የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ለሚያካሂደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ሲሆን በዚሁ ስራ ይረዳ ዘንድ ለአጭር ጊዜ የፕሮጄክት አስተባባሪ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ - የፕሮጄክት አስተባባሪ
የስራ ጊዜው - የአጭር ጊዜ ማስተባበር (21 ቀናት)
የስራ መደቡ ዋና ዋና ሃላፊነቶች
-ለሲዳማ ሪፈረንደም አፈጻጸም ፕሮጄክት ስራ የማስተባበር ድጋፍ መስጠት
-ከቦርዱ የምርጫና ሎጀስቲክስ ክፍል ጋር በመተባበር የምርጫ ዝግጅቱን እና ሂደቱን ማገዝ
-አስፈላጊ ከሆኑ የተለያዩ አካላት ጋር ግንኙነቶችን ማድረግና ስራዎች በእቅድ መሰረት መፈጸማቸውን ማረጋገጥ
-የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የሚመለከቱ ውይይቶችን እና ሁነቶችን ማዘጋጀት፣ማስተባበር
-አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከቦርዱ የሚፈለጉ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መስጠትና በተመሳሳይም ለቦርዱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማጠናከር
-የስራውን ሂደት እና ውጤት አስመልክቶ ከቦርዱ የምርጫና ሎጀስቲክስ ክፍል ጋር በመተባበር ሪፓርት ማጠናከር
ተፈላጊ ችሎታ

-የመጀመሪያ ደረጃ ዲግሪ
-ቢያንስ ለ5 አመት ያህል የማስተባበር ስራ ልምድ
-የምርጫ እና ተያያዥ ሂደቶችን በሚገባ የሚረዳ/የምትረዳ
-በፍጥነት ችግሮችን የመፍታት ክህሎት ያለው/ያላት
-በአጭር ጊዜ የማስተባበር ስራዎችን የመስራት ልምድ ያለው/ያላት
-መረጃዎችን መሰብሰብና ሪፓርት ማጠናቀር ልምድና ችሎታ ያለው/ያላት
-የፌደራሉን የስራ ቋንቋ በሚገባ መጻፍና መናገር የሚችል/የምትችል፣ (ተጨማሪ ቋንቋ ማወቅ ይበረታታል)
ክፍያ - በስምምነት
ለማመልከት - ለስራው ማመልከት የሚፈልጉ አመልካቾች ሲቪ እና የተጠቀሱትን ችሎታቸውን የሚገልጽ ሸኚ ደብዳቤ በማዘጋጀት የሚልኩት ኢሜል ርእስ ላይ ፕሮጄክት አስተባባሪ የሚል በመጻፍ electionsethiopia [at] gmail.com መላክ ይችላሉ፡፡
የማመልከቻ ጊዜ - ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ3 የስራ ቀናት ብቻ
 

የስራ ማስታወቂያ
ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም.