙ እጩዎች
የእጩዎች ምዝገባ ከተጀመረ በኋላ በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች
- የምረጡኝ ዘመቻ አድራጊዎች ለአጭር ጊዜ መያዝ፣ እቃ መወሰድ - ጋምቤላ
- የወረዳ ሃላፊዎች ማስፈራራት (የግል እጩ ሪፓርት ያደረጉት)
- የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም የሚል ማስታወቂያ የለጠፈ ወረዳ (ደቡብ ክልል)
- እጩነት በምዝገባ ላይ እያሉ በጸጥታ ሃይሎች የተያዙ
7. የተሰጡ መፍትሄዎች
- የሚያምታቱ እና ግልጽነት የጎደላቸው አሰራሮች ላይ ለአስፈጻሚዎች ተደጋጋሚ መልእክቶችን ( በአጭር መልእክት ሲስተም አማካኝነት) ማስተላለፍ እና አሰራሮችን ማሻሻል
- በቦርዱ የመረጃ ማእከል አማካኝነት አስፈጻሚዎችን ጥያቄ መመለስ እና አሰራርን ግልፅ ማድረግ
- የፓሊሲ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን መውሰድ እና በጽሁፍም ጭምር ማሳወቅ (ቦርዱ መመሪያ ያሻሻለባቸው ፣ መግለጫ ያወጣባቸው ጉዳዮች አሉ)
- የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች አቅራቢያ ባሉ የምርጫ ክልሎች አንዲመዘገቡ ተደርጓል
- አስፈጻሚዎች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች እየታዩ ነው (ሁለት ዋና አቤቱታዎች)
- የምርጫ ክልል ቢሮዎች ያሉበት ልዩ ቦታን የያዘ ሰነድ ይፋ ተደርጓል
- አስፈጻሚዎች ዘግይተው መክፈታቸውን ተከትሎ የቀናት ጭማሪ እና ክትትል ተደርጓል
ዕጩዎች ያቀረቡ ፓርቲዎች ዝርዝር
1. ሐረሪ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
2. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
3. ራያ ራዩማ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
4. ቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5. ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
6. ብልፅግና ፓርቲ
7. ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
8. ኅዳሴ ፓርቲ
9. ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
10. አዲስ ትውልድ ፓርቲ
11. እናት ፓርቲ
12. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
13. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
14. የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
15. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
16. የጌድዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
17. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
18. የሲዳማ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
19. የሲዳማ አንድነት ፓርቲ
20. የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
21. የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
22. የአገው ብሔራዊ ሸንጎ
23. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
24. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ
25. የአርጎባ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
26. የአርጐባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
27. የአፋር ሕዝብ ፓርቲ
28. የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ
29. የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር
30. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ
31. የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ
32. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
33. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ
34. የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ
35. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ-ፍትህ ፓርቲ
36. የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት
37. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
38. የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ
39. የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት
40. የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
41. የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር
42. የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
43. የዶንጋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
44. የጋምቤላ ህዝቦች ፍትህ ለሰላም እና ልማት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ
45. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
46. የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
47. የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት
በግል የተወዳደሩ - 125 እጩዎች
አራት ፓርቲዎች ለክልል ምክር ቤት ብቻ የተወዳደሩ ሲሆኑ ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ለተወካዮች ምክር ቤት ብቻ የተወዳደሩ ናቸው።